loader
 • የግብረ ስጋ ግንኙነት ምንነት በትዳር ውስጥ።

  @Miss Counselor   4 months ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @Miss Counselor   4 months ago
  Sewasewer
  የግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት ባለትዳር በሆኑ ጥንዶች መካከል ማለትም በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ለጠለቀ ግንኙነት፣ ለስሜት እርካታና ልጅን ለመውለድ የሚደረግ አካላዊ ወይም ወሲባዊ ግንኙነት ነው :: የግብረ ስጋ ፍላጎትን በማሟላት ፍቅርን የመሥራት ወይም የመገንባት ሂደት ነው። ባለትዳሮች መካከል ችግሮችና አለመግባባቶች እንዲፈጠሩ ከሚያደርጉ ምክንያት አንዱ በግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣምና አለመርካት ወይም መልካም የሆነ ግንኙነት አለመኖር ነው። በግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣም ራሱን የቻለ ያለመግባባት መንስኤ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በትዳር መካከል የሚፈጠሩ የተለያዩ ችግሮችን የሚያባብስ አቀጣጣይ የመሆን ሚናም ይጫወታል ::

  በግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣም የሚፈጠሩ ችግሮች ግለት ቶሎ እንዳይበርድ የሚያደርግና ቀስ በቀስም የትዳርን ህልውና የሚያጠፋ የተዳፈነ እሳት ሊሆን ይችላል። ከባህላችን ተጽዕኖ የተነሳ በትዳር ውስጥ ፍላጎታችንና ችግራችንን በፍጹም ግልጥነት የማናወራበትና የማንወያይበት ጉዳይ ቢኖር የግብረ ስጋ ግንኙነት ነው። የጋብቻ አስተማሪዎችም ሆንን አማካሪዎች እንደ ሌሎች ችግሮች በድፍረት የማናስተምርበትና የማናማክርበት ርዕሰ ጉዳይ ከመሆኑ የተነሳ ችግሩ ከመቼውም በበለጠ እየጨመረና እየተባባሰ በመምጣቱ ብዙዎች ለአለመግባባት፣ ለመለያየትና ለፍች ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል። በትዳር ላይ የሚፈጠር የግብረ ስጋ ግንኙነት አለመጣጣም ችግር ጥንዶቹ ሊያስተካከሉት ፍላጎት ካላቸውና ተገቢ ጥረት ካደረጉ በሂደት ሊቀንስ ይችላል፡፡ እንደገናም በተለያዩ እርዳታዎችና ሕክምናዎች የመሻሻልና የመስተካከል ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ልንገነዘብ ይገባል።

  በትዳር ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎትና ድርጊት አንዱ የጋብቻ ክፍል እንጂ የትዳር ሁሉ ነገር አድርገን ከማሰብ መቆጠብና ሌላው የትዳር ገጽታ የሚጠይቀውን የሁለትዮሽ መሰጠት፣ መተሳሰብና መረዳዳት መዘንጋት አይገባንም። በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስንተሳሰብና ስንረዳዳ በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ወደ መጣጣም መምጣት የሚያስችለንን መልካም ስሜት መፍጠርና ማሳደግ እንችላለን:: በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ትምህርትና ምክር ሊሰጥበትና ባለትዳሮች የሆንን አንዱ ሌላውን በመረዳት፣ በመተሳሰብና በመጣጣም አንድነታችንና የጠለቀ ግንኙነታችንን እያጠናከርን ልንኖር ይጠበቅብናል።

  ምንጭ
  የግጭት መንስኤዎቻቸው እና መፍትሔዎቻቸው ፣ ፓስተር ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ።
 • loader Loading content ...