loader

Topics (8)


loader Loading content ...

Explanations (10)


 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መስራች ዲ/ ን ዳንዔል ክብረት ሲሆን አላማው ለኢትዮጵያ በጎ የሰሩ እና ለሌሎች አራያ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማበረታታት እና እውቅና መስጠት ነው። የሚከተለው ሃተታ ከበጎ ሰው ድረ-ገፅ ላይ የተወሰደ ሲሆን የድርጅቱን አላማው ባጭሩ ይገልፃል።

  " የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ኢንዱስትሪያሊስቶች፣ የዲፕሎማሲ ሰዎች፣ ወዘተ የማበረታታት፣ የማድነቅ፣ የመሸለምና ዕውቅና የመስጠት ባህል እምብዛም የለንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የመተቻቸትና የመናናቅ፣ የመመቀኛኘትና የመጓተት ልማዶች ጎልተው ይታያሉ፡፡ ይህንን መሰሉን ባህል ባለማዳበራችን የተነሣ የሚሠሩ ሰዎች ያመጡትን ለውጥ ዐውቀው ይበልጥ እንዲተጉ፣ ሌሎች ደግሞ የእነርሱን አርአያ ተከትለው ለሀገራቸው እንዲሠሩ አላደረግናቸውም፡፡ ትውልዱም የእርሱን ዘመን ጀግኖች እንዳያገኝ ዕንቅፋት ሆኖበታል፡፡ በዚህም የተነሣ የውጭውን አድናቂና ናፋቂ ሆኗል፡፡ ይህንን ልማድ ለመቅረፍና ሀገራዊ ጀግኖችን ለማውጣት፣ ለመሸለምና ትውልዱ እንዲያውቃቸው ለማድረግ መሥራት የመንግሥት ብቻ ኃላፊነት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ሊፈጽመው የሚገባ የዜግነት ግዴታው ነው፡፡ "


                  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መስራች ዲ/ ን ዳንዔል ክብረት

  የበጎ ሰው ሽልማት የተለያዩ ዘርፎችን ያካተተ ሲሆን የሚከተሉት አስር ዋና ዋና የእጩ መጠቆሚያ ዘርፎች ናቸው።

  1. ሰላም:- በዚህ ዘርፍ ለሀገራዊ ሰላም፣ ለሕዝቦች መግባባት፣ ለግጭቶች መፈታት፣ ማኅበረሰቡ ላቅ ያለ ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ የሠሩ ይሸለማሉ

  2. ሳይንስ:- በሕክምና፣ በቴክኖሎጂ፣በፊዚክስ፣ በኬሚስሪ፣ በምሕንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ ወዘተ የሠሩ ይሸለማሉ

  3. ኪነ ጥበብ:- በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች በአዲስ መንገድ፣ በልዩ አቀራረብ፣ የሥነ ጽሑፍን ደረጃ ከፍ ያደረጉ፣ በማኅረሰቡ ዘንድ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሥራ የሠሩ፣ ለኪነ ጥበባችን ዕድገት የተጉ ዜጎች ይሸለማሉ ሀ. ፊልም ለ. ሙዚቃ ሐ. ሥነ ጽሑፍ መ. ቴአትር ሠ. ሥዕልና ቅርጻ ቅርጽ

  4. የበጎ አድራጎት ሥራዎች:- በርዳታና ሰብአዊ አገልግሎት የሠሩ ይሸለማሉ

  5. ግብርና ንግድና የሥራ ፈጠራ:- በንግድ(ቢዝነስ)፣ በግብርና እና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሥራዎች በመፍጠር፣ አዳዲስ የሥራ ሐሳቦችን በማመንጨት የሠሩ ይሸለማሉ

  6. ስፖርት:- በስፖርቱ መስክ አርአያነት ያለውና በጎ ተጽዕኖ የሚያመጣ ሥራ የሠሩ ይሸለማሉ

  7. መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን መወጣት:- በተመደቡበት መንግሥታዊ የኃላፊነት ዘርፍ አርአያ የሚሆን ለውጥ ያመጡና ተገቢውን ሕዝባዊ አገልግሎት የሰጡ

  8. ማኅበራዊ ጥናት:- በማኅበራዊ ጥናት መስክ ተሠማርተው የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ ችግሮች የሚፈቱና አዳዲስ ግንዛቤ የሚያመጡ፣ ዕውቀት የሚጨምሩ ላቅ ያሉ ሥራዎችን የሠሩ ይሸለማሉ

  9. ሚዲያና ጋዜጠኝነት፡ በሚዲያና በጋዜጠኝነት መስክ ለውጥ አምጭና በጎ ተጽዕኖ አሳዳሪ ሥራ የሠሩ ይሸለማሉ

  10.  ቅርስና ባሕል:- ቅርስና ባሕልን በመጠበቅ፣ በማስተዋወቅ፣ በመሰነድና ዓለም ዐቀፍ ዕውቅና እንዲያገኝ በመሥራት ለውጥ ያመጡ ይሸለማሉ፡፡ 
  የሚከተሉት አስራ አምስት ነጥቦች ደግሞ እጩዎችን የመጠቆሚያ መመዘኛዎች ናቸው።

  1. የሚጠቆመው እጩ በሕይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ሰው ወይም ተቋም መሆን አለበት
  2. የምንጠቁማቸው ኢትዮጵያውያን በጎ ለውጥ አምጭ የሆነ ሥራ የሠሩ መሆን አለባቸው፣
  3. የዜጎችን ሕይወት በማሻሻልና ሀገርን በማሳደግ ሊጠቀስ የሚችል ነገር ያከናወኑ መሆን አለባቸው፣
  4. አንድ ሰው በተለምዶ ሊሠራው ከሚገባው ወይም ከሚችለው ሥራ ላቅ ያለ ሰብእና የሚታይበት ተግባር የፈጸሙ መሆን አለባቸው፤
  5. በአሠራር፣ በአስተዳደር፣ በጥናትና ምርምር፣ በኪነ ጥበብና በማኅበራዊ አገልግሎት አዲስ መንገድ ያመላከቱ፣ አዲስ አሠራር የዘረጉ መሆን አለባቸው፣
  6. የሀገርና የሕዝብን ችግር የፈታ ተግባር የከወኑ መሆን አለባቸው
  7. በተሠማሩበት መስክ መሥዋዕትነት ጠያቂ ግዳጅን የተወጡ፣ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን የሰጡ መሆን አለባቸው
  8. ይሁነኝ ብለው የሀገርንና የወገንን ስም የሚያስጠራ፣ ታሪካችንን፣ ባሕላችንን፣ ቅርሳችንን አጉልቶ የሚያወጣ የዜጋ ሥራ የሠሩ መሆን አለባቸው
  9. የማኅበረሰቡን ሞራላዊና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን ለሌሎች መጥፎ ምሳሌ በሚሆን መንገድ ያልጣሱና ለትውልዱ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  10. በተቻለ መጠን ከዚህ በፊት ሥራቸው ሊነገር፣ ሊዘከርና ሊታወቅ ያልቻለ
  11. ለሀገሪቱ ዕድገትና ሥልጣኔ ለውጥ አምጭ አስተዋጽዖ ያደረጉ
  12. ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ብቁ አመራሮችን የሰጡ፣ በአመራሮቻቸውም አካባቢያቸውን፣ ድርጅታቸውንና መሥሪያ ቤታቸውን የለወጡ፣
  13. አዲስ፣ የራሱ ወጥነት ያለውና ያልተደፈረ የሚመስለውን ሥራ ያከናወኑ፣
  14. የሀገሪቱን ክብርና ደረጃ ያስጠበቁ፣ የሀገሪቱንም መብት ያስከበሩ፣
  15. ሀገራቸውን በዓለም አደባባይ በበጎ ያስጠሩ፣ ስሟን ከፍ ያደረጉ

  ምንጭ:
  የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅት ድረ-ገፅ
  http://www.begosew.com/
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በ፳፻፭ ዓ/ ም በአምስት የተለያዩ ዘርፎች ፸ በጎ ግለሰብ ኢትዮጵያውያንን እና ፯ ተቇማትን ጥቆማ በመውሰድ የሚከተሉትን አምስት በጎ ሰዎች ሸልሟል።


                 በትምህርት መስክ - ንቡረ ዕድ ተፈራ መልሴ

  የርእሰ አድባራት አዲስ ዓለም ማርያም አስተዳዳሪ ናቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በትምህርት ያላደረሱት መስክ የለም፤ በሲመትም የታላቋ ደብር አለቃ ሆነዋል፡፡ ይህ እልቅናቸው እንደ ሌሎቹ ቤት ልሥራ፤ ዘር ልዝራ አላሰኛቸውም፡፡ ነገር ግን ሀገራዊ ጉዳይ ያሳስቸው ነበር፡፡ እርሳቸው አረጋዊ ናቸው፤ በእርጅና ጎንበስ ብለው ድካምን የሚጋፉት፤ እርሳቸው በዕድሜ ጣርያ ላይ ያሉ ናቸው፤ ዐርፈው መቀመጥ የሚያስፈ ልጋቸው፤ ግን እንዲህ አላደረጉም፡፡ በዚህ የእርጅና ዕድሜያቸው በመላው ዓለም እየዞሩ፣ እየለመኑና እያባበሉ ኢትዮጵያዊ ዕውቀት የሚገኝባቸው፣ ነገር ግን እንደ ዋልያና ቀይ ቀበሮ በመጥፋት ላይ ያሉት የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጠበቁ፣ ተሻሽለውም እንዲቀጥሉ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማሰባሰብ ተግተዋል፤ ድካም ሳያግዳቸው የሰው ፊት እያዩ ለአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሆን ገንዘብና ቁሳቁስ ሰብስበዋል፡፡ ይቀጥላል ...


                 በሚዲያ እና የሴቶች ኣስተዋጾ -- ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ

  በመረዋ ድምጽ፣ ልብን ሰርሥሮ በሚገባ፣ ቤተኛ በሚያደርግ የቃለ መጠይቅ ጥበብ እንደ መልካም ወገኛ በማጫወት የተካነች ናት፡፡ ለጋዜጠኝነት ሞያ ባላት ፍቅር ኢትዮጵያዊ መልክ ያላቸውን፣ ታሪክና ባህልን የሚያስታውሱንን ታላላቅ ሰዎቻችንን እንድናውቅ የሚያደርጉንን ፕሮግራሞች የሚያቅፍ የሬዲዮ ጣቢያ በመመ ሥረትና በመምራት፣ ታላላቅ ሰዎቻችንን ሞት ሳይቀድመን በፊት ቅርስ ሆነው እንዲቀሩ፣ የማይታወቁ ጀግኖቻችን ለአደባባይ በቅተው እንዲታወቁ በማድረግ፤ አንድ የተለየ ጣዕምና ሚና፣ አንድ የሚደመጥና የሚናፈቅ፣ አንድ ልዩ ቀለምና ጠባይ ያለው የሬዲዮ መሥመር ሸገር ሬዲዮን በመዘርጋት የተዋጣለት ተግባር እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ይቀጥላል...


         በማህበራዊ አገልግሎት -- የመቄዶኒያ አረጋውያንና የዓዕምሮ ህመምተኞች መርጃ ማዕከል መስራች ቢንያም በለጠ

  የ35 ዓመት ወጣት ነው፡፡ አያቱ በጎንደር ከተማ የታወቁ ነበሩ፡፡ ችግረኞችን በመርዳትና ሰው ለሌላቸው ሰዎች መጠጊያ በመሆን ነበር የሚታወቁት፡፡ እንዲያውም የተቸገረ ሰው ላመጣላቸው ሰው ወሮታውን በእህል ይከፍሉ እንደነበረ የከተማው ሰዎች ዛሬም ያስታውሷቸዋል፡፡ አባቱም በዚያው መንገድ ተጓዙና ሰው መርዳት ሆነ ነገር ዓለማቸው፡፡ በወቅቱ የሼል ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አባቱ አቶ በለጠ ደመወዛቸው 4000 ብር ነበር፡፡ በቤት ውስጥ ግን ልጆቻቸው ሽሮ እንኳን አጥተው ጦም የሚያድሩበት ጊዜ ነበር፡፡ ጠጥተውበት አይደለም፣ ቁማር ተጫዉተዉ ተበልተውም አልነበረም፡፡ ለችግረኞች የሚራሩ በመሆናቸው ለድኾች አከፋፍለው ስለሚጨርሱት እንጂ፡፡ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ያፈራል ነውና፤ ይህንኑ በጎ ነገር ልጃቸውም ወረሰው፡፡ ለታክሲ የተሰጠውን ገንዘብ በእግሩና በአውቶቡስ እየተጓዘ በመቆጠብ ችግረኛ ተማሪዎችን ይረዳበት ነበር፡፡ እንዲህ እየኖረና እየተማረ አድጎ አሥራ ሁለተኛ ክፍል አራት ነጥብ አመጣ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ገብቶ ሕግ ተማረ፡፡ ከዚያም ተመርቆ ጥቂት ጊዜ ሠራና አሜሪካ ገባ፡፡ ይቀጥላል ...


                 በኢኮኖሚ መስክ -- ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን

  የአፍሪካ የምግብ ችግር ከምርት ብቻ ሳይሆን ከምርቱ ገበያ ጋር የተያያዘ ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡ በዚህም የተነሣ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች ላይ ሠርተዋል፤ ተመራምረዋል፡፡ በዓለም ባንክ፣ ዋሽንግተን በሚገኘው ዓለም ዐቀፍ የምግብ ፖሊሲ ጥናት ማዕከል፣ እና በተባበሩት መንግሥታትም በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ በኢኮኖሚክስ ዲግሪያቸውን ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ፣ ማስትሬታቸውን ከሚችጋን ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፤ በአፕላይድ ኢኮኖሚክስ ደግሞ ፒ ኤች ዲያቸውን ከስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል፡፡ ለምግብ እህል እጥረት አንዱ ችግር የገበያው ሁኔታ ነው የሚከለውን የጥናት ውጤታቸውን እውን ይዘው ከነ መፍትሔው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ይቀጥላል ...


                 የወጣቱን የንባብ ባህል በማሳደግ -- ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ

  ደራሲ ነው፡፡ ሰባት ያህል መጻሕፍትን አቅርቦልናል፡፡ የተወለደው ወልቂጤ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚከታተልበት ጊዜ ‹ተስፋ› ብሎ በሰየማት አነስተኛ የመጻሕፍት መደብሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ እያከራየ የንባብ ባሕል እንዲዳብር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ እንደ ተከራዮቹ ሞያና የትምህርት ደረጃ ስለ መጻሕፍቱ አጭር ማብራርያ እየሰጠ፤አንብበው ሲመልሱም ስለ መጻሕፍቱ አስተያየት እየተቀበለ ያበረታታ ነበር፡፡ በወልቂጤ ከተማ ውጤታማነትን ለማበረታታት በራሱ ተነሣሽነት በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማቶችን ይሸልማል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሲሆን በዚህ የሥራ ድርሻው አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨትና በመተግበር ደራስያን እንዲጠቀሙ ድርሰትም እንድታብብ እያደረገ ነው፡፡ ይቀጥላል ...

  ምንጭ
  የበጎሰው ድረ-ገፅ እና የዳንዔል እይታ ድረ-ገፅ 
  http://www.begosew.com/index.php/4-2006-winner 
  http://www.danielkibret.com/2014/06/2006_10.html 
  ለሰፊ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል። 
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በ፳፻፮ ዓ/ ም በሰባት የተለያዩ ዘርፎች ከ፻፳ በላይ በጎ ኢትዮጵያውያንን ጥቆማ በመውሰድ የሚከተሉትን ሰባት በጎ ሰዎች ሸልሟል።


                 በባሕል፣ ቅርስና ቱሪዝም ዘርፍ - ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ

  የሐረር ሸሪፍ ሙዝየም መሥራችና ባለቤት የተማሩት የአካውንቲንግ ሞያ የሠሩት በጭላሎ እርሻ ልማት ቢሆንም የሀገራችን ታሪክና ቅርስ ጉዳይ የሚቆጫቸው ሰው ናቸው፡፡ ከ23 ዓመት በፊት የሐረርን ታሪክ፣ ቅርስ፣ የወግ ዕቃዎች፣ በቁፋሮ የተገኙ ታሪካዊ መረጃዎች፣ መጻሕ ፍትና ሌሎችንም በቤታቸው ውስጥ ማሰባሰብጀመሩ፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ የሚያምናቸውና የሚያከብራቸው አብዱላሂ ሸሪፍ ሕዝቡ ሥራቸውን ተመልክቶ ያገኛቸውንና በእጁ የሚገኙትን መረጃዎችና ቅርሶች ይሰጣቸውነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ቤታቸውን ሙዚየም አድርገው ሲያሰባስቡና ሲያሳዩ የነበሩት አብዱላሂ ሸሪፍ ለሥራው ዋናው የገቢ ምንጫቸውም የራሳቸው ገቢ ነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ሲሠሩበት የነበረው ቤታቸው ‹‹በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግለሰብ የቅርስ ስብስብ›› ተብሎየተመዘገበ ሲሆን በ1990/91 ዓም ወደ ሌላ ቦታ ተዛወረ፡፡ የሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ሙዝየም የሐረር ገዥ የነበሩት ራስ ተፈሪ ወደ ነበሩበት ቤት በ1990/91 ዓም የተዛወረ ሲሆን ዛሬ ይህ ሙዝየም ‹‹ሸሪፍ የሐረር ከተማ ሙዝየም›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ በዚህ ሙዝየም ውስጥ ከ1200 በላይ ጥንታውያን መጻሕፍት፣ ከ400 ሰዓታትበላይ የሚወስዱ ጥንታውያን የድምጽ መረጃዎች፣ ጥንታውያን ሳንቲሞችን፣ ከመካከለኛው ዘመን ጀምረው የነበሩ የጦር መሣርያዎችን፣ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ ፎቶዎችን፣ የሐረርን የንግድ ግንኙነት የሚያሳዩ ሳንቲሞችን፣ መዛግብትን፣ የወግ ዕቃዎችን ሰብስበዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  በኪነ ጥበብ ዘርፍ - ታላቁ የጥበባት ባለ ሀብት ተስፋየ ሣሕሉ 

  ሰኔ 12 ቀን 1916 ዓም ባሌ ውስጥ ከዱ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ የትምህርት ዕድል ያገኙት ወላጆቻቸው ወደ ሐረር ከተዛወሩ በኋላ ነው፡፡ በአሥራ አራት ዓመታቸው አባታቸው አቶ መንበረ ወርቅ ለሚባ ሰው አደራ ሰጥተዋቸው ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡ አሳዳጊያቸውና ቤተሰቦቻቸው በጣልያን ጦርነት በማለቃቸው መጀመሪያ ጫማ በመጥረግ በኋላም በሆስፒታሎች አካባቢ በማገልገል ራሳቸውን ለመደገፍ ሞከሩ፡፡ ከዚያም ደግሞ በእቴጌ ሆቴል(ጣይቱ ሆቴል) ተቀጥረው ሠርተዋል፡፡ እዚሁ ሆቴል ሲሠሩ መጀመሪያ ክራርና ማሲንቆ ቀጥለውም ፒያኖ መጨዋት ጀመሩ፡፡ ከጣልያኖች ጋ በተፈጠረ አለመግባባት ከአዲስ አበባ ሐረር ተላኩ፡፡ እዚያ እያሉ ጣልያን ከኢትዮጵያ ተባረረ፡፡ በሐረርም የራስ ሆቴል የምግብ ቤት ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ በ1934 ዓም በጦርነት ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች ይሰብሰቡ ሲባል አባባ ተስፋዬ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ በዚሁ ዓመትም ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች የሚማሩበት ትምህር ቤት ገብተው መማር ጀመሩ፡፡ ይቀጥላል...


                 በሰብአዊ አገልግሎት ዘርፍ - ዶክተር በላይ አበጋዝ

  ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የልብ ሐኪም ዶክተር በላይ አበጋዝ የተወለዱት ህዳር 13 ቀን 1937 ዓ.ም በደሴ ከተማ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ያጠኑት ደግሞ ሕክምና ነው፡፡ በኋላም በሕጻናት ልብ ህክምና ስፔሻላይዝድ አደረጉ፡፡ ዶክተር በላይ ከ1973 ዓም ጀምረው ላለፉት 30 ዓመታት በሕጻናት ሕክምናና በሕጻናት ካርዲዮሎጂስትነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አገልግለዋል፡፡ ፔዲያትሪክስን በማስተማር፣ ስለ ሞያውም ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማሳተም ይታወቃሉ፡፡ከ1981 ዓም ጀምረው የአሜሪካ ፔዲያትሪክስ አካዳሚ አባል ሲሆኑ፣ በInternational Society of Hypertension in Blacks, The Pan African Society of Cardiology, The National Drug Advisory Board of Ethiopia አባል ሲሆኑ በEthiopian Medical Journal በአባልነት፣ በረዳት ዋና ጸሐፊነትና በሊቀ መንበርነት አገልግለዋል፡፡ ዶክተር በላይ አበጋዝ የማይረዱትና የማያግዙት የዓለም ክፍል የለም ለማለት ያስችላል፡፡ የHealing the Children USA, Save a Child's Heart ISREAL and Chain of Hope UK ተባባሪ ናቸው፡፡ ይቀጥላል...


                  በንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርናና ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ - ቤተልሔም ጥላሁን

  /ሮ ቤተልሔም ጥላሁን ሶል ሪብልስ የተሰኘው በአፍሪካ ታዋቂ ከሆኑት ጫማ አምራቾች አንዱን የመሠረቱና የሚመሩ ሰው ናቸው፡፡ ድርጅቱን የመሠረቱት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2005 ዓም ሲሆን ዋና ተግባሩም ኢትዮጵያ ውስጥ በባሕላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውል ይነበረውን በርባሶ ጫማ በዘመናዊ መንገድ አምርቶ ለዓለም ገበያ ማዋል ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዘነበ ወርቅ አካባቢ ተወልደው ያደጉት ወ/ሮቤተልሔም ጥላሁን በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎች በድህነት ምክንያት ብዙዎቹ ሥራ አጦች መሆናቸውን፤ ነገር ግን ማንም ያልተጠቀመበት ክህሎት ያላቸው መሆኑን በማስተዋል የእነዚህን ወገኖች አቅም ወደ ምርትና ገበያ ለመለወጥ ተነሡ፡፡ በዚህም መሠረት እኤአ በ2004 ዓም ከባለቤታቸውና ከቤተሰቦቻቸው ባገኙት የመነሻ ገንዘብ በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ከሚገኙ ታዋቂ የጫማ አምራቾች አንዱ የሆነውን ሶል ሪብልስ የተሠኘውን ኩባንያ መሠረቱ፡፡ በባሕላዊ መንገድ ይመረቱ የነበረውን የበርባሶን የአመራረት መንገድ በዘመናዊ መልክ በማምጣት ለአካባቢ ብክለት አስተዋጽዖ የማያደርግ፣ ካርቦን ዜሮ የሆነ ጫማ ለማምረት ችለዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ሀገራዊ ሰላምና ዕርቅ - ብጹዕ አቡነ ዮናስ

  ብጹዕ አቡነ ዮናስ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ ወደ አፋር አካባቢ የመጡት በ1972 ዓም ነው፡፡ የሁሉም አባት በመባል በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ የሚጠሩት አቡነ ዮናስ አያሌ የአፋር ልጆችን ፊደል ያስቆጠሩና ለከፍተኛ ማዕረግም ያደረሱ ናቸው፡፡ በተለይም በአፋር አካባቢ ያለው የመጠጥ ውኃ ችግር እንዲቀረፍ ገጠር ወርደው በማስተማር ሕዝቦ ችግሩን ራሱ እንዲቀርፍ አነሣስተዋል፡፡ ለአካባቢው አረጋውያን መኖሪያ 5227 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ እየሠሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 50 አረጋውያን በቦታው ይረዳሉ፡፡ ይህንን የአረጋውያን መርጃ ፕሮጀክት ለመደገፍም 7 ሄክታር መሬት ከመንግሥት ተቀብለው ከጃፓን ኤምባሲ ጋር በመሆን የአካባቢውን ሕዝብ አስተባብረው እያለሙ ናቸው፡፡ ይቀጥላል ...


                 በጥናትና ምርምር ዘርፍ - አምባሳደር ዘውዴ ረታ

  ጋዜጠኛ ዲፕሎማትና ደራሲ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተወለዱ፡፡ ቀድሞ ደጃዝማች ገብረ ማርያም ይባል በነበረውና ኋላ ‹‹ሊሴ ገብረ ማርያም›› ተብሎ በተሰየመው የፈረንሣይ ትምህርት ቤት የመጀመ ሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ከ1948 ዓ.ም እስከ 1952 ዓ.ም በፓሪስ የጋዜጠኝነት ሞያ ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ የሊሴ ገብረማርያምን ትምህርት ለጊዜው አቁመው እያሉ በ1945 ዓ.ም የራዲዮ ዜና አንባቢ ሆነው ሥራ ጀመሩ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አምባሳደር ዘውዴ ረታ በጋዜጠኝነት በዲፕሎማትነትና በመጨረሻም በደራሲነት በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ከ1945 ዓ.ም እስከ 1967 ዓ.ም በጋዜጠኝነት ሙያ በጋዜጣና ማስታወቂያ መሥሪያ ቤት የቤተ መንግሥት ዜና ጋዜጠኛና በራዲዮ ዜና አቅራቢ፣ የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣና የመነን መጽሔት ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ራዲዮ የብሔራዊ ፕሮግራም ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ወሬ ምንጭ ዋና ዲሬክተር ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት - አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ

  አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ለሃምሳ ሁለት ዓመታት አገራቸውን በዲፕሎማሲ መስክ ያገለገሉ አንጋፋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዓመታት አገራችንን ወክለው በተባበሩት መንግሥታት፣ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በአፍሪካ ህብረት በሠሩባቸው ጊዜያት በዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ በሰብዓዊ መብት፣ በስደተኞች፣ ትጥቅ በማስፈታት፣ በጸረኮሎኒያሊዝምና በመሳሰሉት ሰፊ እውቀትና የሥራ ልምድ አላቸው፡፡ እ.አ.አ. በ1962 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዲፕሎማትነት ሥራቸውን የጀመሩት በተባበሩት መንግሥታት መምሪያ ውስጥ ሦስተኛ ጸሐፊ ሆነው ነበር፡፡ ከሦስት ዓመት በኋላ ዕድገት አግኝተው በሁለተኛ ጸሐፊ ማዕረግ ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት እንዲሠሩ ተመደቡ፡፡ በዚህ ኃላፊነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ እ.አ.አ. በ1970 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በቅድሚያ በአፍሪካ መምሪያ ቀጥሎም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ገለልተኛ አገራት መምሪያ ውስጥ በፖለቲካ ኦፊሰርነት ሠርተዋል፡፡ ይቀጥላል...

  ምንጭ:
  የበጎሰው ድረ-ገፅ እና የዳንዔል እይታ ድረ-ገፅ
  http://www.begosew.com/index.php/4-2006-winner
  http://www.danielkibret.com/2014/06/2006_10.html
  ለሰፊ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  በኦሮሚያ ወለጋ የተወለደው አብዲሳ የኢትዮጲያን ጦር የተቀላቀለው በ14 አመቱ ሲሆን ጣልያን ኢትዮጲያን ስትወር አገሩን ለመከላከል በሚደረግ ውጊያ ላይ መሳተፍ ጀመረ። እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎች ከታጠቀው የጣልያን ጦር ጋር በሚደረገው ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሱማሊያ በኩል ወደ ሲሲሊ ተወስዶ በጣልያን አገር የጦር እስረኛ ተደረገ።


                  ሻምበል አብዲሳ አጋ

  በእስር ቤት ጠባዎች ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት አብዲሳ እዛው ታስሮ የሚገኝ ሁሊዮ የተባለ የዩጎዝላቪያ ምርኮኛ በጋራ እቅድ በማውጣት ከእስር ቤት ማምለጥ ቻለ። ከእስር ካመለጡ በኋላ ከፋሺስት ጣልያን ወታደሮች በመደበቅ እና በመሸሽ ፋንታ በአብዲሳ መሪነት እና እቅድ አውጪነት በሌሊት ታስረው ወደነበረበት እስር ቤት ተመልሰው ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም የታሰሩትን እስረኞች በሙሉ ነጻ በማውጣት የኢትዮጲያውያንን ጀግንነት በአድዋ ብቻ ሳይሆን በጣልያን ምድርም ያስመሰከረ ድንቅ ተዋጊ ነበር። የአብዲሳ ጀግንነት በዚህ አላበቃም ከእስር ቤት ያስመለጧቸውን ሰዎች በማሰባሰብ የራሱን ጦር ካደራጀ በኋላ ጣልያኖችን በገዛ አገራቸው ያንቆራጥጣቸው ገባ። ከአድዋ ጀምሮ የኢትዮጲያውያንን ወኔ የተረዱት ጣልያኖች የአብዲሳን ጦር በፍርሃት ያዩ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች ከጣልያን ጦር ጋር በመዋጋት ብዙ ድሎችን እያስመዘገበ ነበር። ቆራጥነቱን የተረዱት ጣልያኖች የሚያረጉት ግራ ቢገባቸው ከበርካታ ስጦታዎች ጋር ጦሩን ይዞ የጣልያንን ሰራዊት እንዲቀላቀል መማጸን ጀምረው ነበር። ለፋሺስት ጦር መዋጋት አገር መክዳት እንደሆነ አስረግጦ የተናገረው አብዲሳ ትግሉን አፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት የሁለተኛው የአለም ጦርነት ተቀሰቀሰ። 

  የተባበሩት የአሜሪካ እና እንግሊዝ መንግስታት ከጀርመን ጋር ያበረችውን ጣልያንን እየተዋጉ በነበረ ሰዓት ስለ አብዲሳ ዝና ከሰሙ በኋላ ለጦሩ የሚገባውን ድጋፍ በማድረግ የፋሺስት ስርዓቱን ለማዳከም ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ሆኗቸው ነበር። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋ ሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር። ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። 

  ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግስታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። እብዲሳ ግን ኢትዮጲያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ህዝቡን እና መንግስቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ውድቅ አደረገ። በዚህ የተናደዱ ምዕራብውያንም በፈጠራ ወንጀል ከሰው ወደ እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ከተከፈለ በኋላ በክብር ወደ ሃገሩ ሊመለስ ችሏል። ወደ ኢትዮጲያ ከተመለሰ በኋላ ሰራዊቱን በቅንነት ያገለገለው አብዲሳ በኮረኔልነት ማዕረግ የአጼ ሃይለስላሴ ልዩ ጠባቂ ጦር እየመራ ቆይቶ ንጉሱ ከስልጣን ከወረዱ ከጥቂት አመታት በኋላ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

  ምንጭ: 
  • http://thearadaonline.com/2013/03/17/ያልተዘመረለት-ጀግና-አብዲሳ-አጋ/
  • በኢጣልያ በረሃዎች (ሻምበል አብዲሳ አጋ በአርበኝነት ጀብዱ የሰራ ኢትዮጵያዊ ታሪክ)

 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  አሰላ በድሮው የኢትዮጵያ አወቃቀር የአርሲ ዋና ከተማ ነበረች። በአሁኑ ወቅት ግን አርሲ ክፍለ ሃገር በሁለት ተከፍላለች -- ምዕራብ አርሲ እና ምሥራቅ አርሲ። አሰላ የምሥራቅ አርሲ ዋና ከተማ ስትሆን ሻሸመኔ ደግሞ የምዕራብ አርሲ ዋና ከተማ ነች።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ታህሳስ ወር 1928 ዓ/ም የመጀመሪያው የኢትዮጵያውያን ክለብ እውን ሆነ፡፡ የአራዳ አካባቢ ልጆች ከኪሳቸው ገንዘብ አዋጥተው ራሳቸውን ተጨዋቾች አድርገው ቅዱስ ጊዮርጊስን መሰረቱ፡፡ አየለ አትናሽና ጆርጅ ዱካስ ደግሞ አስተባባሪዎች ነበሩ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ትልቅ ስም ያላቸው ይድነቃቸው ተሰማ ክለቡ ከተመሰረተ ከሁለት ወር በኃላ እንደተቀላቀሉት የክለቡ መረጃ ያመለክታል፡፡ ጊዮርጊስ በተመሰረተበት አመት ጣሊያን ኢትዮጵያን በመውረሩ ለነፃነት መንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ በአምስቱ የጣልያን የወረራ ዘመናት “ቅ/ጊዮርጊስ” የሚለው ስያሜ በጣልያኖቹ ዘንድ ባለመወደዱ “ሊቶርዮ ውቤ ሰፈር አራዳ” በሚል ስያሜ እንዲጠራ ተደርጎ ነበር በወቅቱ በነበረው የወራሪዎቹ የዘረኝነት አስተሳሰብ ጥቁሮች ከነጮች ጋር እንዳይጫወቱ ይደረግ ስለነበር ቅ/ጊዮርጊስ ከሌሎች የኢትዮጵያውያን ቡድኖች ጋር እንጂ ከውጭ ሃይሎች ጋር አይጫወትም ነበር፡፡ በወቅቱ ከጊዮርጊስ በተጨማሪ የቀበና፣ የጉለሌ፣ የስድስት ኪሎና እንጦጦ በመባል የሚታወቁ የኢትዮጵያውያን ቡድኖች ነበሩ፡፡ ጊዮርጊስ ከነዚህ ቡድኖች ጋር ጨዋታውን ሲያደርግ ሲመሰረት የነበረውን የነጭና ቡናማ ማልያ በመተው ሰማያዊ ማልያ በመልበስ አምስቱን የወራራ ዘመን አሳልፏል፡፡ ለበለጠ መረጃ: http://www.ethiofootball.com/team/profile.php?teamid=20 ይመልከቱ።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ኢትዮጵያ ቡና የተመሰረተው በ1975 ዓ/ም በቡና ቦርድ ስረ ነበር።ስያሜውም ቡና ገበያ ስፖርት ክለብ የሚል ነበር። በቀጣይነት የቡና ላኪዎች ማህበር ከምርት ገበያ ጋር በመሆን በጀት እየመደቡለት በቦርድ በመመራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የኢትዮጵያ ቡና ክለብ የሚከተሉትን ክብሮች አግኝቷል:- ፩ - የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፕዮን : አንድ ጊዜ በ፳፻፫ ዓ.ም። ፪ - የኢትዮጵያ ሻምፒዮና: አንድ ጊዜ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም። ፫ - የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና: ሶስት ጊዜ በ፲፱፻፹፱፣ ፲፱፻፺፪፣ እና በ፳፻ ዓ.ም። ፬ - የኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ: ሶስት ጊዜ በ፲፱፻፹፱፣፲፱፻፺፪፣ እና በ፳፻ ዓ.ም። ለበለጠ መረጃ: http://www.ethiofootball.com/ ይመልከቱ።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ሕብረ ቃል: ከጥላቸው እንድትርቅ። ሰም: ወንድሜ፣ ሕመምህ እንዳያገረሽብህ ከሰው ጥላ ራቅ! ወርቅ: ከነዚሕ ሰዎች ፀብ (ጥል) ራቅ፤ እራስሕን አታነካካ።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  (ስም): በቤተ ክርስቲያን ትምህርት የገፋ እና ቅስናውን ያፈረሰ ሰው። አንዳንድ ጊዜ ይህን እውቀቱን በጎ ላልሆነ ነገር ስለሚጠቀምበት ደብተራ የሚለው ስም ከመተት እና ከአስማት ጋር ይያያዛል።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ቡራቡሬ፣ዝንጉርጉር፣ድብልቅ፣ቅይጥ፤ ማለት ነው።
 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Comments (13)


 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  እናመሰግናለን መስፍን! በጥይት መገበያየት እንደውም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እንደነበረ እዚሁ ሰዋስው ላይ ዓጼ ምኒልክ ይህንን አስመልክተው ያወጡትን አዋጅ አንብቤያለሁ። የመጀመሪያዎቹ ሁሉት ግን ራቅ ያለ ዘመን ላይ የነበሩ ሳይሆኑ አይቀሩም።
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  አንድ የጓደኛችን ሰርግ ላይ ፉከራ ሲፎከር አይቼ ተመችቶኝ ነበር :) በደህናው ቀን ዝምተኛ የነበሩት ወንዶች ሁሉ እሳት ጎርሰው እሳት ልሰው ሳያቸው ተገርሜ፣ ተገርሜ :)
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የሆነ ወቅት ላይ ይህንን መፅሃፍ በከፊል ለማንበብ ችዬ ነበር። ራስ ካሳ በጊዜያቸው ከነበረው አስተሳሰብ ትንሽ ወጣ የማለት ዝንባሌ ነበራቸው  ለማለት ያስደፍረኛል። ምን ያህሉን ፍልስፍናቸውን በራሳቸው ህይወት ላይ ኖረውታል የሚለውን ባላውቅም።
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  Great poem by Dr. Bedilu! Thanks for bringing it to sewasew, እሸቱ! I also like the explanation by Hon. Dr. Kebede Michael!
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  እናመሰግናለን መስፍን! በገመድ የሚሻገሩት ሰዎች ግን ጉደኞች ናቸው :) ሌላ መሻገሪያ የለም እንዴ?
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  እናመሰግናለን ቶላ! ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ሌሎች በርካታ ፅሁፎችም አሏቸው፤ እነዚህን ፅሁፎች በሌላ መጣጥፍ ይዘህ እንደምትመጣ ተስፋ አደርጋለሁ!
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ለ፳፻፮ ዓ/ም በጎ ሰው ሽልማት ዝርዝር ደግሞ ይህንን የሰዋስው መጣጥፍ መመልከት ይቻላል።
  http://www.sewasew.com/phrases/1344?withDetails=1
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቇንቇዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ባሳተመው የመዝገበ ቃላት መፅሐፍ ላይ እንዲህ በሚል ተተርጉሟል።

  ደብተራ ማለት ሁለት ትርጉም ሲኖረው አንደኛው የዜማ፣ ያቇቇም፣ የቅኔ ምሁር ማለት ሲሆን፤ ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ መፃፍ ገላጭ፣ ኮከብ ቆጣሪ በማለት ይፈታዋል።
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ለምሳሌ: የከበቡሽ ልጅ እንደው መስታወቱን አታምነውም! መልኬ ጠፋኝ ነች :)
 • Load more...
loader Loading content ...