loader

Topics (13)


loader Loading content ...

Explanations (13)


 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ድንቅነሽ (ሉሲ) 3.2 ሚሊዮን ዓመት ያላት የመጀመሪያዋ የሰው ቅሪት አካል ስትሆን በአፋር ውስጥ ሃዳር የተባለ ቦታ ኅዳር 24 ቀን 1974 ዓ.. Donald Johanson, Marice Taieb, Yves Coppens and Tom Gray ተገኘች::


  ሉሲም የተባለችው በዛን ወቅት ተመራማሪዎቹ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ድንቅነሽ ያልናትን የሰው ልጅ ቅሬተ አካል ሲያገኙ በወቅቱ ታወቂ የነበረውን የቢትልስ ሉሲ ኢን ዘ ስካይ ዊዝ ዲያመንድስ የተባለውን ዘፈን እያዳመጡ ነበርና ያገኙትን ቅሬተ አካል ሉሲ ብለው በመሰየም ለዓለም አስተዋወቁ።
  የሉሲ ቅሪተ አካል የሚያሳየው በግዜው ቆማ ትሄድ እንደነበረ ነው።

  ትክክለኛው ቅሪተ አካል በብሔራዊ ሙዚየም ፖሊዎ አንትሮፖሎጂ ላብራቶሪ ይገኛል፡፡

  ምንጭ:- ሪፖርተር ጋዜጣ ህዳር / 2006 እትም 
 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::

  ዕለት፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና  አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ  እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::

  ወር፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::

  ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::

  የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀን 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና  5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::

  የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ  ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::

  ምንጭመስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  የእሬቻ ክብረ በዓል በኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ በዓል ዋነኛው ሲሆን የሚከበረውም በጸደይ በሚጀምርበት ወቅት፤ ከጨለማ ክረምት እና ጎርፍ በሰላም ማለፍ ምክንያት በማድረግ እንደ ምስጋና ነው::  እሬቻ ማለት ለተከበረ ነገር የሚከፈል ዋጋ ማለት ሲሆን ሳር ደግሞ በኦሮሞ ባህል እርጥበቱ ህይወትን የሚያሳይ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው ነገር ነው::

  በዓሉም ወደ መልካ(መልካ ማለት አንድን ወንዝ ጥልቅ ያልሆነ እና አደገኛ እንስሳት የማይገኝበት በቀላሉ ሊሻገሩ የሚችሉት ቦታ) እርጥብ ሳር ይዘው “ማሬ_ሆ” የሚባል ዜማ እያዜሙ ይጓዛሉ፤ እንደደረሱም ያካባቢው የዕድሜ ባለጸጋ ታላቅ የሆነ ሰው ለምርቃት ይጋበዛል:: 

  በድሮ ጊዜ የሚከበርበት ቀን የሚወሰነው አያንቱ በሚባሉ ባህላዊ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ ቀን እና ለሊቱ እኩል የሚሆንበት ቀን ላይ ነበር:: ባሁሉ ወቅት ግን በዘመናዊ ቀን አቆጣጠር በየአመቱ ከመስከረም 19 እስከ 24 ባለው ጊዜ በሚውለው እሁድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ቢሾፍቱ በመሄድ ያከብራሉ::

  ምንጭ:- ከአያንቱ ዜና መስከረም 24/2014

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ምኒልክ ... 1993 .. በአዲስ አበባ ተወለዱ:: ትምህርታቸውን በሐረር የተከታተሉ ሲሆን ለ5 ዓመታትም የፈረንሳይኛ ትምህርት ተምረዋል:: ለመጀመሪያ ጊዜ በቲያትር ቤት በድምጻዊነት የተቀጠሩት ምኒልክ በአጭር ጊዜ እውቅናን አትርፈው የኢትዮጵያ ባህል ሙዚቃን ለማስተዋወቅ ብዙ አገራትን በመዘዋወር የበኩላቸውን አስተዋጽዎ አድርገዋል::

  ምኒልክ ከአማርኛ ዘፈኖቻቸው በተጨማሪ የኦፔራ እና በሱዳንኛም ዜማዎችንም ይጫወቱ ነበር:: ምኒልክ የ“ራስ ባንድ” የሙዚቃ ቡድን አባል የነበሩ ሲሆን ታዋቂነትን ካተረፉባቸው ስራዎቻቸው መካከል፦”ትዝታ  አያረጅም”፣ “ጋሽ ጀምበኤ”፣ “ፍቅር ባስተርጓሚ”፣ “አደረች አራዳ” እና “እትት በረደኝ” ተጠቃሽ ናቸው::

  ድምፃዊ ምኒልክ የአራት ልጆች አባት ሲሆ ትም ለ22 ዓመታት በሱዳን እና አሜሪካ ሃገራት ቆይታ በኋላ ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ባደረባቸው ህመም 2001 .. በሞት ተለይተዋል::

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ሀብተጊዮርጊስ እ... በ1844 ዓ.. ከአባታቸው አቶ ዲነግዴ በተራና ከእናታቸው ከእመት ኢጁ ተወለዱ:: በተለያየ ጸሃፍት ሀብተጊዮርጊስ የጉራጌ ወይም የኦሮሞ ወይም ደግሞ የሁለቱ ቅልቅል እንደሆኑ ተጽፏል:: በ1859 ዓ.. የምዕራብ ሸዋን ግብር ለማስከፈል በተደረገው ጦርነት ሀብተጊዮርጊስ አቶ አይተንፍሱ በተባሉ ዘማች ተማርከው ነበር:: ከዛም አጼ ምኒልክ ባወጡት አዋጅ መሰረት አቶ አይተንፍሱ  ሀብተጊዮርጊስን ለምኒልክ  አስረከቡ::

  ሀብተጊዮርጊስ ንጉስ ምኒልክ እና  ንጉስ ተክለሃይማኖት እምባቦ (ወለጋ) ላይ ባደረጉት ጦርነት ዘምተው ትልቅ ጀግንነት በማሳየታቸው ከአጼ ምኒልክ ጋር ያላቸው መቀራረብ ጨመረ:: ከዛም በመቀጠል በ1889 .. በአድዋ ጦርነት ፊታውራሪ ገበየሁ በተሰው ጊዜ እሳቸውን በመተካት ሀብተጊዮርጊስ የጦር አበጋዝ ሆነው በሚያገለግሉበት ጊዜ  አጼ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ የፊታውራሪነት ማዕረግ ሰጣቸው:: ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስም ባላቸው የጦር አመራር ብቃት “አባ መላ” የሚል ቅጽል ስም አትርፎላቸዋል:: ታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ይህንን የሚያመላክት ውዳሴ “ምኒልክ” በተሰኘው የሙዚቃ ስራው ላው አሳይቷል::

  በ1900 ዓ.. አጼ ምኒልክ ከአውሮፓ ባገኙት ልምድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲያቋቁሙ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስን የደቡብ ኢትዮጵያ አስተዳዳሪ አድርገዋቸዋል::   ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ለረጅም ጊዜ ታመው በ1919 ዓ.. ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል::

     ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ - ሰብ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ኮንሶ  ከአዲስ አበባ ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል በ595 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ባጠቃላይ 9 ጎሳዎችን ይዛለች:: በብዛት “አፋኾንሶ” የተባለ ቋንቋ የሚናገሩት ኮንሶዎች አስቸጋሪ የሆነውን መልከአ ምድር በባህላዊ እርከን አፈሩን ከመሸርሸር ጠብቀው ሰፊ በሆነ ግብርና የሚተዳደር ማህበረሰብ ነው::

  የኮንሶ ታታሪው ማህበረሰብ ድንጋያማ፣ ደረቅ፣ ተራራማ እና ወጣ ገባ የሆነውን መሬት በባህላዊ መንገድ እርከን እየሰሩ እና እያረሱ አፈሩ እንዳይሸረሸር በማድረግ ውጤታማ በመሆናቸው "Konso Cultural Landscape" በሚል በዩኔስኮ በ2011 ተመዝግቦ ይገኛል::

  የኮ ህዝብ የሞራ የሚባል 3 የማህበረሰቡ መሰብሰቢያ አደባባዮች አሉአው:: አንደኛው ከስራ በኋላ በዚህ አደባባይ ተሰባስበው ገበጣ የሚባለውን ጨዋታ እየተጫወቱ ጨቃ የተባለውን ባህላዊ መጠጥ እየጠጡ የሚዝናኑበት ነው:: ሁለተኛው የእምነት አገልግሎት የሚካሄድበት እና የተጣሉ ሰዎች ለመተማመየሚማማሉበት ነው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ትልቅ የዓመት በዓል የሚከበርበት ነው::

  በኮ ትልቅ ስራ ወይም ታሪክ ሰርቶ ላለፈ ሰው ሶስት ረጃጅም ድንጋይ የሚተከልላቸው ሲሆን እነዚህም ሰዎች ዋካዎች በመባል ይታወቃሉ:: በሌላ በኩል የኮንሶ ህዝብ ከትውልድ ትውልድ ስልጣን ሲረካከብ ኦላሂታ የሚባል የትውልድ ማስታወሻ የእንጨት ፖል ይተክላሉ::

     ምንጭ:- አዲስ አድማስ፣ ዩኔስኮ ድረ-ገፅ ፣ ውክፒድያ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  በአሉ ... 1939 .. በኢሊባቡር ክፍለ ሃገር ሱጴ ቦሩ በሚባል ስፍራ ተወለዱ:: እናታቸው የዚያው አካባቢ ተወላጅ ሲሆኑ አባታቸው ግን ሕንዳዊ እንደሆኑ ይነገራል:: የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ እና በዊንጌት ተምተው ከዛም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስ እና ጋዜጠኝነት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል:: በመቀጠልም ከሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፖለቲካል ሳይንስ እና ጋዜጠኝነት ተመርቀዋል::

  በአሉ በጋዜጠኝነት ሙያቸው በተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ሲሆን ለመጥቀስ ያህል፦ “መነን መጽሄት”፣ “አዲስ ሪፖርተር”፣ “የዛሬይቱ ኢትዮጵያ”፣ “ኢትዮጵያ ሄራልድ” እንዲሁም በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተሹመው አገልግለዋል::

  ደራሲ በአሉ በስነጽሑፍም ከአድማስ ባሻገር፣ የቀይ ኮከብ ጥሪ፣ ደራሲው፣ ሀዲስ፣ የህሊና ደውል እና ኦሮማይ ስራዎች አበርክተዋል:: ከአድማስ ባሻገር የተባለው ስራቸው በሩስያኛ ቋንቋ ተተርጉሟል:: ኦሮማይ ደግሞ ደራሲው ታዋቂነት ያተረፈበት ታላቅ ስራ ሲሆን በወቅቱ በነበረው ስርአት ግን ተቀባይነትን ባለመግኘቱ በአሉ ከስራ  እስከመባረር ብሎም ... 1984 .. ዱካቸው እንደጠፋ ከዛም እስካሁን ይኑሩ ይሙቱ የሚታወቅ ነገር ያለም::

  ደራሲ በአሉ ከባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ አበራ 3 ልጆችን አፍርተዋል::

                      ምንጭ:- ውክፔዲያ እና ታሪካዊ መዝገበ ሰብ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  በ1978 በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሚገኘው በአማራ ክልል ሰሜን ጎደር ዞን ከደባርቅ ከተማ 32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከ1900-3926 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡

  ይህ ተፈጥሯዊ ፓርክ ከዘመናት ብዛት በዝናብ እየተሸረሸረ የተለያየ የሾለ ጫፍ እና ጥልቅ የሆነ ሸለቆ በመኖሩ ድንቅ የሆነ ውበት እና መስህብ ተላብሷል:: በተጨማሪም ብርቅዬ እንስሳቶች እንደ ዋልያ፣ የሰሜን ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮ እና የተለያዩ አዋፋት መሰባሰቢያም ነው:: በመሆኑም የሚጎበኘው የቱሪስት ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በመጨመር ላይ ነው::


              ጭላዳ ዝንጀሮ

    ምንጭ:- አጋር ሎጅ ድረ ገጽ እና የዩኔስኮ (unesco) ድረ ገጽ
 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ዕቁብ ማለት ሰዎች የገንዘብ እጥረት በሚያጋጥማቸው ጊዜ ለማሰባሰብ የሚጠቀሙበት ማህበራዊ መረዳጃ ነው:: በኢትዮጵያ ብድር ከተቋማት የማግኘት አገልግሎት ባብዛኛው የሌለ በመሆኑ ህብረተሰቡ ዕቁብን በመጠቀም ችግሮቹን በመፍታት ይታወቃል:: በመሆኑም “ሰውን ሰው ያደረገው ዕቁብ ነው” የሚል አባባል የተለመደ ነው::

  ዕቁብ የአባላቱ ብዛት፣ ገንዘቡ የሚሰበሰብበት ርቀት(በቀን፣ በሳምንት ወይም በወር) እና የሚያልቅበት ጊዜ የሚወሰነው ገንዘቡን ለማሰባሰብ በጀመረው ሰው ወይም በዕቁብ መስራች ሲሆን በዛ መሰረት አባላት ማሰባሰብም ይጀመራል::

  ብዙውን ጊዜ  ገንዘቡን ፈልጎ ያሰባሰበው የመጀመሪያውን ዙር የተሰበሰበ ገንዘብ የሚወስድ ሲሆን የሚቀጥሉትን ተራዎች በዕጣ ይደለደላል:: ዕቁብ በተለምዶ የሚከናወነው በመተዋወቅ እና በመተማመን ሲሆን ትልልቅ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ዕቁብ ግን ህጋዊ በሆነ መልኩ ሰብሳቢ፣ ጸሐፊ እና ጠበቃ ሳይቀር በክፍያ የሚያስተዳድሩት አካላት ይኖሩታል:: ባለዕጣም በደረሰው ጊዜ ተያዝ ማምጣት የግድ ነው:: 

                            ምንጭ:- በዘመኔ ካየሁት ተነስቼ የፃፍኩት

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ሚጥሚጣውን አግሩን ቀንጥሶ በደንብ አርገው ከለቀሙ በኋላ ኮረሪማ፣ ጨውና ጦስኝ በርከት አድርጎ ጨምሮ ጸሃይ ላይ ማስጣት::


  ሲደርቅ አልሞ አስፈጭቶ ክዳን ባለው እቃ ማስቀመጥና ለተለያየ ምግብ ማባያነት መጠቀም ይቻላል::


 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.