loader
 • ምሳሌያዊ አባባሎች ምንድን ናቸው?

  @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደመስቀል ስለ ምሳሌያዊ ንግግሮች ጠቀሜታ የሚከተለውን ይላሉ --

  "... ምሳሌዎች አንዳንድ ጊዜም ተረቶች የምንላቸው በልዩ ልዩ ሁናቴ የሀገራችንን ጠቅላላ መልክ የሚያሳዩ ናቸው፤ እነዚህም በሕዝብ እጅ ገብተው በዘመን ብዛት መልካቸው ቢለወጥም ከተመራማሪዎች፤ ከአርቆ ተመልካቾች፤ ከአስተዋዮች፣ በእውቀት ከበሰሉ ሰዎች የተገኙ መሆናቸው የማያጠራጥር ነው።  በተለይም በህሊና ርትዕን መሰረት በማድረግ የሚነገሩት ምሳሌዎች ምን ያህል የማስረዳት ኃይለ ቃል እንዳላቸው መገንዘብ አስቸጋሪ አይደለም፤ እነዚህም ከአባት ለልጅ እየተላለፉ ለእኛ የደረሱን ምሳሌዎች በአለፈው ጊዜ የሕግ አንቀፆች ሆነው በየአደባባዩ ሲሰራባቸው ቆይተዋል።"

  ይሉና የሚከተሉትን በሕግ ረገድ ሲጠቀሱ የነበሩ ምሳሌያዊ ንግግሮችን ያስረዳሉ :-

  • ሞኝ ወርውረው ቢስቱት ያልወጉት ይመስለዋል።
  ማስተዋል እና ማመዛዘን ያነሰው ሰው ባይመታም፤ ባይረታም፤ በአቅም ማነስ ወይም በልዩ ምክንያት ቢሳትም ድርጊቱ እንዳልተፈፀመ ያህል ይቆጥረዋል። እንደእውነቱ "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ" የተባለውን ምሳሌ መዘንጋት አይገባም።

  • ዋስ ካለው ዱቄትህን ለንፋስ አበድረው።
  ብድር ጠያቂው ያልታመነ ወይም ንብረቱ ዝቅተኛ ቢሆንም ዋሱ አጥጋቢ ከሆነ በሱ አማካኝነት ብድሩ ይሰጠው ማለት ነው።

  • ከአፍ የወጣ ቃል ከእጅ የወደቀ እንቁላል።
  ከእጅ የወደቀ እንቁላል መፍረጡ፣ መፍረሱና መሰበሩ እንደማይጠረጠር ሁሉ ከአፍ የወጣውን ቃልም እሰው ጆሮ ስለሚደርስ ማስቀረት አልመቻሉን ስለመግለፅ።

  • አሳ ጎርጉዋሪ ዘንዶ ያወጣል፤ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል።
  አሳ በመቃጥን እና በመረብ ሲያዝ አልጠግብ ባይ በእጅ ለመያዝ አለቱን በመፈንቀል ዘንዶ እንዲያወጣ፤ ሰርተው ያላገኙትን የሰው ሀብት አንጋጦ መመኘትም የራስን እስከማጣት ያደርሳል።

  • ሳይበሉ ማግሳት፣ ልክበር ብሎ መጏጏት።
  ሳይበሉ ማግሳት እንደማይቻል ሁሉ፣ ሳይሰሩ ለመክበር መመኘትም በሃሳብ ውቅያኖስ ተውጦ እንደመቅረት ያለ ነው።

  • ሳይተርፋት አበደረች፣ ሳትቀበል ሞተች።
  ለብልጭልጭ እና ለከንቱ ነገር እንዲሁም ለይወቁልኝ የሚሰራ ራሱን እንኯ እንደማይጠቅም፤ ለውዳሴ ከንቱ ያበደረችም ሳትቀበለው ሞተች።

  • የወጋ ቢረሳ፣ የተወጋ አይረሳ።
  ሞት ቢዘገይም እንደማይቀር ሁሉ በደል ቢቆይም አይረሳም፤ በነገር የወጋው ቢዘነጋ እንኯ የተበደለው ሲቆረቁረው ይኖራል፤ ቁስሉ ቢሽርም መዳው አይጠፋም።

  • አመልና ቀንድ በስተሇላ ይበቅላል።
  የእንስሳት ቀንድ ቆይቶ እንደሚወጣ ሁሉ፤ ሰውም በጊዜ ብዛት የሚያስከትለው ነገር ስለማይታወቅ ፍፃሜውን ሳታይ በመጀመሪያ አትውደደው፣ አታመስግነው።

  • እወቁኝ ብሎ ደብቁኝ።
  ወረተኛ ሰው በመጀመሪያ አለሁ አለሁ በማለት ባለሟል ወይም ዘመድ የምስልና በሕዋላ የአገዳ መብራት ሲሆን ይታያል። እንዲሁም በሰላም ጊዜ ፎካርና ባለጉራ ሆኖ ጦርነት ሲመጣ ለሚርበደበድ እና በነገር ሰው ሲያጠቃ ቆይቶ በተገለጠበት ጊዜ እንዳልሰማ ለመሆን ለሚጣጣር ወስላታ ሊጠቀስ ይችላል።

  • ጥንቱን ባልዘፈንሽ፣ ከዘንፈንሽም ባላሳፈርሽ።
  ቀድሞውኑ አለመጀመር፣ አቅምን ማወቅ፣ በጉዳዩ አለመግባት ደግ ነው፤ ከጀመሩ ግን በነገሩ፤ በሁኔታው መዝለቅ ይገባል።

  • ወስፌ ሲለግም ቅቤ አይወጋም።
  ሰው ያለፍቃዱ ቢሰራ ፈር አያወጣም፤ የሚያውቀውን እንክዋን አላውቅም ሊል ይችላል፤ ጉዳዩንም ከፍፃሜ አያደርስም።

  • እንባ ሲሻኝ፣ ጢስ ወጋኝ።
  ስፈልገው ተወሳልኝ፤ ስመኘው ሳለ ሆነልኝ ወይም እንደፍላጎቴ ታዘዝሁ።

  ምንጭ:
  የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ስብስብ ስራዎች
 • loader Loading content ...
 • @Demoze   1 year ago
  Sewasewer
  እናመሰግናለን ቶላ! ይገርምሃል፣ አሁን ላለው ትውልድ የምሳሌያዊ አነጋገሮችን ፋይዳ ማስረዳት በጣም ከባድ ነው :) እንደዚህ አይነት ፅሁፎች ነገሮችን ያቀላሉ ብዬ አስባለሁ!
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን ቶላ!
 • @Alembrehan   1 year ago
  Sewasewer
  Thanks Tola for sharing, I have checked other posts by you and they are amazing! please keep it up!
 • @Moti   1 year ago
  Sewasewer
  Thank you Tola!
 • @Meklit   1 year ago
  Sewasewer
  I love it! Thanks Tola!

Load more...