loader
 • አብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ (Abijatta Shalla National Park)

  @ሰላም   2 years ago
  Live a life you are proud of.
 • loader Loading content ...
 • @ሰላም   2 years ago
  Live a life you are proud of.

  አብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ ከአዲስ አበባ በ210 ኪ.ሜ ያህል ርቀት ላይ ከላንጋኖ ደግሞ በስተቀኝ 5 ኪ.ሜ ገባ ብሎ በኦሮሚያ ክልል ይገኛል፡፡ የተመሰረተው እኤአ 1974 ዓም ሲሆን 887 ስኩየር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት አለው፡፡ ይህ ፓርክ ከባህር ጠለል በላይ ከ1540-2007 ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ በብዛት እንደዣንጥላ የሚዘረጉ የግራር ዛፎች ይገኙበታል፡፡

  በብዝሀ ህይወት ስብጥሩ እና በስፋቱ የበለጸገ የቱሪዝም መስህብ የሆነው ይህ ፓርክ በርካታ የውሀ ላይ አእዋፍ የሚታዩበት፤ በተለይ በክረምት ወቅት ወደ 50,000 የሚጠጉ የፍላሚንጎዎች ተከማችተው ለዓይን በሚስብ መልኩ የሚታዩበት ነው፡፡ ወፎችን ለሚያደንቁ ጎብኝዎች ተመራጭ ስፍራ የሆነው ይህ ፓርክ በአፍሪካም ግንባር ቀደም እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ ሰጎንም በዚህ ፓርክ ከሚገኝ አእዋፍ አንዱ ነው፡፡

  ይህ ፓርክ ልዩ ልዩ አጥቢ የዱር እንስሳት የአእዋፍ እና የእፅዋት ዝርያዎችን ይዟል፡፡ በፓርኩ ውስጥ የሜዳ ፍየልን፣ ከርከሮና አጋዘን የመሳሰሉት የዱር እንስሳትን ሁሉ ይገኙበታል፡፡
                ምንጭ:- ሀገራችንን እንወቅ

 • loader Loading content ...

Load more...