
-
@አማን 2 years agoStop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.
-
@አማን 2 years agoStop waiting for the perfect moment. Take the moment you've and make it perfect.
አትሌት መሰረት ሃምሌ 12 ቀን 1975 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ ተወለደች:: የችግረኛ ልጅ የነበረችው መሰረት ከልጅነቷ ጀምሮ የተለያዩ የቀን ስራዎችን እየሰራች ቤተሰቦቿን እየደጎመች ያደገች ቢሆንም ትምህርቷንም ጎን ለጎን ታስኬደው ነበር:: ወደሩጫው ያዘነበለችው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ሲሆን በወቅቱ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት ይዘጋጁ በነበሩ በርካታ ውድድሮች በማሸነፉዋ እ.ኤ.አ. 1998 ዓ.ም. በባንኮች አትሌቲክስ ቡድን ልትታቀፍ ቻለች:: በባንክ ቡድን ውስጥ እያለች በተደረጉ በርካታ የሃገር ውስጥ ውድድር ባሳየችው ያሸናፊነት ድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እንድትመረጥ አስችሏታል:: ለመጀመሪያም ጊዜ 1999 ዓ.ም. በፖላንድ የ3ሺ ሜትር ዓለም አቀፍ ውድድር አድርጋ ሁለተኛ ወታለች::
መሰረት ያሻሻለቻቸው የአለም ክብረ ወሰኖች፣ 2006 ኒውዮርክ ላይ በተካሄደው የ5ሺ ሜትር፣ 2007 ጀርመን ላይ በተካሄደው የ3ሺ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር፣ 2007 ካሊፎርኒያ ላይ በተካሄደው የ2 ማይል፣ 2007 ቤልጂየም ላይ በተመሳሳይ የ2 ማይል በራሷ ተይዞ የነበረውን ሰዓት በማሻሻል ይጠቀሳሉ:: በዚም ውጤትዋ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን “የ2007 ምርጥ አትሌት” የሚባለውን የሽልማት ዘርፍ አጎናጽፉአታል::
መሰረት ምንም እንኳን በቂ ውጤት እና ድሎች ቢኖራትም በኦሎምፒክ ውድድሮች አገሯን ወክላ ለመሮጥ ብዙ ፈተናዎችን በትግስት ተቋቁማ ለመጀመሪያ ጊዜ በአቴንስ ኦሎምፒክ ለ5ሺ ሜትር ውድድር በተጠባባቂነት ዕድሉን ስታገኝ በአስደናቂ ብቃት በአንደኛነት መፈጸም የቻለችና ብቃቷን ያስመሰከረች ጀግና ነች:: ይህንኑ ብቃቷን በ2012 ለንደን ኦሎምፒክ ደግማዋለች::
በግል ህይወቷም የባንክ ክለብ እግር ኳስ ተጫዋች ከነበረው ቴዎድሮስ ሃይሉ ጋር ትዳር መስርታ የመጀመሪያ ሴት ልጃቸውን አግኝተዋል::


Similar topics
በላይ ዘለቀ ማን ነው? ጀግና ያሠኙት ሥራዎቹ ምንድን ናቸው?
ወታደራዊ ደርግ አጼ ኃይለስላሴን ከስልጣን ሲያውርድ ያከናወናቸው መርሃ ግብሮች ምን ይመስሉ ነበር?
አቡነ ጴጥሮስ በኢጣልያኖች በአደባባይ ሲገደሉ ሂደቱ እና በዕለቱ የታዩት ክስተቶች ምን ይመስሉ ነበር?
የአፄ ቴዎድሮሥ ወደ ሥልጣን አመጣጥ ምን ይመሥል ነበር?

Popular topics
ወታደራዊ ደርግ አጼ ኃይለስላሴን ከስልጣን ሲያውርድ ያከናወናቸው መርሃ ግብሮች ምን ይመስሉ ነበር?
ለተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤት መቋቋሚያ እርዳታ የሰጡ ሰዎች የስማቸው መታሰቢያ።
በኢትዮጵያ እና የእንግሊዝ ሱማሌ-ላንድ ድንበር ማካለል ኮሚሽን ውስጥ ሁለቱን አገራት የወከሉት ዋና ዋና ግ...
Meskea-hazunan Medhane Alem(Sidetegnaw) Church in Addis Ababa
ጀመዶ ማርያም ገዳም (Jemedo Mariam Monastry) - የዋሻ ውስጥ ገዳም
ሽፈራው ወይም ሽፈሬ ተክል (Moringa Oleifera)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የፓትርያርክ ስልጣኗን ለማግኘት ከግብፅ ቤተክርስትያን ጋር ያረ...
አቡነ ጴጥሮስ በኢጣልያኖች በአደባባይ ሲገደሉ ሂደቱ እና በዕለቱ የታዩት ክስተቶች ምን ይመስሉ ነበር?