loader
 • ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው።

  @አቦቸር   2 years ago
  መሳቅ፣ መሳቅ፣ አሁንም መሳቅ!
 • loader Loading content ...
 • @አቦቸር   2 years ago
  መሳቅ፣ መሳቅ፣ አሁንም መሳቅ!
  አቶ ተገኘ የሚባሉ አንድ ሰው ነበሩ። አንድ ቀን ስራ በዝቶባቸው እቤታቸው ውለው ኖሮ አሽከራቸውን ጠርተው ዛሬ ብርቱ ስራ ይዣለሁና ማንም ሰው መጥቶ ቢጠይቅህ የለም ወደውጭ ወጥቷል ብለህ መልሰው አሉና አዘዙት። አሽከርየውም እንደታዘዘው አድርጎ ብዙ ሰው ሢመጣ የሉም እያለ መለሰ። አንድ ሰው በሇላ መጥቶ አቶ ተገኘ በቤታቸው ውስጥ ካንዱ ወደ አንደኛው ክፍል ሲተላለፉ በመስኮት አይቷቸው ኖሮ አሽከሩን ንገርልኝ አለው። አሽከር ግን እንደ ልማዱ የሉም ወደ ውጪ ወጥተዋል ብሎ መለሰ። እንግዳው ኝ አሁን ባይኔ አይቻቸዋለሁና ታልነገርክልኝ አይሆንም ብሎ አስቸገረው። አሽከር ወደ ቤት ገብቶ ላቶ ተገኝ ይህንኑ ነገራቸው፤ እሳቸውም ተቆጥጠው በሩን ከፍተው ወጡና እንግዳው ወዳጄ ምን ትፈልጋለህ አሉት። እርስዎን ነው ቢላቸው፣ እኔን ከሆነ የለሁም ወደ ውጪ ወጥቻለሁ ብለው በሩን በኃይል ወርውረው ዘግተው እቤታቸው ተመልሰው ገቡ።

  ምንጭ:
  • ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)

 • loader Loading content ...

Load more...