loader
 • ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለ58 ዓመት በስፖርት ዓለም

  @ምስጋና   2 years ago
  You have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
 • loader Loading content ...
 • @ምስጋና   2 years ago
  You have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.

  ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ  ከአባታቸው ከታዋቂው የሙዚቃ ሰው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መካኒክ፣ ሾፌር እና የስነ ጽሁፍ ሰው ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ እና ከእናታቸው ከወ/ ሙላቷ ገብረስላሴ በጅማ ከተማ መስከረም 1 ቀን 1914 .ተወለዱ፡፡

  አባታቸው ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በልጅ እያሱ ጊዜ የቴሌግራም እና የፖስታ ሚኒስቴር ሆነው በማገልገላቸው አፄ ሀይለስላሴ ስልጣን ሲይዙ በግዞት ወደ ጅማ በላኳቸው ጊዜ ነበር ይድነቃቸው እዛው የተወለዱት፡፡

  ይድነቃቸው ተሰማ እንደጊዜው ልጆች ሁሉ በቤት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እና የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን የተከታተሉ ሲሆን የፈረንሳይኛን ቋንቋንም በአሊያንስ፣ በምኒሊክ እና በተፈሪ መኮንን /ቤቶች ተምረዋል፡፡ 1928 . ወደ ፈረንሳይ አገር ለመሄድ ከተመረጡት ሁለት ጎበዝ ተማሪዎች መሀከል አንዱ በመሆን ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ቢሆንም አገራችን በጣሊያን በመወረሯ ምክንያት ጉዞአቸው አልተሳካም፡፡ በጠላት ወረራ ዘመንም በጊዜው ለኢትዮጵያውያን የሚፈቀደውን ትምህርት በጣሊያን /ቤት ተከታትለዋል፡፡ 8 ዓመት እድሜቸው የስፖርት ዓለም ተሳትፎን የጀመሩት ይድነቃቸው ተሰማ  14 ዓመታቸው ደግሞ የአራዳ ልጆች በመባል የሚታውቁ አቶ አየለ አትናሽ እና ጆርጅ ዱካስ የመሰረቱትን የዛሬውን ዝነኛ እና ባለታሪክ የዛኔውን የሰፈር ቡድን ተቀላቀሉ፡፡

  ይድነቃቸው ተሰማ 1936 . ከወ/ በዛብሽ ተክለማርያም ጋር ትዳር መስርተው እስከ እለተ ሞታቸው 43 ዓመት ያህል አብረው ኖረው 11 ልጆችን አፍርተዋል፡፡  በዚያው  አመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንንም እንደመሠረቱበሀገሪቱ የክለቦች ውድድር እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን በመመስረት ካፕቴን በመሆን ያገለገሉ ሲሆን 15 ጊዜ ያህል ተሰልፈው ተጫውተዋል፡፡

  ሁለገብ ስፖርተኞች የነበሩት ይድነቃቸው ተሰማ በአጭር ርቀት ሩጫ በቦክስ እና በብስክሌት ስፖርተኝነትም የታወቁ ነበሩ ከሁሉም በላይ ግን ታላቅ እግር ኳስ ተጫዋች የነበሩ ሲሆኑ ለክለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ የወድድር ዘመን 47 ጨዋታዎች 43 ጐሎችን በማስቆጠር እስከአሁንም ድረስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለሪከርድ ናቸው፡፡

  1940 . የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፀሐፊ በመሆነ የተመረጡ ሲሆን 1953 የኢትዮጵያ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

  1953 የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴን መስፈርቶች በሙሉ እንዲሟላ አድርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የመሠረቱ ሲሆን የኮሚቴው ፕሬዝዳንት በመሆን ከመስረታው እስከ 1973 . ድረስ አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም 1952 የሮም፣ 1956 የቶኪዮ፣ እና 1960 የሞስኮ ኦሎምፒኮች የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን መሪ ነበሩ፡፡

  በአለም አቀፍ የስፖርት ደረጃ ደግሞ ይድነቃቸው ተሰማ በተጨዋችነት፣ በቡድን መሪነት፣ የአሰልጣኝነት የኢትየጵያ ቡድን ይዘው 1940 . ጀምሮ በተለያዩ የአፍሪካ፣ አውሮፓ ሀገሮች የተዘዋወሩ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ወክለው በአለም አቀፍ የስፖርት ጉባዔ ላይ የተካፈሉት ግን 1949 . በሱዳን ካርቱም ከተማ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መስራች ጉባዔ ላይ ነበር፡፡

  ከዚህ ጉባዔ በኋላ በአደራጅ ኮሚቴነት፣ በምክትል ፕሬዝዳንትነት፣ እና በፕሬዝዳንትነት የአህጉሩን ኮንፌዴሬሽን 30 ዓመታታት በታላቅ ትጋት፣ ብልህነት እና ቆራጥነት አገልግለዋል፡፡

  ከዚህም በተጨማሪ ይድነቃቸው ተሰማ በሚከተሉት አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ በማገልገል ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው እና ለወገኖቻቸው አኩሪ ታሪክ ጽፈዋል፡፡

                   -  በአፍሪካ ብሔራዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በመስራችነት እና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት፣

                   -  በአፍሪካ የሰፖርት ኮንፌዴሬሽኖች ህብረት ውስጥ በመስራችነት እና በፕሬዝዳንትነት፣

                   -  በአፍሪካ የብሔራዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ውስጥ በመስራችና በክብር ፕሬዝዳንትነት

                   -  በአፍሪካ የስፖርት ሚኒስትሮች ካውንስል ውስጥ በቋሚ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት

                   -  በአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት

                   -  የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባልነት እና

                  -  የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ምሳሌነቱ አቻ የማይገኝለት አገልግሎት ስጥተዋል፡፡

          -----ምንጭ - ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፌዴሬሽን ድረ ታሪካዊ መዝገበ_ሰብ 2006 ዕትም
 • loader Loading content ...

Load more...