loader
 • የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አጠቃላይ መረጃ

  @Tariku   2 years ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @Tariku   2 years ago
  Sewasewer
  የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ5 አሰተዳደራዊ ዞኖች፣ በ129 ወረዳዎችን በ28 ከተማዎች የተዋቀረ ነው፡፡ የገጠሩ የክልሉ ክፍል 326 የገበሬ ማህበራት ሲኖሩት የከተማው ክፍል 32 ቀበሌዎች አሉት፡፡ የአፋር ክልል በአርኮሎጂካል ጥናት መሰረት የሰው ልጅ መገኛ ቦታ ሲሆን፣ በቅርቡም 4.4 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያለው ቅሪት አካል ተገኝቷል፡    • የስፍራው አቀማመጥ
   • የአፋር ክልል በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ይገኛል፡፡ በሰሜን ምስራቅ ከኤርትራ፣ በሰሜን - ምዕራብ ከትግራይ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ከአማራ ክልል፣ በደቡብ ከኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ - ምስራቅ ከሶማሌ ክልል  እንዲሁም በምስራቅ ከጂቡቲ ጋር ይዋሰናል፡፡

  • ሰንደቅ አላማ

   

  • ርእሰ ከተማ
   • ሰመራ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡


                  ሰመራ ከተማ

  • የቆዳ ስፋት
   • የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 270,000ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡

  • ስነ-ህዝብ
   • በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 1,106,383ሲሆን ከዚህም ውስጥ 626,839ወንዶች እና 479,544ሴቶች ናቸው፡፡ 1,020,504 (89.5 ከመቶ)የሚሆነው በገጠራማው የክልሉ ቦታዎች ይኖራል፡፡ በሀይማኖት ረገድም 96 ከመቶ የእስልምና፣ 3.86 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 0.43 ከመቶ የፕሮቴስታንት፣ 0.09 ከመቶ የካቶሊክ እንዲሁም ሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች 0፣02 ከመቶ የሌሎች እምነት ተከታዮች ናቸው፡
   • በብሄር ስብጥር አኳያም 91.8 ከመቶ የአፋር፣ 4.5 ከመቶ የአማራ፣ 0.92 ከመቶ የአርጎባ፣ 0.82 ከመቶ የትግራዊ፣ 0.8 ከመቶ የኦሮሞ፣ እንዲሁም 0.013 ከመቶ የሀዲያ ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡
   • የአፋርኛ ቋንቋ የክልሉ የስራ ቋንቋ ሲሆን 91.8 ከመቶ በክልሉ ይነገራል፣ አማርኛ 6.68 ከመቶ፣ ትግርኛ 0.74 ከመቶ፣ ኦሮምኛኛ 0.74 ከመቶ፣ አርጎብኛ 0.4 ከመቶ እንዲሁም ወላይትኛ 0.26 ከመቶ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎቸ ናቸው፡፡


                  የአፋር ልጃገረዶች

  • ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
   • በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትከሚገኘው ህዝብ 90 ከመቶየሚሆነው ህዝብ አርብቶ አደር ሲሆን፤ ግመሎችን፣ የቀንድ ከብቶችን፣ ፍየልና በግ እንዲሁም አህያዎችን ያረባል፡፡ በክልሉ በቆሎ፣ ባቄላ፣ ማሽላ፣ ፓፓዬ፣ ሙዝ እና ብርቱካን በስፋት ይመረታሉ፡፡ በጥጥ ምርትም ክልሉ ያታወቃል፡፡  የንግድ እንቅስቃሴ በተለይም የጨው ማውጣት ስራ በክልሉ በስፋት ይከናወናል፡፡  • የመሬት አቀማመጥ እና የአየር ንብረት
   • የአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ በስምጥ - ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ አብዛኛው የክልሉ ቦታዎች ጠፍጣፋ መሬት ነው፡፡ የክልሉ የከፍታ መጠን ከ160 ሜትር ከባህር ጠለል በታች (እስከ 50oc የሚደርስ በምድር ላይ ክተኛው የሙቀት መጠን የሚመዘገብበት) እስከ 1600 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ይደርሳል፡፡ የክልሉ ዝቅተኛ ቦታዎች ከባህር ጠለል በላይ ከ1600 ሜትር በታች ሲሆኑ እነደ ሙሳ-አሌ ተራራ ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ከባህር ጠለል በላይ 2063 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛሉ፡፡ 


   • የአፋር ክልል የሙቀት መጠን ከ25oc በዝናባማ ወቅት(ከመስከረም - መጋቢት) እሰከ 48oc በደረቃማ ወቅት(ከመጋቢት - መስከረም) ይደርሳል፡፡ ላለፉት 11 ዓመታት በዱብቲ ከተማ በሚገኘው የሜትሪዎሎጂ ጣቢያ የተመዘገበው የዝናብ መጠን 187.9 ሚ.ሜ ነበር፡፡

  • ወንዞችና ሀይቆች
   • የሚሌ እና የሎጊያ ወንዞች የሚገብሩለት የአዋሽ ወንዝ ክልሉን አቋርጦ ያልፋል፡፡ የአቢ ቢል፣ የአፋምቦ እና የአብዴል ሀይቆች የአዋሽ ወንዝ የሀገሪቱን አብዛኛው ቦታዎች አዳርሶ የሚያርፍበት መዳረሻዎች ናቸው፡፡ በውስጣቸውም የተለያዩ የብዝሀ ሕይወት ስብጥርን የያዙ ናቸው፡፡

  • ማዕድን
   • በአፋር ክልል ውስጥ እንደ ጨው፣ ፖታሽ፣ ድኝ፣ ማንጋኔዝ፣ ቤንቶኔት፣ እብነ በረድ፣ የኖራ ድንጋይ እና ፔትሮሊየም ዋና ዋና ማእድናት ይገኛሉ፡፡ የተንዳሆ የከርሰምድር ሀይል ማመንጫ ለኤሌሪክ ማመነጫነት ከፍተኛ አገልግሎት የመስጠት አቅም አለው፡፡

  •  ቱሪዝም እና ቅርሶች
   • የአዋሽ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን፣ የያንጉዲ ራሳ ብሄራዊ ፓርክ እና በምድር ዝቅተኛ ቦ የሆነው የዳሎል ዝቅተኛ ቦታ እነዚህ ሁሉ በኢትዮጵያ በረሃማ ውበቶች መገለጫዎች ናቸው፡፡

                   ዳሎል

   • በነዚህ ፓርኮች ከሚገኙ የዱር እንስሳት መካከል የአቢሲንያ የሜዳ አህያ፣ አዞ፣ አንበሳ፣ ድኩላ፣ የበርሀ ተኩላ፣ የዱር ድመት፣ አቦሸማኔ ና ሚዳቆ ይገኙበታል፡፡
   • ከዚህ ሁሉ ባሻገር ይህ ክልል 4.4 ሚሊዮን አመት ያለው የሰው ልጅ ቅሪተ አካል መገኛ ነው፡፡


                  የሉሲ ቅሪተ-አካል

  ምንጭ:-  
  • የኢትዮጵያ መንግስት ፖርታል (http://www.ethiopia.gov.et/)
  • ማእከላዊ ስታትስቲክስ እጀንሲ (http://www.csa.gov.et)
  • www.maps.google.com

 • loader Loading content ...

Load more...