loader
 • የ፳፻፮ ዓ/ም በጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች

  @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በ፳፻፮ ዓ/ ም በሰባት የተለያዩ ዘርፎች ከ፻፳ በላይ በጎ ኢትዮጵያውያንን ጥቆማ በመውሰድ የሚከተሉትን ሰባት በጎ ሰዎች ሸልሟል።


                 በባሕል፣ ቅርስና ቱሪዝም ዘርፍ - ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ

  የሐረር ሸሪፍ ሙዝየም መሥራችና ባለቤት የተማሩት የአካውንቲንግ ሞያ የሠሩት በጭላሎ እርሻ ልማት ቢሆንም የሀገራችን ታሪክና ቅርስ ጉዳይ የሚቆጫቸው ሰው ናቸው፡፡ ከ23 ዓመት በፊት የሐረርን ታሪክ፣ ቅርስ፣ የወግ ዕቃዎች፣ በቁፋሮ የተገኙ ታሪካዊ መረጃዎች፣ መጻሕ ፍትና ሌሎችንም በቤታቸው ውስጥ ማሰባሰብጀመሩ፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ የሚያምናቸውና የሚያከብራቸው አብዱላሂ ሸሪፍ ሕዝቡ ሥራቸውን ተመልክቶ ያገኛቸውንና በእጁ የሚገኙትን መረጃዎችና ቅርሶች ይሰጣቸውነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ቤታቸውን ሙዚየም አድርገው ሲያሰባስቡና ሲያሳዩ የነበሩት አብዱላሂ ሸሪፍ ለሥራው ዋናው የገቢ ምንጫቸውም የራሳቸው ገቢ ነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ሲሠሩበት የነበረው ቤታቸው ‹‹በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግለሰብ የቅርስ ስብስብ›› ተብሎየተመዘገበ ሲሆን በ1990/91 ዓም ወደ ሌላ ቦታ ተዛወረ፡፡ የሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ሙዝየም የሐረር ገዥ የነበሩት ራስ ተፈሪ ወደ ነበሩበት ቤት በ1990/91 ዓም የተዛወረ ሲሆን ዛሬ ይህ ሙዝየም ‹‹ሸሪፍ የሐረር ከተማ ሙዝየም›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ በዚህ ሙዝየም ውስጥ ከ1200 በላይ ጥንታውያን መጻሕፍት፣ ከ400 ሰዓታትበላይ የሚወስዱ ጥንታውያን የድምጽ መረጃዎች፣ ጥንታውያን ሳንቲሞችን፣ ከመካከለኛው ዘመን ጀምረው የነበሩ የጦር መሣርያዎችን፣ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ ፎቶዎችን፣ የሐረርን የንግድ ግንኙነት የሚያሳዩ ሳንቲሞችን፣ መዛግብትን፣ የወግ ዕቃዎችን ሰብስበዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  በኪነ ጥበብ ዘርፍ - ታላቁ የጥበባት ባለ ሀብት ተስፋየ ሣሕሉ 

  ሰኔ 12 ቀን 1916 ዓም ባሌ ውስጥ ከዱ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ የትምህርት ዕድል ያገኙት ወላጆቻቸው ወደ ሐረር ከተዛወሩ በኋላ ነው፡፡ በአሥራ አራት ዓመታቸው አባታቸው አቶ መንበረ ወርቅ ለሚባ ሰው አደራ ሰጥተዋቸው ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡ አሳዳጊያቸውና ቤተሰቦቻቸው በጣልያን ጦርነት በማለቃቸው መጀመሪያ ጫማ በመጥረግ በኋላም በሆስፒታሎች አካባቢ በማገልገል ራሳቸውን ለመደገፍ ሞከሩ፡፡ ከዚያም ደግሞ በእቴጌ ሆቴል(ጣይቱ ሆቴል) ተቀጥረው ሠርተዋል፡፡ እዚሁ ሆቴል ሲሠሩ መጀመሪያ ክራርና ማሲንቆ ቀጥለውም ፒያኖ መጨዋት ጀመሩ፡፡ ከጣልያኖች ጋ በተፈጠረ አለመግባባት ከአዲስ አበባ ሐረር ተላኩ፡፡ እዚያ እያሉ ጣልያን ከኢትዮጵያ ተባረረ፡፡ በሐረርም የራስ ሆቴል የምግብ ቤት ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ በ1934 ዓም በጦርነት ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች ይሰብሰቡ ሲባል አባባ ተስፋዬ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ በዚሁ ዓመትም ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች የሚማሩበት ትምህር ቤት ገብተው መማር ጀመሩ፡፡ ይቀጥላል...


                 በሰብአዊ አገልግሎት ዘርፍ - ዶክተር በላይ አበጋዝ

  ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የልብ ሐኪም ዶክተር በላይ አበጋዝ የተወለዱት ህዳር 13 ቀን 1937 ዓ.ም በደሴ ከተማ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ያጠኑት ደግሞ ሕክምና ነው፡፡ በኋላም በሕጻናት ልብ ህክምና ስፔሻላይዝድ አደረጉ፡፡ ዶክተር በላይ ከ1973 ዓም ጀምረው ላለፉት 30 ዓመታት በሕጻናት ሕክምናና በሕጻናት ካርዲዮሎጂስትነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አገልግለዋል፡፡ ፔዲያትሪክስን በማስተማር፣ ስለ ሞያውም ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማሳተም ይታወቃሉ፡፡ከ1981 ዓም ጀምረው የአሜሪካ ፔዲያትሪክስ አካዳሚ አባል ሲሆኑ፣ በInternational Society of Hypertension in Blacks, The Pan African Society of Cardiology, The National Drug Advisory Board of Ethiopia አባል ሲሆኑ በEthiopian Medical Journal በአባልነት፣ በረዳት ዋና ጸሐፊነትና በሊቀ መንበርነት አገልግለዋል፡፡ ዶክተር በላይ አበጋዝ የማይረዱትና የማያግዙት የዓለም ክፍል የለም ለማለት ያስችላል፡፡ የHealing the Children USA, Save a Child's Heart ISREAL and Chain of Hope UK ተባባሪ ናቸው፡፡ ይቀጥላል...


                  በንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርናና ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ - ቤተልሔም ጥላሁን

  /ሮ ቤተልሔም ጥላሁን ሶል ሪብልስ የተሰኘው በአፍሪካ ታዋቂ ከሆኑት ጫማ አምራቾች አንዱን የመሠረቱና የሚመሩ ሰው ናቸው፡፡ ድርጅቱን የመሠረቱት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2005 ዓም ሲሆን ዋና ተግባሩም ኢትዮጵያ ውስጥ በባሕላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውል ይነበረውን በርባሶ ጫማ በዘመናዊ መንገድ አምርቶ ለዓለም ገበያ ማዋል ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዘነበ ወርቅ አካባቢ ተወልደው ያደጉት ወ/ሮቤተልሔም ጥላሁን በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎች በድህነት ምክንያት ብዙዎቹ ሥራ አጦች መሆናቸውን፤ ነገር ግን ማንም ያልተጠቀመበት ክህሎት ያላቸው መሆኑን በማስተዋል የእነዚህን ወገኖች አቅም ወደ ምርትና ገበያ ለመለወጥ ተነሡ፡፡ በዚህም መሠረት እኤአ በ2004 ዓም ከባለቤታቸውና ከቤተሰቦቻቸው ባገኙት የመነሻ ገንዘብ በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ከሚገኙ ታዋቂ የጫማ አምራቾች አንዱ የሆነውን ሶል ሪብልስ የተሠኘውን ኩባንያ መሠረቱ፡፡ በባሕላዊ መንገድ ይመረቱ የነበረውን የበርባሶን የአመራረት መንገድ በዘመናዊ መልክ በማምጣት ለአካባቢ ብክለት አስተዋጽዖ የማያደርግ፣ ካርቦን ዜሮ የሆነ ጫማ ለማምረት ችለዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ሀገራዊ ሰላምና ዕርቅ - ብጹዕ አቡነ ዮናስ

  ብጹዕ አቡነ ዮናስ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ ወደ አፋር አካባቢ የመጡት በ1972 ዓም ነው፡፡ የሁሉም አባት በመባል በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ የሚጠሩት አቡነ ዮናስ አያሌ የአፋር ልጆችን ፊደል ያስቆጠሩና ለከፍተኛ ማዕረግም ያደረሱ ናቸው፡፡ በተለይም በአፋር አካባቢ ያለው የመጠጥ ውኃ ችግር እንዲቀረፍ ገጠር ወርደው በማስተማር ሕዝቦ ችግሩን ራሱ እንዲቀርፍ አነሣስተዋል፡፡ ለአካባቢው አረጋውያን መኖሪያ 5227 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ እየሠሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 50 አረጋውያን በቦታው ይረዳሉ፡፡ ይህንን የአረጋውያን መርጃ ፕሮጀክት ለመደገፍም 7 ሄክታር መሬት ከመንግሥት ተቀብለው ከጃፓን ኤምባሲ ጋር በመሆን የአካባቢውን ሕዝብ አስተባብረው እያለሙ ናቸው፡፡ ይቀጥላል ...


                 በጥናትና ምርምር ዘርፍ - አምባሳደር ዘውዴ ረታ

  ጋዜጠኛ ዲፕሎማትና ደራሲ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተወለዱ፡፡ ቀድሞ ደጃዝማች ገብረ ማርያም ይባል በነበረውና ኋላ ‹‹ሊሴ ገብረ ማርያም›› ተብሎ በተሰየመው የፈረንሣይ ትምህርት ቤት የመጀመ ሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ከ1948 ዓ.ም እስከ 1952 ዓ.ም በፓሪስ የጋዜጠኝነት ሞያ ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ የሊሴ ገብረማርያምን ትምህርት ለጊዜው አቁመው እያሉ በ1945 ዓ.ም የራዲዮ ዜና አንባቢ ሆነው ሥራ ጀመሩ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አምባሳደር ዘውዴ ረታ በጋዜጠኝነት በዲፕሎማትነትና በመጨረሻም በደራሲነት በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ከ1945 ዓ.ም እስከ 1967 ዓ.ም በጋዜጠኝነት ሙያ በጋዜጣና ማስታወቂያ መሥሪያ ቤት የቤተ መንግሥት ዜና ጋዜጠኛና በራዲዮ ዜና አቅራቢ፣ የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣና የመነን መጽሔት ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ራዲዮ የብሔራዊ ፕሮግራም ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ወሬ ምንጭ ዋና ዲሬክተር ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት - አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ

  አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ለሃምሳ ሁለት ዓመታት አገራቸውን በዲፕሎማሲ መስክ ያገለገሉ አንጋፋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዓመታት አገራችንን ወክለው በተባበሩት መንግሥታት፣ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በአፍሪካ ህብረት በሠሩባቸው ጊዜያት በዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ በሰብዓዊ መብት፣ በስደተኞች፣ ትጥቅ በማስፈታት፣ በጸረኮሎኒያሊዝምና በመሳሰሉት ሰፊ እውቀትና የሥራ ልምድ አላቸው፡፡ እ.አ.አ. በ1962 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዲፕሎማትነት ሥራቸውን የጀመሩት በተባበሩት መንግሥታት መምሪያ ውስጥ ሦስተኛ ጸሐፊ ሆነው ነበር፡፡ ከሦስት ዓመት በኋላ ዕድገት አግኝተው በሁለተኛ ጸሐፊ ማዕረግ ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት እንዲሠሩ ተመደቡ፡፡ በዚህ ኃላፊነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ እ.አ.አ. በ1970 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በቅድሚያ በአፍሪካ መምሪያ ቀጥሎም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ገለልተኛ አገራት መምሪያ ውስጥ በፖለቲካ ኦፊሰርነት ሠርተዋል፡፡ ይቀጥላል...

  ምንጭ:
  የበጎሰው ድረ-ገፅ እና የዳንዔል እይታ ድረ-ገፅ
  http://www.begosew.com/index.php/4-2006-winner
  http://www.danielkibret.com/2014/06/2006_10.html
  ለሰፊ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል።
 • loader Loading content ...

Load more...