loader
 • ያንድ ኢትዮጵያዊ ፀባይ እንዴት ያለ ነው?

  @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
 • loader Loading content ...
 • @Tola (ቶላ)   2 years ago
  ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!
  ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ፣ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚከተሉት ፀባዮች አሉት ይሉናል።

  • ፈሪሃ እግዚአብሔር
  የኢትዮጵያ ህዝብ ትንሳኤ ሙታንን ስለሚያምን፤ ደግ በመስራት ፅድቅ፤ ክፉ በመስራት ኩነኔ እንዳለ ያውቃል። ስለዚህም፣ "የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው።" የሚለውን መሰረታዊ ህግ ጠብቆ ህሊናውን ንፁህ አድርጎ ለመኖር ይጣጣራል፤ የፈጣሪው ረድኤት እንዳይለየውም ፆምና ፀሎትን ማዘውተር ይወዳል። ይህንን በመፈፀም ክፉ ከማሰብና ከመስራት ታጋሽነትን እንደሚያገኝ ያምናል።

  • ትሕትና
  የኢትዮጵያ ህዝብ በተፈጥሮው ትሁትና ሰው አክባሪ ነው። እንኯን የሚያውቀውን የማያውቀውንም ቢሆን በእድሜ ከበለጠው እጅ በመንሳት ሰላምታ ሠጥቶ እርስዎ ብሎ ቦታ ይለቃል።  ተቀምጦም  እንደሆነ ተነስቶ ያነጋግራል፤ በከብት ላይ እንደሆነ ይወርዳል። በማእረጋቸውና በጨዋነታቸው ሊከበሩ የሚገባቸውን ሰዎች ጌታዬ፣ እመቤቲ፤ እንዲሁም በእድሜ ታላቅ የሆኑትን አያ፣ እንኮዬ እያለ ማነጋገር የተለመደ ተግባሩ ነው። ወጣቶች እንኯን እርስ በርሳቸው ሲከባበሩ ጋሼ፣ አብዬ፣ አበባዬ፣ እትዬ ይባባላሉ።

  • ርህራሄ
  የኢትዮጵያ ህዝብ ሩህሩህ ነው። ወገኑ በተቸገረ ጊዜ ያለውን ከፍሎ ይሰጣል፤ ታስሮም እንደሆነ ዋስ ሆኖ ወይም እንደ አቅሙ እዳውን በመክፈል ያስፈታዋል። የታመመን ይጠይቃል፤ የታረዘን ያለብሳል፤ የተራበን ያበላል፤ የተጠማን ያጠጣል።

  • ታማኝነት
  የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ታማኝ ነው። ጏደኛውን እንደ ወንድሙ ይወዳል። የጌታውን ውለታ አይዘነጋም። አሳዳሪው ቢደኀይ እንኯን "በነበረው ጊዜ በልቼ፣ ሲቸግረው አልለይም፤ አልከዳም" ብሎ ተጎድቶም ቢሆን አብሮት ይቀመጣል። አንዳንድ አሽከር ጌታው ሲሞት ውለታ ለመመለስ ብሎ ከልጅየው ጋር መኖርን ይቀጥላል። አሽከሮቹም ጌታቸውን ዘመድ በሞተው ጊዜ የሃዘኑ ተካፋይ በመሆን ያፅናኑታል። ይህም የኢትዮጵያን ሰው ታማኝነት ከሚገልፁት ማስረጃዎች አንዱ ነው።

  • ቃል ኪዳን መጠበቅ
  የኢትዮጵያ ህዝብ ቃሉን አክባሪ ነው። በፅህፈትም ባይሆን ያደረገውን ስምምነት ይጠብቃል። በጋብቻም ሆነ በንብረት ግዢና ሽያጭ ላይ የወረቀት ስምምነት ሳያስፈልገው በሰጠው ቃል ብቻ ይፀናል። ብድሮ ጊዜ ከአባቶቻችን እንደሰማንው ብዙ መኯንንት እና ሃብታሞች ገንዘባቸውን ለነጋዴ እንዲሰራበት ሲሠጡ ያለፅሁፍና ያለምስክር ነበር ይባላል። አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኯን ቃሉን የማያከብር ሰው ባይጠፋም፣ በጠቅላላው በአንድ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚገኘው ታማኝነት መጠኑ በቀላሉ የሚገለፅ አይደለም።

  • እንግዳ ተቀባይነት
  የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ በመቀበል የታወቀና ስመ ጥሩ ነው። ይልቁንም ለውጭ አገር ሰዎች ባይተዋር በመሆናቸው፣ የተለየ ክብር እና አስተያየት ይሰጣቸዋል። ሰው ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜም መብሉን፣ መጠጡን፣ ከብቱን ለእርድ ያቀርባል። የአንዳንድ ክፍለ አገር ህዝብ ደግሞ እንግዳ ባየ ጊዜ ተሽቀዳድሞ ከቤቱ እንዲገባለት ይለምናል። ሃሳብ ሳይፈፀምለት ቢቀር ግን ያዝናል፤ ይቀየማል። ይህም በእውነቱ እጅግ የሚያስደስትና የሚያኮራ ደግነት እና ሩህሩህነት የተሞላበት የትቀደሰ ተግባር ስለሆነ ሊያስመሰግነው ይገባል። በኢኮኖሚም ረገድ ቢሆን እንኯን ዝናን አትርፎ ወዳጅ ስለሚገዛበት ያለግባብ ሃብት ባከነ የሚያሰኝ አይደለም።

  • እውነተኛነት እና ሃቀኝነት
  የኢትዮጵያ ህዝብ በታም ሃቀኛ ነው። ሙት ካለ ቃሉን ኣያጥፍም፤ በራሱ ይመሰክራል፤ ቅጣት የሚያስከትልበትም ቢሆን ያደረገውን አይክድም። በነፍስ ግዳይ የተያዘ እንኯን ቢሆን "ቢያናድደኝ፤ ቢዝትብኝ ገደልኩት" ይላል እንጂ አልታየሁም በማለት የሚያከራክር እና የሚያንጏትት ነገር ኣያመጣም። ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል እውነተኛ መሆኑን ያስረዳል። 

  ምንጭ: 
  የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል ስብስብ ስራዎች 
 • loader Loading content ...

Load more...