
-
@wubante 2 years agoSewasewerአንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ፣እንዲህ ሲል ተጣላ ከብርጭቆው ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሃን የምሰጥ፣
ጨለማን አትፍቸ የምገላልጥ።
አንተ ግን እፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበ ኸ ኝ እንዲህ ተደንቅረህ።አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ፣
ብርሃኔ ሩቅ ደርሶ ደምቆ እንዳያበራ።
ተሠራጭቶ በጣም እንዳይዘረጋ፣
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንህ ስራዬን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሃኔ ይስፋፋ።
እውነትማ ላንተ ከሆንኩህ ዕንቅፋት።
ልሂድልህ ብሎ ሲልቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰ የነፋስ ሽውታ፣መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፍታ።አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ፣
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ።
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሣ፣
ሰውም እንደዚሁ ያመጣል አበሳ።
ምንጭ:
- ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)
- ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)


Similar topics

Popular topics
የመጀምሪያዋ ዘመናዊ የኢትዮጵያ የጦር መርከብ ማን ትባላለች?
ያለፉት የኢትዮጵያ ነገስታት ማዕረግ ለምን "ዘእምነገደ ይሁዳ..." የሚለውን ተቀጽላ ያዘ?
የኢትዮጵያው ንጉስ አፄ ካሌብ (st. Elesbaan)
Meskea-hazunan Medhane Alem(Sidetegnaw) Church in Addis Ababa
የእቴጌ መነን አሥፋው ታሪክ ምን ይመሥላል? በአገዛዙ ላይ ምን አይነት ሚና ነበራቸው?
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ምን አይነት ቦታ አላት?
የላሊበላ ውቅር አብያተክርሥትያናት ሥንት ቤተ ክርሥትያኖችን የያዘ ነው?
የ፲፱፻፶፫ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ በፍጥነት ታቅዶ በፍጥነት የተከወነ ነው ይባላል። ለዚህ አባባል እ...
ጄነራል ተፈሪ በንቲ ከደርግ የተሰናበቱበት እና ኮሎኔል መንግስቱ ስልጣን ያጠናከሩበት ሂደት ምን ይመስል ነ...