loader
 • Ethiopian New Year (እንቁጣጣሽ)

  @Ruth   2 years ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @Ruth   2 years ago
  Sewasewer

  እንቁጣጣሽ (Enqutatash) which means “Gift of Jewels” is Ethiopian New Year day and it is celebrated on Meskerem 1 on the Ethiopian calendar which is September 11 or 12 when it is a leap year on Gregorian calendar. It is also the beginning fall, after the rainy winter season is over and when beautiful flowers are blossoming all over the cities. For Ethiopians this is a month of hope, celebration and exchange of gifts.

   This New Year festival has been celebrated for centuries and legends associate it with Queen of Sheba saying that when Queen Sheba returned after visiting King Solomon, her chiefs welcomed her by replenishing her treasury with “Enqu” or jewels

   The New Year evening at the end of Pagueme (the leap year) is the feast of Saint John in which torch (Chibo) is lit and neighbors come out and sing and dance together around the torch.

   The next day is እንቁጣጣሽ (New Year) is celebrated with exchange of gifts, cards and girls singing አበባየሆሽ (Abebayehosh) in groups and presenting bouquet of flowers, walking from house to house.   Reference: Ethiopian Festivals

 • loader Loading content ...
 • @Haset   1 year ago
  Sewasewer
  እንቁጣጣሽ

  በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከምናከብራቸውና ከምንዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጁ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በአዲሱ ዓመት መባቻ በወርሃ መስከረም ጋራ ሸንተረሩ በአደይ አበባ ይለመልማል። ሰው ሁሉ በአዲስ ተስፋ ይሞላል። ከወዳጅ ዘመዱ ጋር መልካም ምኞቱንም በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይለዋወጣል። ምክንያቱም ወሩ የዓመቱ መጀመሪያ የተስፋ ብስራት መንገሪያ ነውና።

  የዘመን መለወጫ በዓል እንቁጣጣሽ በመባልም ይጠራል። ለቃሉ የተለያዩ ትረጓሜ ሲሰጠው ይስተዋላል። በተለይም በመንፈሳዊ፣ በዓለማዊውና ከታሪክ አንፃር የሚሰጠው ትርጉም የተለያየ ቢሆንም ሁሉም ከዘመን መለወጫ በዓል ጋር የሚያያዙ መሆናቸው አንድ ያደርጋቸዋል። በከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማረኛ መዝገበ ቃላት ትርጓሜ መሰረት እንቁጣጣሽ ማለት በክረምት ዘመን በወፈረ መሬት ላይ የሚበቅል እንግጫ ማለት ነው። የእንግጫው ሥር ሽታው ለአፍንጫ የሚጣፍጥ፤ የዐውደ ዐመት ዕለት ልጆች ከአበባው ጋር እያሰሩ ለቤተ ዘመዱ የሚሰጡት፣ ሰጭውም እንቁጣጣሽ ብሎ ሲሰጥ ተቀባዩ በየዓመቱ ያምጣሽ ብሎ የሚመርቅበት ነው፡፡

  ስለ እንቁጣጣሽ ትርጓሜ ከሚነገሩ ታሪኮች በጥቂቱ፣

  አሮጌው ዓመት አልቆ አዲስ ዓመት ሲጀመር ዕለቱ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ እንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ አገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ በማለት ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

  ሁለተኛው ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቶና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉስ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ብቻ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኝቷት ሲያበቃ "ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ" ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት፡፡ በማለት የበአሉን ስያሜ አያይዘው የሚናገሩ የታሪክ ሰነዶች አሉ።

  ሌላው ትርጓሜ ደግሞ "ዕንቁ" እና "ጣጣሽ" በሚባሉት ሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን በየዓመቱ እንቁጣጣሽ ማለታችን የእንቁጣጣሽ ግብር፤ የእንቁጣጣሽ ገጸ በረከት ነው ብለን ለመመሰጋገንና መልካም ምኞታችንን ለመለዋወጥ የምንጠቀምበት እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

  ምንጭ:-  የኢትዮጵያ  ዓመት በዓላት
 • loader Loading content ...

Load more...