loader
 • የ ፀረተሃዋስያን (Antibiotics) መድሃኒቶችን በብዛት መወሰድ የሚያስከትሏቸው ዋና ዋና ጉዳቶች ምንድን ናቸው?

  @Ephrem Takele   6 months ago
  Sewasewer
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   6 months ago
  Sewasewer

  የማንኛውም ዓይነት መድሃኒት አጠቃቀም ውሱን መሆን አለበት።በተለይም ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች በአጠቃቀም እንዲወሰኑ የሚያስፈልግበት ምክንያት ከዚህ በታች ተመልክቷል ::

  1. መመረዝና አለርጂ -  ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች የበሽታ ጆርሞችን መግደል ብቻ ሳይሆን አካልን በመመረዝና በማስቆጣት አደጋ ያደርሳሉ :: በየዓመቱ ብዙ ሰዎች የማያስፈልጓቸውን ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች በመውሰጃቸው ይሞታሉ :: 
  2. ያሰውነትን የተፈጥር ሚዛን ማዛባት -  በአካል ውስጥ ያሉ ባክቴርያዎች በሙሉ ለጤና ጎጂ አይደሉም :: አንዳንዶቹ አካል በትክክል የተፈጥሮ ተግባሩን እንዲያከናውን ይረዳሉ :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች ግን ለአካል ጠቃሚ የሆኑ ባክቴርያዎችንም ከጎጂዎቹ ጋር በጅምላ ይገድላሉ :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒት የተሰጣቸው ህጻናት አንዳንድ ጊዜ በአፍና በምሳሳቸው ውስጥ ትራሽ ወይም ሞኒሊያሲስ የሚባል ፈንገስ ይወጣባቸዋል :: ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ዘረእንጉዳዮችን (ፈንገሶችን) የሚያጠፉትን ባክቴርያዎች የተወሰደው መድኃኒት ስሰሚፈጃቸው ነው :: ለብዙ ቀናት አምፒሲሊን ወይም ሌላ ብዙ ጀርሞችን በአንድ ጊዜ የሚገድሉ ፀረተሃዋስያን የሚወስዱ ግለሰቦች ተቅማጥ ይይዛቸዋል :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች ምግብ ለመፍጨትና ለማዋሃድ የሚረዱ ባክቴርያዎችን በመግደል የአንጀት ውስጥ የተፈጥሮ ሁኔታዎችን ያውካሉ ::
  3. ከመድሃኒቶች ጋር የመማመድ ሁኔታ - የረተሃዋስያን መድሃኒቶችን አጠቃቀም መወሰን ያስፈለገበት ክንያት ዘወትር ጥቅም ላይ ከዋለ የልዩ ልዩ በሽታ ሕዋሶች መድሃኒቱን ቀስ በቀስ ስለሚለማመዱና ፋይዳ ቢስ ስለሚሆኑ ነው::


  ስለዚህ ለማንኛውም ዓይነት ቀላል በሽታዎች ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶትን መጠቀም አይገባም:: ቀላል የቆዳ ቁስልን በውሃና በሳሙና በማጠብ፣ በሙቅ ውሃ በመዘፍዘፍና ጂቪ በመቀባት ማዳን ይቻላል :: ቀላል የአየር የመተንፈሻ ህመሞች (ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛ ወዘተ) ብዙ ውሃ በመጠጣት፣ በእንፋሎት በመታጠን፣ በቂና የተመጣጠነ ምግብ በመመገብና በቂ ዕረፍት በማድረግ ይድናሉ :: ለአብዛኛዎቹ የተቅማጥ ህመሞች ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች አስፈላጊ ካለመሆናቸውም በላይ ጉዳት ያስከትላሉ :: አስፈላጊው ነገር ህፃኑ ፈሳሾችን እንዲጠጣና እስከቻለ ድረስ በቂ ምግብ መመገቡን እንዲቀጥል ማድረግ ነው ::


  ምንጭ        
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...