loader

Topics (318)


loader Loading content ...

Explanations (72)


 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer

  የማንኛውም ዓይነት መድሃኒት አጠቃቀም ውሱን መሆን አለበት።በተለይም ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች በአጠቃቀም እንዲወሰኑ የሚያስፈልግበት ምክንያት ከዚህ በታች ተመልክቷል ::

  1. መመረዝና አለርጂ -  ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች የበሽታ ጆርሞችን መግደል ብቻ ሳይሆን አካልን በመመረዝና በማስቆጣት አደጋ ያደርሳሉ :: በየዓመቱ ብዙ ሰዎች የማያስፈልጓቸውን ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች በመውሰጃቸው ይሞታሉ :: 
  2. ያሰውነትን የተፈጥር ሚዛን ማዛባት -  በአካል ውስጥ ያሉ ባክቴርያዎች በሙሉ ለጤና ጎጂ አይደሉም :: አንዳንዶቹ አካል በትክክል የተፈጥሮ ተግባሩን እንዲያከናውን ይረዳሉ :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች ግን ለአካል ጠቃሚ የሆኑ ባክቴርያዎችንም ከጎጂዎቹ ጋር በጅምላ ይገድላሉ :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒት የተሰጣቸው ህጻናት አንዳንድ ጊዜ በአፍና በምሳሳቸው ውስጥ ትራሽ ወይም ሞኒሊያሲስ የሚባል ፈንገስ ይወጣባቸዋል :: ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ዘረእንጉዳዮችን (ፈንገሶችን) የሚያጠፉትን ባክቴርያዎች የተወሰደው መድኃኒት ስሰሚፈጃቸው ነው :: ለብዙ ቀናት አምፒሲሊን ወይም ሌላ ብዙ ጀርሞችን በአንድ ጊዜ የሚገድሉ ፀረተሃዋስያን የሚወስዱ ግለሰቦች ተቅማጥ ይይዛቸዋል :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች ምግብ ለመፍጨትና ለማዋሃድ የሚረዱ ባክቴርያዎችን በመግደል የአንጀት ውስጥ የተፈጥሮ ሁኔታዎችን ያውካሉ ::
  3. ከመድሃኒቶች ጋር የመማመድ ሁኔታ - የረተሃዋስያን መድሃኒቶችን አጠቃቀም መወሰን ያስፈለገበት ክንያት ዘወትር ጥቅም ላይ ከዋለ የልዩ ልዩ በሽታ ሕዋሶች መድሃኒቱን ቀስ በቀስ ስለሚለማመዱና ፋይዳ ቢስ ስለሚሆኑ ነው::


  ስለዚህ ለማንኛውም ዓይነት ቀላል በሽታዎች ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶትን መጠቀም አይገባም:: ቀላል የቆዳ ቁስልን በውሃና በሳሙና በማጠብ፣ በሙቅ ውሃ በመዘፍዘፍና ጂቪ በመቀባት ማዳን ይቻላል :: ቀላል የአየር የመተንፈሻ ህመሞች (ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛ ወዘተ) ብዙ ውሃ በመጠጣት፣ በእንፋሎት በመታጠን፣ በቂና የተመጣጠነ ምግብ በመመገብና በቂ ዕረፍት በማድረግ ይድናሉ :: ለአብዛኛዎቹ የተቅማጥ ህመሞች ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች አስፈላጊ ካለመሆናቸውም በላይ ጉዳት ያስከትላሉ :: አስፈላጊው ነገር ህፃኑ ፈሳሾችን እንዲጠጣና እስከቻለ ድረስ በቂ ምግብ መመገቡን እንዲቀጥል ማድረግ ነው ::


  ምንጭ        
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer

  ለማንኛውም ዓይነት የታወቀ በሽታ ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች ከተወሰዱ በአንድና በሁለት ቀኖች ውስጥ ማሻል ይጀምራሉ :: ፀረተሃዋስያኑ መድሃኒቶች አላሽል ካሉ ግን የሚከተሉትን ማወቅ ተገቢ ነው።

  1. ህመሙ በትክክል ባለመታወቁ የታዘዘው መድሃኒት ሊያድነው አልቻለም ማለት ነው :: 
  2. የፀረተሃዋስያኑ መድሃኒት አወሳሰድ መጠን ትክክል አለመሆኑን ተገንዝቦ፥ እርምት ማድረግ::
  3. የበሽታው ጀርም ፀረተሃዋሲውን መድሃኒት በመለማመዱ ለመቋቋም (ላለመጠቃት) ሃይል መፍጠሩን በመረዳት በተተኪነት ሊሰጥ የሚገባውን መድሃኒት መሞከር::
  4. በሽታውን ለማከም የሚያስችል በቂ ዕውቀት የለም ማለት ነው :: ስለዚህ የህክምና ዕርዳታ ማግኘት ይገባል ፤ በተለይም ችግሩ ከፍተኛ ከሆነና እየተባባሰ ከሄደ በአስቸኳይ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል፡፡


  ምንጭ        
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer

  1. አንድን ፀረተሃዋስያን መድሃኒት እንዴት እንደሚጠቀሙበትና ለየትኛው በሽታ እንደሚያገለግል በትክክል ካላወቁ ከመጠቀም መቆጠብ ይገባል :: 
  2. ሊታከሙ ለፈለጉት በሽታ የተፈቀደን ፀረተሃዋስያን መድሃኒት ብቻ መጠቀም ይበቃል ::
  3. ፀረተሃዋስያን መድሃኒት ከተወስነው መጠን በላይ ወይም በታች መታዘዝ የለበትም :: የመድሃኒቱ መጠን የሚወሰነው እንደግለሰቡ የበሽታ ዓይነትና ሁኔታ እንዲሁም ከዕድሜውና ከክብደቱ አንጻር ነው :: 
  4. ፀረተሃዋስያን መድሃኒት በአገልግሎት ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚያስከትለውን አደጋና ሊደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ሁሉ አስቀድሞ ማወቅና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል :: 
  5. ህመምተኛው መድሃኒቱን በአፉ መዋጥ ከቻለ በመርፌ ሊሰጠው አይገባም :: በመርፌ መሰጠት ያለበት የግድ አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ነው :: 
  6. ፀረተሃዋስያን መድሃኒት ህመምተኛው ከበሽታው ፈጽሞ እስኪፈወስ ድረስ መሰጠት አለበት ወይም የህመሙ ምልክቶች ትኩሳት ወዘተ ከጠፉ በኋላ ለሁለት ተከታታይ ቀኖች መስጠት ይኖርበታል :: (በነቀርሳ፣ በስጋ ደዌና በመሳሰሉት በሽታዎች የተያዘ ግለሰብ ከዳነ በኋላም ቢሆን መድሃኒት ለብዙ ወራትና ዓመታት ማቋረጥ የለበትም::)
  7. ፀረተሃዋስያን መድሃኒት ከተወሰደ በኋላ የቆዳ ሽፍታ፣ ማሳከክ፣ የመተንፈስ ችግርና ሌላ ከባድ የህመም ስሜት ካስከተለ ማቋረጥ ይገባል ::
  8. ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች መታዘዝ ያለባቸው እጅግ በጣም አስፈላጊ ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው :: ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች በብዛት ጥቅም ላይ ሲውሉ ሃይላቸው ይቀንሳል ::


  ምንጭ        
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer

  ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ሰዎች ካለጥርጥር አንዳንድ መድሃኒቶች ባይዎስዱ ይመረጣል።
  • ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች ለጤናቸው በጣም አስፈላጊ ከሆኑት መድሃኒቶች በስተቀር ምንም ነገር መውሰድ አይገባቸውም :: ቢሆንም የተወሰነ መጠን የብረት ማዕድንና የቪታሚን እንክብሎችን ያለምንም ሥጋት መውሰድ ይችላሉ ::

  • ለአራስ ልጆች መድሃኒቶችን መስጠት ካስፈለገ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት :: ማንም ሰው ለአራስ ልጆች መድሃኒት ከመስጠቱ በፊት የጤና ባለመውያ ምክርና ዕርዳታ መሻት ይገባዋል :: ብዙ መድሃኒት ከመስጠትም መቆጠቡ ይበጃል፡፡
  • የቃር በሽታ ወይም የሆድ መቃጠል (የጨጓራ ህመም) ያለባቸው ሁሉ አስፒሪንና የአስፒሪን ዝርያ የሚገኝባቸውን መድሃኒቶች መውሰድ የለባቸውም ::
  • አንዳንድ መድሃኒቶች የተወሰነ ዓይነት በሽታ ባለባቸው ግለሰቦች ሲወሰዱ ጎጂና አደገኛ ናቸው :: ለምሳሌ፣ የጉበት በሽታ (ሄፐታይቲስ) ላለባቸው ሰዎች ፀረተሃዋስያን መድሃኒቶች ወይም ሌሎች ከባድ መድሃኒቶች ከተሰጡ የታወከው ጉበት የተጎዳ በመሆኑ ማንኛውንም ነገር ሊያጣራ ስለማይችል መድሃኒቶቹ ለሰውነት መርዝ ይሆናሉ
  • የሰውነት መድረቅ (ዲሃይድሬሽን) ወይም የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች በሚወስዷቸው መድሃኒቶች ላይ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው :: ማንም ህመምተኛ ሽንቱን በሚገባ እስካልሸና ድረስ መድሃኒትን ከአንድ ጊዜ በላይ መስጠት አይገባም፡፡ ለምሳሌ፣ ህፃን ከባድ ትኩሳት ኖሮት ከሰውነቱ ውስጥ የፈሳሽና የሌሎች ንጥረ ነገሮች መባከን ቢደርስበት ሽንቱን በትክክል መሽናት ካልጀመረ በስተቀር ከአንድ ጊዜ በላይ አስፒሪን መውሰድ የለበትም ::


  ምንጭ       
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።

 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer

  በመጀመሪያ ደረጃ መድሃኒት መውሰድ ያለብን ግን በጣም አስፈላጊ ሲሆን ብቻ መሆኑን ለጤና ባለሙያዎቹም ማስታወስ ይኖርብናል :: በዚህ ሁኔታም ገንዘብን ከመቆጠብ በተጨማሪ ጤንነትን መጠበቅ ይቻላል :: አንዳንድ የጤና ባለሙያዎችና በርካታ ሐኪሞች፣ ህመምተኞች መድሃኒት ካልተሰጣቸው ደስ አይላቸውም በማለት ብቻ መድሃኒት ሳያስፈልግ ያዛሉ :: መድሃኒቶችን መውሰድ ግድ ሆኖ ስንወስድ ግን የሚከተሉትን መሰረታዊ መርህ መከተል ብልህነት ነው።

  1. ስለማንኛውም መድሃኒት አጠቃቀምና ሊወሰድ ስሰሚገባው ጥንቃቄ ማወቅ:: 
  2. ትክክለኛውን መጠን መጠቀምን ማረጋገጥ ::
  3. መድሃኒቱ ካልረዳ ወይም ችግር ካስከተለ መጠቀምን ማቆም:: 
  4. ጥርጣሬ ካደረ የህክምና ባለሙያ ምክር መጠየቅ ::


  ምንጭ       
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።

 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer

  ከታች የተዘረዘሩትን የጤና ችግሮች ከሳምባ ምች (ኒሞኒያ) በስተቀር አብዛኛውን ጊዜ ያለ ምንም መድሃኒት በውሃ ብቻ ማዳን ይቻላል :: መድሃኒት መጠቀም የሚያስፈልገው በጣም አስፈሳጊ ሲሆን ብቻ ነው ::

  • ተቅማጥና የፈሳሽ መባከን ፣ ትኩሳት የሚያመጡ የህመም አይነቶች
   • ብዙ ውሃ መጠጣት
  • ከፍተኛ ትኩሳት

   • ገላን ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ መንከር
  • ቀላል የሽንት ቧንቧ ህመም (ሴቶች ላይ በብዛት ይታያል)
   • ውሃ በብዛት መጠጣት
  • ሳል፣ አስም ፣ ደረቅ ሳል (ብሮንካይትስ)፣ የሳንባ ምችና ትክትክ

   • ብዙ ውሣ መጠጣትና በውሃ እንፋሎት መታጠን ጠቃሚ ነው (ወፍራም አክታን ያቀጥናል)::
  • የቆላ ቁስል፣ ችፌ ፤ የራስና የቆዳ ላይ ጭርት፣ ቆረቆር፣ ብጉር
   • በሳሙናና ውሃ አዘውትሮ መታጠብ
  • ያመረቀዙ ቁስሎች ፣ መዃመግል የቋጠሩ እባጮችና ብጉንጆች
   
   • በሞቀ ውሃ መዘፍዘፍ ወይም ማጀል ::
  • የሰውነት ጡንቻዎች ህመም ሲያስከትሉ፣ የመጋጠ

   • በሞቀ ውሃ መዘፍዘፍ ወይም ማጀል
  • ለቁርጭምጭሚት ወለምታ ወይም ቅጥቅጥ
   • ለመጀመሪያ ቀን በበረዶ ውሃ መያዝ
  • ለሚያሳክክ፣ ለሚያቃጥልና ለሚያዥ የቆዳ ላይ ሽፍታ
   • ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ
  • ለቀላል ቃጠሎ
   • ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ መንከር
  • የጉሮሮ ህመም ወይም ቶንሲል
   • ጨው ባለበት ትኩስ ውሃ መጉመጥመጥ
  • አሲድ ፣ ቆሻሻ ወይም ዓይን የሚያስቆጣ ጉድፍ
   • ዓይንን በቀዝቃዛ ውሃ ወዲያውኑ ማጠብና ለ15 ደቂቃ ያህል ሳያቋርጡ በውሃ ማጠብን መቀጠል
  • አፍንጫ ሲታፈን
   • ጨው የተጨመረበት ውሃ በዓፍንጫ መሳብ

  • ለሆድ ድርቀት
   • ብዙ ውሃ መጠጣት፣ (ሆድን መታጠብ የሚያስቀምጡ መድሃኒቶችን ከመጠቀም ይሻላል :: ነገር ግን አይብዛ::)
  • በትኩሳት የተነሳ ሽፍታ ከንፈሮች ላይ ሲፈነዳዳ

   • ቁስሉ (ሽፍታው) ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል በረዶ ማድረግ::

  ምንጭ      
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።

 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer
  አንድ ሰው ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ምልክቶች ውስጥ አንዱ ወይም ከዚያ በላይ ከታየበት ቤት ውስጥ መታከም ስለማይችል የጤና ባለሙያ ዕርዳታ ማግኘት አለበት :: ህይወቱ አደጋ ላይ ሊሆን ስለሚችል ዕርዳታውን በአስቸኳይ ማግኘት አለበት ::

  • በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ የሚደርስ ከባድ የደም መፍሰስ
  • ደም የተቀላቀለበት አክታ
  • የክንፈሮችና የጣቶች ጥፍሮች ሰማያዊ መሆን
  • ለመተንፈስ ችግር ሲፈጠርና በተለይም በዕረፍት ላይ እያሉ ሳይሻል ሲቀር
  • ህሊና መሣት
  • ህመምተኛው በጣም ድካም ሲሰማውና መቆም አቅቶት ለአንድ ቀን ወይም ከዚያ በላይ ሳይሸና ሲቆይ
  • ምንም ዓይነት ፈሳሽ ሳይጠጣ ለአንድ ቀን ወይም ከዚያ በላይ ሲቆይ
  • በከባድ ተቅማጥና ትውከት ለአንድ ቀን ወይም ከዚያ በላይ ሲሰቃይ፣ በህጻናት ላይ ከሆነ ለጥቂት ሰዓቶች ትውከት ወይም ተቅማጥ ከታየ
  • ክሰል የመሰለ ጥቁር ዓይነምድር መውጣት ወይም ደም ቅልቅል ማስታወክ
  • የሆድ ህመም፣ ትውከት ሲያስከትልና የዓይነምድር መውጣትን ሲከለክል
  • ለ3 ቀኖችና ከዚያም በላይ የሚቆይ ከባድና የማያቋርጥ የሰውነት ህመም ሲኖር
  • የአንገት መግረርና የወገብ እንደ ደጋን መጉበጥ፤ መንጋጋ እንደተዘጋ ወይም በጡናማ ሁኔታው እንዳለ ሲቆይ
  • ከአንድ ጊዜ በላይ ህሊናን በማሳት ሰውነትን የሚያወራጭ ትኩሳት ወይም ከፍተኛ ህመም ሲታይ
  • ማብረድ የማይቻል ከ39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ የሰውነት ትኩሳት ሲኖር ወይም ከ4 እስከ 5 ቀናት በላይ ትኩሳቱ ከቆየ
  • ለረጅም ጊዜ የሰውነት ክብደት ቀስ በቀስ እየቀነሰ ከሄደ
  • በሽንት ውስጥ የደም ተቀላቅሎ መገኘት
  • እየሰፋ የሚሄድና በህክምና የማይድን ቁስል
  • በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ የወጣ ቀስ በቀስ እያደገ የሚሄድ እብጠት
  • በእርግዝና ወቅት ደም ከመታ
  • በመጨረሻው የእርግዝና ወራት የሚደርስ የፊት እብጠትና አጣርቶ የማየት ችግር ካለ
  • ምጥ ከጀመረና የእንሽርት ውሃ ከፈሰሰ በኋላ የሚቆይ ምጥ
  • ከባድ የደም መፍሰስ

  ምንጭ     
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer  • የላይኛው የግፊት መጠን የልብ ጡንቻ ተኮማትሮ ደሙን ወደ ደም ቅዳ ደም ስር መርጨቱን የሚያመለክት ነው :: አንድ ጤናማ የሆነ ሰው የዚህ ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን አብዛኛውን ጊዜ በአማካይ ግምት ከ110 እስከ 120 ሚሊ ሜትር ይሆናል ::
  • የታችኛው የደም ግፊት በልብ ምት መካከል የተኮማተረው የልብ ጡንቻ መዝናናቱን የሚያመለክት ነው :: ይህም በአማካይ ግምት ክ60 እስከ 80 ሚሊ ሜትር ይሆናል :: 


  የአንድን ግለሰብ የጤንነት ሁኔታ ለማጠቅ የሚረዳው አብዛኛውን ጊዜ የላይኛው የደም ግፊት ልክ ሳይሆን የታችኛው የደም ግፊት ልክ ነው :: ለምሣሌ የአንድ ግለሰብ የደም ግፊት ልክ 140/85 ቢሆን እምብዛም የሚያስጨንቅ አይደለም :: ነገር ግን የደም ግፊቱ መጠን 135/110 ቢሆን ከፍተኛ የደም ግፊት ችግር ያለበት መሆኑን የሚጠቁም ስለሆነ ግለሰቡ የሰውነት ውፍረት ካለው የቅባት ምግቦችን በመተው ውፍረቱን እንዲቀንስ ወይም ህክምና እንዲያገኝ መምከር ያስፈል ጋል ::


  የታችኛው የደም ግፊት ልክ ከ100 በላይ ከሆነ አብዛኛጠውን ግለሰቡ የደም ግፊት ያለበት መሆኑንና በቂ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ያመለክታል :: ምናልባትም የምግብ ቁጥጥርና ህክምና ማድረግ ያስፈልገዋል ማለት ነው ::

  የአንድ ጤናማ ሰው የደም ግፊት ልክ አብዛኛ ውን ጊዜ ከ100/60 እስከ 140/90 ሊሆን ይችላል :: ነገር ግን የግለሰቡ የደም ግፊት ዘወትር ዝቅተኛ ከሆነ ምንም የሚያስጨንቅ ጉዳይ አይደለም :: በእርግጥ የአንድ ግለሰብ ዝቅተኛው የደም ግፊት ልክ ከ90/60 እስከ 110/70 ከሆነ ጤናማና ረጅምእድሜ ሊኖር የሚችል፣ ለልብ ህመም ወይም ስትሮክ የመጋለጥ እድሉ ዝቅተኛ መሆኑን ይጠቁማል፡፡  ምንጭ    
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer  የጤና ባለሙያዎች የደም ግፊትን በሚለኩበት ጊዜ ከሁሉ አስቀድሞ ግለሰቡ የተረጋጋ መንፈስ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው :: ለምሳሌ፣ የአካል እንቅስቃሴ እንዳደረገ ሳያርፍ የሚለካ ግለሰብ፣ የቁጣ ወይም የብስጭት ስሜት ያለበት ከሆነ የደም ግፊቱ በከፍተኛ መጠን ጨምሮ ይታያል :: ይህም ትክክለኛ መረጃን አይሰጥም:: ደምን ከመለካት በፊት ለግለሰቡ ስለደም አለካክ ዘዴ ገለፃ ማድረግና እንዳይፈራ ወይም እንዳይደነግጥ ማስገነዘብ ይገባል ::


  የጤና ባለሙያዎች የደም ግፊትን በሚለኩበት ጊዜ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ሲያስረዱ ከባድ የህክምና ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ ሊገነዘበው ወይም ሊረዳው በሚችለው ቋንቋ የታችኛውና የላይኛው የደም ግፊት ልክ የሚለውን አባባል ቢጠቀሙ ይመረጣል :: ሕብረተስቡ የላይኛውንና የታችኛውን የደም ግፊት ልክ ነጩ ደም እና ቀዪ ደም እያለ የተ ሳሳተ ግንዛቤ የያዘ ስለሆነ ተገቢውን የሙያ ምክር መስጠት ያስፈልጋል ::

  በሌላ በኩል ደግሞ ብዛት የሚባለበው አባባልም የደም ግፊት የሚለውን ትክክለኛ መጠሪያ የማይተካ በመሆኑ ተገቢው እርምት ሊደረግ ይገባል ::


  ምንጭ    
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
 • @Ephrem Takele   8 months ago
  Sewasewer
  በእጅ ፣ በእገር መደም በሌላ የሰውነት ክፍ የስሠሜት ማኖሩን ለማወቅ ግለሰቡ ዓይኑን እንዲሸፍን አድርጐ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹን ወጋ፣ ወጋ ማድረግ:: ከዚያም የመውጋት ስሜት ይሰማው እንደሆነ በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላል::  የሚከተሉት የእጅ ፣ የእግር ፣ ወይም የሌላ የሰውነት ክፍል የስሜት ማጣት መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ። 

  • ነጣ ካለ ቆዳ አካባቢ ምንም የማይሰማው ከሆነ የሥጋ ደዌ በሽታ ሊሆን ይችላል ::
  • በእጆችና እግሮች ላይ የመደንዘዝና የስሜት ማጣት ችግር ካለ መንስኤው የስኳር በሽታ ወይም የሥጋ ደዌ በሽታ ሊሆን ይችላል ::
  • በሰውነት አጋማሽ የመደንዘዝና የስ ሜት ማጣት ምልክት ካለ የጀርባ ህመም ችግር ወይም አደጋ ሊሆን ይችላል ::


  ምንጭ    
  ሐኪም በሌለበት ፣ በዴቪድ ወርነር ፣ በጠና አበረ።
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.