loader

Topics (134)


loader Loading content ...

Explanations (115)


 • @ርብቃ (ሰዋስው)   2 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.

  ጳውሎስ የተወለዱት ሃረር ልዩ ስሙ ቁልቢ አካባቢ ህዳር ፩፩ ቀን ፩፱፪፮ ዓ.ም. ሲሆን ያደጉት ግን በድሬደዋ ከተማ ነበር። ትምህርታቸውን እስከ ፬ኛ ክፍል ብቻ ቢከታተሉም ለስነ ፅሁፍ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ብዙ መፃህፍትን ያነቡ ነበር። ጋዜጠኛ ጳውሎስ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ በፀሃፊነት  ለረጅም አመታት በአዘጋጅነት  ደግሞ ለጥቂት ወራት ያገለገሉ ሲሆን  ከሚያዘጋጁትም ጽሁፎች "ደብዳቤዎቹእና "አንድ ጥያቄ አለኝ" በሚለው አምዳቸው ታዋቂነትን አትርፈዋል።  


  በድርሰቱም ሙያቸውም ብዙ መፅህፍትን ያሳተሙና ለንባብ ያበቁ ታላቅ ደራሲ ናቸው:: ስራዎቻቸውም በጥቂቱ
    -  አጫጭር ልብ ወለዶች (ከሴቶች አምባ፣ የአራዳው ታደሰ፣ የጌታቸው ሚስቶች)
    - ታሪካዊ መፃህፍት (አጤ ቴዎድሮስ፣ አጤ ምኒሊክ፣ የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦር ነት) ተጠቃሾች ናቸው::
  ከዚም በተጨማሪ የአፄ ምኒልክን በአገር ውስጥም ሆነ በአለም ዓቀፍ የተፃፃፉትን ደብዳቤ ከእንግሊዘኛ፣ ከአረብኛ፣ ከጣላኒኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም እንዳዘጋጅ ይነገራል::

 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   2 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.

  የፍርፍር አሰራር በመጀመሪያ ቀይ ሽንኩርት ልጦ አድቅቆ ከከተፉ በኋላ በድስት ውስጥ ጨምሮ በዘይት/ቅቤ ማቁላላት፤ ቀጥሎም በርበሬ መጥኖ ጨምሮ ሙቅ ውኅ ጠብ እያደረጉ ማማሰል፤ ስጋ መጨመር ከተፈለገ ጎላ ጎላ አድርጎ ከትፎ መጨመር እና ከቁሌቱ ጋር ማብሰል፤ ከዛም ቅመማ ቅመም እንደ ቁንዶ በርበሬና ቀረፋ መነስነስ፤ ከዛም ጨው እና ውሃ መጥኖ መጨመር፤ በጨረሻም ተክተክ ሲል እንጀራውን ቆራርሶ  መጨመርና  እያገላበጡ ማዋሃድ:: 

 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   2 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.

  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲአዲስ አበባኢትዮጵያ የሚገኝ የመጀመሪያውና ትልቁ የመንግሥት የከፍተኛ ትምሕርት ተቋም ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስምነት የኢትዮጵያን የትምህርት ፋናንና ዕርምጃን እንዲያሳይ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ከመመረቁ በፊት፣ መሠረቱ በንጉሠ ነገሥቱ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ተጣለ። ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ በመባል ይታወቅ ነበር፤ በኋላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን የዘውዳዊው መንግሥት ሥርዓት ካከተመ በኋላ የተመሠረተው ወታደራዊ መንግሥት አሁን በሚጠራበት ስሙ ሰይሞታል።
  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና አስተዳደሩን ሰድስት ኪሎ በሚገኘው በዋናው ጊቢ ያደረገ ሲሆን በአምስት ኪሎ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ- ሰሜን)፣ በአራት ኪሎ የሳይንስ ፋኩልቲ፣ በስድስት ኪሎ (የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ እንዲሁም የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ)፣ በጥቁር አንበሳ (የህክምና ፋኩልቲ ) በልደታ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ደቡብ)፣ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ የጥርስ ህክምና ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም በደብረዘይት ከተማ የእንሰሳት ህክምና ፋኩልቲን ያስተዳድራል። አዲስ አበባ በስሩ የሚከተሉትን ፋኩልቲዎች እና ኢንስቲቲዩቶች ይዞአል

 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   2 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  ግዮን ሁቴል አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ ሆቴሎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ሆቴሉን ታዋቂ ካደረጉት ነገሮች ውስጥ አንዱ፣ ውበቱ የሚነገርለት፣ ሰፊና በአበባ የደመቀው መናፈሻ ቦታ ነው። ግዮን ሆቴል የሚገኘው ከመስቀል አደባባይ አጠገብ፣ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በስተሰሜናዊ ምዕራብ በኩል፣ 6 ኪሎ ሜትር (3.7 ማይል)ርቀት ላይ ነው።
  በ1950 ዓ.ም. የተመሠረተው ግዮን ሆቴል በ123 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ነው፡፡ ሆቴሉ 191 መኝታ ክፍሎች፣ ሰባት የመሰብሰቢያ አዳራሾችና አንድ የመዋኛ ገንዳ አለው፡፡ የተለያዩ ሬስቶራንቶችም አሉት፡፡
 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   2 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  “(እቴጌ) ጣይቱ ሆቴል” በሀገራችን ቀዳሚው ሆቴል መሆኑን በርካታ ድርሳናት መዝግበዋል፡፡ ሆቴሉ በ1898 ዓ.ም በነሀሴ ወር ግንባታው ተጀምሮ በ1900 ዓ.ም ጥቅምት 25 ቀን ተመርቆ መከፈቱን ታላቁ ብዕረኛ ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለውና የአጼ ምኒልክን ታሪክና ተግባራት በከተበበት መጽሐፉ ይገልጻል፡፡
  በዘመኑ በነበረው ባህልና ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦች ምክንያት በወቅቱ ሆቴል ከፍቶ “ምግብ ከፍላችሁ ተመገቡ፤ መጠጥም እንዲሁ” ማለት፣ እንዲሁም ሆቴሉ እንኳን ቢገኝ ከፍሎ መመገብ እንደነውር የሚታይ በመሆኑ፣ ህዝቡም ሆነ መኳንንቱ ስለማይፈጽሙት ጉዳዩ ንጉሡን አጼ ምኒልክንም ሆነ እቴጌ ጣይቱን እጅጉን አሳስቧቸው ነበር፡፡ እናም ምኒልክና ጣይቱ ይህንን መፈጸም ነውር እንዳልሆነ በቅርባቸው ላሉ መኳንንት ከማስረዳት ባለፈ በርካታ ጥረቶችን አድርገዋል፡፡ ነባሩን ባህልና ልማድ ባጠበቀ ማህበረሰብ ውስጥ አዲስ ባህልን መትከል ቀላል አይደለምና፡፡ የጳውሎስ ትረካ ይህን ይላል፡-
   “እንደ አገር አባባል ጣይቱ እጅ የሚያስቆረጥም ወጥ እያሠሩ ገበያ ቢጠብቁ ጠፋ:: እንኳን ምግብ መብላት ከግሪኮች ሻይ ቤት ገብቶ ሻይ መጠጣት ነውር ነበረና ጣይቱ ጠዋት የሚያሠሩት ወጥ ለሠራተኞቹ የማታ ራት ይሆን ጀመር፡፡ የሚስታቸው ገበያ ማጣት ያሳሰባቸው አጤ ምኒልክ አንድ ቀን ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በአካባቢያቸው ላሉ መኩዋንንቶች “ጣይቱ ምግብ የሚሸጥበት ቤት ከፍታለችና ኑ እንሂድና ልጋብዛችሁ” ብለው ወሰዱዋቸው፡፡ መኳንንት በላ ጠጣና ምኒልክ 30 ብር ከፈሉ፡፡

  በማግሥቱ እንደተለመደው ገበያ ቢጠበቅ ጠፋ ቀጥሎም ጠፋ፤ ቀጥሎም ጠፋ፡፡ እንደገና ምኒልክ ሆቴል ገብቶ መብላት ነውር ያለ መሆኑን ለመኳንንቱ ገልፀው እንደገና ምሣ ጋበዙ፡፡ በሌላው ቀን አሁንም ገበያ አልተገኘም፡፡ ቢጠበቅ ቢጠበቅ ድርሽ የሚል ሰው ጠፋ፡፡
  በሌላ ቀን ደግሞ አጤ ምኒልክ ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በዙሪያቸው ላሉ መኳንንት “ሰማችሁ ወዳጆቼ” አሉ:: “በፈረንጅ አገር አንድ ቀን አንድ ሰው የጋበዘ እንደሆነ ያ የተጋበዘ ሰው በሌላ ቀን ደግሞ ብድሩን ይከፍላል ብድሩን ካልከፈለ ግን እንደ ነውር ይቆጠርበታል፡፡” ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ መኳንንቱ “እርስዎን ፈርተንና አፍረን ነው እንጂ የሚሆንልን ከሆነ የምኒልክን ብድር ለመመለስ እኔ አለሁ” እያለ ተራ በተራ ከሆቴል ቤት ምኒልክንና ጣይቱን ይጋብዝ ጀመረ፡፡ ገበያ እየደራ ሄደ፡፡ ምሳችንን እቴጌ ሆቴል ሄደን እንብላ የሚለው ስለበዛም ስሙ እቴጌ ሆቴል ተባለ፡፡”

         --- ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ ጥር ፱ 2007 ኧትም
 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   3 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  አዳም የትላንቱ የጥንት የጠዋቱ ሳይለፋ ሳይታክት ተኝቶ ባደረ ውሃ አጣጭ አቻውን ተጎኑ ተቸረ ይብላኝ ላሁኑ አ ዳም ለታካች ምስኪኑ ምነው በተኛና በሸሸው ከጎኑ ለምትል ሄዋኑ
 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   3 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  በስልጣን ከፍ ከፍ በዝና ከፍ ከፍ በሀብትም ከፍ ከፍ ወደላይ ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ.... ከፍ ከፍ ከዛ የወደቅህ ዕለት አጥንትህ እንዳይተርፍ::
 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   3 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ቀዳሚ ኢትዮጲያዊ የቫዬሊን እና ፒያኖ ዐቀናባሪ ሲሆኑ የቀድሞ ሰማቸው የወብዳር ገብሩ ነበር:: የተወለዱተም ከባለሃብት በተሠቦቻቸው ከሆኑት ከንቲባ ገብሩ እና ካሣዬ የለምቱ እኤአ December 12, 1923 አዲስ አበባ ነው። የሙዚቃ ትምሀርታቸውን በሲውዘርላንድ እንደተከታተሉም ይነገራል። ለበለጠ መረጃ፣ http://www.emahoymusicfoundation.org
 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   3 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  ከተማዋ ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ በመረጡት ፡ ቦታ ፡ ማለትም ፡ በፍል ፡ ውሐ ፡ አካባቢ ፡ ላይ ፡ በባላቸው ፡ በዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ፡ ተቆረቆረች። ዳግማዊ ምኒልክ የሸዋ ንጉስ ሲሆኑ ደብረ እንጦጦ በደቡብ ዘመቻ ጊዜ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት ለጉብኝት በወረዱም ግዜ አንድ ያልተጨረሰ ውቅር ድንጋይ ቤተክርስቲያን አንዳገኙ ይነገራል። ሚስታቸው እቴጌ ጣይቱ ቤተክርስቲያን በእንጦጦ ላይ በጀምሩበት ወቅት፣ የምኒሊክ ዝንባሌ ወደእዚህ ስፍራ በተለይ ተሳበ፣ አዲስ ፡ አበባ ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ (1879) ፡ ዓ/ም ፡ ፍልውሃ ፡ ፊል-ፊል ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተው ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ዋና ፡ ከተማ ፡ ስትሆን ፡ በተጨማሪ ፡ የአፍሪካ ፡ ሕብረት ፡ መቀመጫ ፡ እንዲሁም ፡ የብዙ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅት ፡ ቅርንጫፎችና ፡ ሌሎችም ፡ የዓለም ፡ የዲፕሎማቲክ ፡ ልዑካን ፡ መሰብሰቢያ ፡ ከተማ ፡ ናት።.............ለበለጠ መረጃ am.wikipedia.org/wiki/አዲስ_አበባ
 • loader Loading content ...
 • @ርብቃ (ሰዋስው)   3 years ago
  Team Sewasew, and believes in social learning.
  (አባባል) ሰዎች የሚሠሩት በሚያውቁት መጠን ነው፣ የተሻለ እስኪያውቁ።
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (8)


loader Loading content ...