loader

Topics (3)


loader Loading content ...

Explanations (3)


 • @Fish Giz   2 years ago
  Sewasewer

  ከክርስቶስ ልደት በኋላ ፡ በአንደኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በንግሥት ህንደኬ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የጥምቀት ዜና በአራት ኛው ክፍለ ዘመን በኦብርሃና አጽብሐ ዘመነ መንግሥት በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ስብከት ተስፋፍቶ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስብከተ ወንጌልን አምኖ ጥምቀትንና ክርስትናን ተቀበለ፡፡

  እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ የአይሁድ (ጁዳይዝም) ሃይማኖት አማኞች በወንጌል አናምንም ክርስቲያን አንሆንም ፣ ሕገ ኦሪትን አንለቅም በማለት በ፱፻፹፪ (982) ዓ. ዓለም ግደማ በቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን የመጣውን እምነተ እሥራኤል መከተልን ቀጠሉ፡፡

  የክርስትና ሃይማኖት አንቀበልም ብለው በአይሁድ (የኦሪት) እምነታቸው የፀኑት ሕዝቦች በነገሥታቱ ትእዛዝ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከሆነችው ከአክሱምና ከዙሪያዋ እየለቀቁ በመውጣት በወልቃይት፣ በሰሜንና ፥ በወገራ ፣ በደምቢያ ፥ ዛአገው ፥ በላስታ ፥ በሰቆጣና በመሳሰሉት ሊኖሩ እንደሚችሉ ስለ ተገለጸላቸው አክሱምንና አካባቢዋን እየለቀቁ በመሔድ ተበታትነው ይኖሩ ጀመረ ። በዚህ ምክንያት ፈላሻ ተባሉ ፡፡

  ፈላሻዎች እምነታቸው ሕገ ኦሪት ቢሆንም ኢትዮጵያዊነታቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ፥ በመንግሥት ትእዛዝ በተፈቀደላቸውና በሚኖሩባቸው በሰሜንና በላስታ እንዲሁም በተለያዩ ሥፍራዎች ለረዥም ጊዜ በመኖር ቁጥራቸው እየበዛ ሔደ ፡፡ የሕዝቡ ቁጥር እየበዛ ሲሄድም ለአክሱም መንግሥት ግብር እየከፈለ በሰላም ይኖር ጀመር፡፡

  በዘጠነኛው ምዕተ ዓመት ፰፻፶፪ (852) ዓ.ም ገደማ ዮዲት የተባለችው የጌዴዎን ልጅ ንግሥት ዘሯ ከፈላሻ ውስጥ በመሆኑ ፈላሾችን ይዛ ተነሣች። በላስታ የሚኖር የክርስትያን ሃይማኖት ተከታይና የቡግና ባላባት በዮዲት ውበትና ኃይለኛነት ስለተማረከ ሃይማኖቱን ለውጦ አገባት። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ኃይል ለማግኘት ቻለች ፡፡

  በዚህ ዘመን በአክሱም ዙፋን ላይ የተቀመጠው የንጉሥ ድግናዣን ልጅ አንበሳ ውድም ነበር ። አንበሳ ውድም አባቱ ሲሞት ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ቢሆንም የንግሥና ሥልጣኑን ያዘ፡፡ ዮዲትም ንጉሡ ገና ሕፃን ስለሆነ የሧን ጥቃት የሚቋቋም ኃይል ሊያሰባስብ እንደማይችል በመገመት አጋጣሚውን ተጠቅማ ልትወጋው አሰበች ፡፡

  ዮዲት ፈላሾች የሆኑትን ሁሉ በአንድነት አስባስባና አስተባብራ የአክሱም ንጉሥ አንበሳ ውድምን ለመውጋት ተነሣች ፡፡ ከላስታ ፣ ሰሜንና ወልቃይት የተሰበሰቡትን ፈላሾችና ሌሎችም ቀሥቅሣና አስፈራርታ በማስነሳት ብዙ ሠራዊት እየመራች ወደ አክሱም ዘመተች ፡፡ ወደ አክሱም በምትጓዝበት ጊዜ ያለፈችበትን ሥፍራ ሁሉ ሠራዊቷ ይመዘብርና ያጠፋ ነበር ። አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎችም ውድ የሆኑ የባህል ቅርሶች የተቃጠሉትና የወደሙት በዮዲት ወረራ ነበር ፡፡

  ይህን በስፋት ይካሄድ የነበረውን ጭፍጨፋ ለመቋቋም የተሳናቸውና በሥጋት ላያ ወድቀው የነበሩት የአክሱም መሳፍንትና መኳንንት ፋታና ጊዜ አግኝተው መልሰው ለማጥቃት እስኪችሉ ድረስ ሕፃኑን ንጉስ ይዘው ሸዋ ውስጥ ወደሚገኘው ወደ መንዝ ሸሹ ፡፡ መንዝ የተመረጠበትም ዋናው ምክንያት የመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ገደላማና ዋሻ በመሆኑ ጠላት ስለማይደፍረው ፥ ገፍቶም ቢመጣ ለመከላከል አመቺ በመመሆኑ ነበር ፡፡

  በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተረፉትና እስካሁን ድረስ ካሉት ጥቂቶች በስተቀር ሐውልቶችን ውብ የሆኑ የሥነ ጥበብ ቅርሶችንሞ አፈራርሳለች፤ አብያተ ክርስትያናትን አቃጥላለች ። የመንግሥት ዘርነት የነበራቸው የመሳፍንት ልጆችም መንግሥቱን አንዳይቀናቀኑና አንዳይሸፍቱ ሕዝቡንም እንዳያነሣሡ ተብሎ ወደ ደብረ ዳሞ ተራራ አየተወሰዱ በእስር እንዲቀመጡ ይደረግ ነበር ።ዮዲት

 • loader Loading content ...
 • @Fish Giz   2 years ago
  Sewasewer


  1.መርዕድ መንገሻ (ሜ/ጄኔራል) የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩ
  2.አክሊሉ ኃብተወልድ (ፀሐፊ ት እዛዝ) ጠቅላይ ሚኒስትር
  3.ይልማ ደሬሣ (አቶ) ገንዘብ ሚኒስትር
  4.አበበ ረታ ( አቶ ) የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
  5.ከበደ ተሰማ (ደጃዝማች) የግቢ ሚኒስትር
  6.ታደሰ ያዕቆብ (አቶ) የመንግስት ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር
  7.አማኑኤል አብረሃም (አቶ) የመገናኛ ሚኒስትር
  8.ክፍሌ እርገቱ (ደጃዝማች) የሀገር ግዛት ሚኒስትር
  9.ከተማ ይፍሩ (አቶ) የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
  10.ግርማቸው ተ/ሐዋርያት (ደጃዝማች) የእርሻ ሚኒስትር
  11.አስፍሐ ወ/ሚካኤል (ቢትወደድ) የፍርድ ሚኒስትር
  12.አሰፋ ለማ (ሻለቃ) የማዕድን ሚኒስትር
  13.ምናሴ ኃይሌ (ዶ/ር) ሚኒስትር (በንጉሠ ነገሥት ልዩ ጽ/ ቤት)
  14.ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ (ዶ/ር) የሥራ ሚኒስትር
  15.አብዱረህማን ሼህ (አቶ) ሚኒስትር (በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
  16.ሳሊት ሄኒት (አቶ) የፖስታ ሚኒስትር
  17.ሥዩም ሐረጎት (አቶ) የማስታወቂያ ሚኒስትር
  18.አብዱልህማን ሙሜ ( _ ) ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር
  19.በለጠ ገ/ጻዲቅ (አቶ) የመሬት ይዞታ ሚኒስትር
  20.ጌታሁን ተሰማ (አቶ) የሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ሚኒስትር
  21.አካለ ወርቅ ሀ/ወልድ (አቶ) የትምህርት ሚኒስትር
  22.ማሞ ታደሰ (አቶ) የፕላን ሚኒስትር • loader Loading content ...
 • @Fish Giz   2 years ago
  Sewasewer

  .ዳንኤል ክብረት

  ያሬድ ክብር አነሰው
  ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . ሰውም ሳይሰፍርባት አሜሪካ ታውቃ፣
  ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . . . እንዲህ ሳትሠለጥን አውሮፓም ተራቅቃ፣
  ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . . ዓለም፣ ከእንቅልፏ ሳትነቃ፣
  እነ ሞዛርት እና እነ ቤት ሆቨን፣ የዜማን ምልክት ገና ሳይነግሩን፣
  ያሬድ አንተ ነበርክ የዜማን ቅማሬ የሠራህልን፣ . . . .
  መንኮራኩር ሠርተው ጨረቃ ላይ ወጥተው፣ አፈር ስላመጡ ዓለም ተደነቀ፣
  ወሬው ተሟሟቀ፣ . . . .
  ከምዕራብ ተነሥቶ ከምሥራቅ ዘለቀ፣ . . . .
  ከሺ ዓመት በፊት ግን ያሬድ የተባለ አንደ ሊቅ ነበረ፣ . . . .
  ጨረቃንም አልፎ ጠፈር ተሻገረ፣ . . . .
  ሐኖስን ሰንጥቆ ሰማያት ውስጥ ገብቶ፣ . . . .
  አስደናቂ ዜማ ከመላእክት ሰምቶ፣ . . . .
  አኩስም ላይ አዜመው ከጽናጽል እና ከመቋሚያ አስማምቶ፣ . . . .
  ግና ምን ያደርጋል . . . . . . . ከጨረቃ አፈር የሚበልጥ ነገር፣ . . . .
  ጨረቃም ላይ ካለው የሚበልጥ ምሥጢር፣ ያሬድ ይዞ መጥቶ፣ . . . .
  የሚናገር እና የሚያደንቅ ጠፍቶ፣ . . . .
  ዓለም አያውቀውም አልሰማውም ከቶ፣ . . . .
  ያሬድ ግን ቅዱስ ነው ያሬድ ምሁር ሊቅ፣ . . . .
  ያሬድ መተርጉም ነው ምሥጢር የሚያረቅቅ፣ . . . .
  ያሬድ ፈላስፋ ነው ያሬድ ባለ ቅኔ፣ . . . .
  ያሬድ ባለ ዜማ የዜማው መጣኔ፣ . . . .
  ያሬድ ሐጋጊ ነው ሥርዓት የሠራ፣ . . . .
  ያሬድ መምህር ነው ዕውቀትን ያበራ፣ . . . .
  ያሬድ ቀማሚ ነው ብሉይ ከሐዲስ፣ . . . .
  ያሬድ ሰባኪ ነው ነፍስ የሚመልስ፣ . . . .
  ያሬድ አመልካች ነው ኖታን የፈጠረ፣ . . . .
  ያሬድ መናኒ ነው በጸሎት የኖረ፣ . . . .
  እነ ቸርችል፣ ፑሽኪን እና ካኒንግሃም አደባባይ መንገድ ሲሰየምላቸው፣
  ያሬድን ስላጡት አዘነ ልባቸው፣ . . . .
  ነቢይ በሀገሩ አይከብርም እንዲሉ፣ . . . .
  እኒህ ኢትዮጵያውያን እጅግ ይሞኛሉ፣ . . . .
  የእጃቸውን ንቀው ሌላ ያከብራሉ፣ . . . .
  ብለው አዘኑብን በፈጸምነው ግፍ፣ . . . .
  ያሬድን ረስተን ሌላውን ስናቅፍ፣ . . . .
  አይበቃም ወይ ታድያ የሞኝነት ኑሮ፣ . . . .
  መቅረት አለበት ወይ ታሪኩ ተቀብሮ፣ . . . .
  ይተረክ ታሪኩ ይነገር ዝናው፣ . . . .
  ይጠና ይመርመር ይታወቅ ሥራው፣ . . . .
  መወያያ ይሁን በየሚዲያው፣ . . . .
  መማማርያ ይሁን ትውልድ ያድንቀው፣ . . . .
  ያለበለዚያ ግን ያለፉትን ንቀን ወደፊት ብንሄድ፣ . . . .
  እኛንም የሚንቅ ይመጣል ትውልድ . . . .

   

 • loader Loading content ...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.