loader

Topics (13)


loader Loading content ...

Explanations (15)


 • @ቀዮ   2 months ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!

  የትውልድ ዘመን ፡ 19/1890

  ኔ አን ፥ ቬትናም

  ሞት ፡ መስከረም 3 ፣ 1969

  የቬትናም አብዮተእና ፕሬዚዳንት


  ሆ ቺ ሚን የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ መስራችና የመጀመሪያ መሪ ነበር። ከፈረንሳይ እና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመታገል የቬትናምን ነጻነት እና አንድነት እንቅስቃሴን በመምራት ከ1945 ጀምሮ እስከ  ሞተበት 1969 ድረስ የቬትናም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆኖ አገልግሏል።


  • ቀደምት ሕይወት

  ሆ ቺ ሚን የተወለደው ኑየን ሺን ኩን (Nguyen Sinh Cung) ፥ በማዕከላዊ ቬትናም በምትገኝ እና ኔ አን በምትባል አውራጃ ውስጥ ግንቦት 19 ፥ 1890 ላይ ነው። ኔ አን የሺህ ዓመት የቻይናውያን ቁጥጥር የተቃውሞ ማዕከል ነበረች። በ19 ኛው ምእተ አመት መጨረሻና በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ለነበረው የፈረንሳይ መሪዎች ተቃዋሚዎች አብዛኞቹ መሪዎችም ከዚሁ ክልል የወጡ ነበሩ። የሆ አባት ራሱን በማሰልጠን እና የሲቪል ሰርቪስ ፈተናን በማለፍ ለመንግስት ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። በመጨረሻም በቬትናም ጉዳዮች ውስጥ የፈረንሳይን ጣልቃ ግብነት በመቃወም ስራውን ለቀቀ። ሆ አሥር ዓመት ሲሞላው እናቱ በወሊድ ምክንያት አጣ። ሆ ሳም የተባለች ታላቅ እህት እና ኔም የተባለ ታላቅ ወንድም ነበሩት።


  ሆ ለአንድ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ድርጅት በተላላኪነት እየሰራ ሳለ ገና ዘጠን አመት ሲሞላው ነው የቀኝ አገዛዝን መቃወም የጀመረው ፤ አባቱም በጊዜው ከነበሩ በርካታ አብዮተኞች ጋር አስተዋውቀውታል። በመቀጠል ዌን ፥ ቬትናም ውስጥ በሚገኘው ብሔራዊ አካዳሚም ውስጥ በመግባት ትምህርቱን ተከታትሏል። በ1908 ጸረ ፈረንሳይ ተቃውሞ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ከትምህርት ቤት ተባረሩ። በ1909 ወደ ደቡብ ቬትናም በመሄድ እና አስተማሪ በመሆን ለአጭር ጊዜ ሰራ። ሆ ለአንድ የፈረንሳይ ኩባንያ በምግብ አብሳይነት ለመስራት በ1911 ውል ተፈራረመ። ለሁለት ዓመት ያህል በባሕር ላይ ሲሰራ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ወደሚገኙ ወደቦች በመሄድ የቋንቋ ችሎታውን ማዳበር ጀመረ። በዚህ መሰረት ከቬትናምኛ በተጨማሪ በቻይና ፥ በፈረንሳይኛ ፥ በሩሲያኛ ፥ በእንግሊዝኛ እና በቻይንኛ መግባባት ቻለ።


  • ለኮምኒዝም ራስን መስጠት

  በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት (1914-18) ፥ ሆ በለንደን ፥ እንግሊዝ እና በፓሪስ ፥ ፈረንሳይ ውስጥ ሠርቷል። በዚህ ጊዜ ነው ለኮሚኒዝም እና ለቬትናም ነፃነት የጋለ ስሜትን ማዳበር የጀመረው። ኮምኒዝም ማለት የማምረቻ ዘዴዎች (እንደ መሬት ፥ ፋብሪካዎች እና ማዕድን ያሉ) በግለሰቦች ሳይሆን በማህበረሰብ የተያዙ ናቸው። ኮሚኒስቶች ይህ አይነት ሥርዓት በአንድ ፓርቲ በኩል እና በአብዮታዊ በመንግስት ብቻ ሊተገበር ይችላል ብለው ያምናሉ። በፓሪስ ከተማ ሳለ ፥ ሆ ኑየን አ ኩ (Nguyen the Patriot) በሚል ስሙን በመቀየር እና የቬትናም ነፃነትን በመጠየቁ ትኩረትን ሳበ። ሆ እ.ኤ.አ በ1920 የፈረንሳይ ኮምኒስት ፓርቲ መስራች አባል ሆነ። ከ 1920 እስከ 1923 ድረስ ፥ በኢንተር ኮኔያል (Intercolonial) ህብረት ውስጥ ተሳትፎንውን በማሳደግ ሁለት ጸረ ኮሎኒያሊስት መጽሄቶችን ማሳተም ቻለ።


  ሆ በ 1923 ወደ ሞስኮ ለመሄድ በቀረበልት ግብዣ መሰረት ወደዛው ተጉዞ ኦሪዬንታል ሰራተኞች ዩኒቨርሲቲ (University of Oriental Workers) ውስጥ ተማረ። በ1925 የኮሚኒዝም እንቅስቃሴ ለማደራጀት ወደ ቻይና ተላከ። በዚህም መሰረት ፥ የቬትናም ወጣቶች አብዮታዊ ሊግን ለማቋቋም ቻለ። አብዛኞቹ አባላቶቹ በደቡባዊ ቻይና የወደብ ግዛት የሆነችው ካንቶን ከተማ ተማሪዎች ነበሩ። ሊጉ ነፃነት ፥ የመሬት ክፍፍል ፥ ፍትሃዊ ቀረጥ እና ለወንዶችና ለሴቶች እኩልነት እንዲኖር ጥሪ አቀረበ። በ1927 የቻይናን መንግሥት በካንቶን አካባቢ ኮሙኒስቶች ላይ ባደረገው ጥብቅ ቁጥጥች ሆ ቻይናን ልቆ ለመሄድ ተገደደ። እርሱ በማይኖርበት ጊዜ ሊጉ ወደ ተለያዩ አንጃዎች እና ቡድኖች መከፋፈል ጀመረ። በ1930 መጀመሪያ ላይ ሆ ወደ ደቡብ ቻይና በመመለስ ተከፋፍሎ የነበረውን የኮሚኒስት ፓርቲ አባላትን እንደገና በማደራጀት ከቬትናም ፥ ከካምቦዲያ እና ከላዖስ በመጡ አባላት አጠናከረው። በሆንግ ኮንግ እና በሻንጋይ ማደራጀቱን የቀጠለ ቢሆንም በ1931 በብሪቲሽ ተይዞ ለሁለት ዓመታት ታሰረ። በ1933 ከተለቀቀ በኋላ በሶቪየት ሕብረት ውስጥ ቀጣዮቹን ዓመታት አሳልፏል።


  • ወደ ቬትናም መመለስ

  እ.ኤ.አ በ1940 ወደ ደቡብ ቻይና ተመለሰ እና ከኢንዶ ቻይና የኮሚኒስት ፓርቲ (Indochinese Communist Party) አባላት ጋር ተገናኘ። በሚቀጥለው ግንቦት አብዛኛው የቬትናም ክፍል በጃፓን ቁጥጥር ስር በነበረበት ጊዜ በቬትናም ጠረፍ ላይ የፓርቲውን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በመምራት ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቬትናም መመለስ ቻለ። ሆ እና ICP ህብረት በመፍጠር ከፈረንሳይ አገዛዝ እና ከጃፓን ወታደራዊ ልዑክ ነፃነትን የሚጠይቅ ድርጅት አቋቋሙ። እ.ኤ.አ. ከ1941 እስከ 1945 በቻይና እንደገና ከአንድ ዓመት በላይ ቢታሰርም ሆ በደቡብ ቻይና ከሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና የደህንነት ባለስልጣናት ከ2 ሚሊዮን በላይ ለተራቡ ሰዎች የምግብ እርዳታ እና የፓርቲውን ወታደራዊ ኃይል ማጠናከር የሚችልበትን መንገድ በእርዳታ መልክ ጠይቋል።


  ነሐሴ 1945 በቬትናም ውስጥ ስልጣንን ለመያዝ ሙከራ አደረጉ። እ.ኤ.አ. መስከረም 2 ፥ 1945 የቪየትናም ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሆ ቺ ሚን በሃኖ ከተማ ውስጥ በብዙ ሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎች ፊት በመቆም “ቪትናም ነፃ አገር የመሆን መብት አላት — ይህም የተረጋገጠ ነው።” በማለት አወጀ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ (1939-45) ፈረንሳዮች ቬትናምን ዳግመኛ በቁጥጥር ስር ለማስመለስ ሞከሩ። ምንም እንኳን ሆ ከፈረንሳይ ጋር በፈረንሳይ ግዛት ውስጥ የቬትናም ነፃ መንግስት እንዲፈጥሩ ስምምነት በመጋቢት 1946 ላይ ቢፈርሙም ፈረንሳይ ሃሳቧን በመቀየሯ ምክንያት በታኅሣሥ ወር በቬትናም እና በፈረንሳይ ኃይሎች መካከል ጦርነት ተነሳ። በ 1954 ፈረንሳውያን በጦርነት ተዳክመው በጄኔቫ ጉባኤ ላይ ለመደራደር ፈለጉ። በሐምሌ ወር ላይ ቬትናምን ወደ ኮምኒስት (ሰሜናዊ ክፍል) እና ኮሚኒስት ያልሆነ (ደቡባዊ ጫፍ) ተብላ እንድትከፈል ስምምነት ተደረገ።


  • በስተመጨረሻ

  ከ1954 በኋላ ሆ ቺ ሚን የቪዬትናም የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት እና የኮሚኒስት ፓርቲ ሊቀመንበር እንደሆነ ቀጠለ። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሃላፊነቱን ለሌሎች ማሸጋገር ጀመረ። ሆ በአለማቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ነበር ፤ በሌሎች ሀገራት ውስጥ የቪዬትናም ጥቅሞችን በማስፋት እንዲሁም በሶቪዬት ሕብረት እና በቻይና መካከል መከፋፈልን ለማስቆም ሞክሯል። ሆ ከ1954 እስከ 1956 ያካሄዳቸው የመሬት ማልማት ዘመቻዎች ብዙም ስኬት አላስመዘገቡም። በቻይና ኮሙኒስቶች አምሳያ የተገነባው የመሬት ማካካሻ ዕቅድ ፥ በቬትናሞች ዘንድ ተቀባይነትን ባለማግኘታቸው የተነሳ አምስት ሺህ የሚሆኑ ገበሬዎች በ ሆ መንግስት ወታደሮች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።


  እ.ኤ.አ. በ1960 በደቡብ ቬትናም የነበረውን መንግስት የሚቃውም እና ብሄራዊ የነጻነት ግንባር (National Liberation Front - NLF) የተባለ እንቅስቃሴን በማደራጀት እና በመምራት ተሳትፏል። በመንግስቱ እና በ NLF መካከል የተደረጉ ግጭቶች የዩናይትድ ስቴትስን ወታደራዊ ኃይል ከደቡብ ቬትናሚዲያ ጎን እንዲቆሙ አድርጓቸዋል። የአሜሪካ ወታደራዊ ቁርኝቶች እየጨመሩ ሲሄዱ እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች በብዛት ሲደርሱ እና በ1965 ሰሜናዊ ቬትናምን በመቃወም ከፍተኛ የቦምብ ድብደባ ዘመቻ ሲያካሂድ ፥ ሆ ከሶቪዬት ህብረት እና ቻይና ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመሥረት ሙከራ አደረገ።


  ከ1960 ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የ ሆ ቺ ሚን ጤና እየተጓደለ በመምጣቱ ምክንያት አልፎ አልፎ ብቻ ለሕዝብ እይታ መቅረብ ጀመረ። ሆ ምንም ትዳር አልመሠረተም ፥ ነገር ግን በሰሜን ቬትናም የአገሬው አባት እንደሆነ በሰፊው ይታመናል። በዚህ የተነሳ ፥ ብዙውን ጊዜ ባክ (አጎት) ሆ እየተባለ ይጠራ ነበር። እ.ኤ.አ. በመስከረም 3 ፥ 1969  (በአሜሪካ የሚታገዘው የደቡብ ቬትናም መንግስት ከመሸነፉ ስድስት አመታት በፊት) በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ለክብሩ ሲባልም የሻዮን ከተማ በስሙ ሆ ቺ ሚን ሲቲ ተብሎ ተሰየመ።


  ምንጭ፤

  ታዋቂ ሰዎች

 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 months ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!

  የትውልድ ዘመን : እ.ኤ.አ. ሰኔ 27 ፣ 1880

  ቱስኮምቢያ ፣ አላባማ

  ሞት: ሰኔ 1 ፣ 1968

  አሜሪካዊ የአካል የአካል ጉዳተኛች ተሟጋች


  አሜሪካዊዋ መምህር እና ደራሲ ሄለን ኬለር (1880-1968) የአካል ጉዳተኞችን ትምህርትና ህይወት ለማሻሻል በመታገል አለምን ዞራለች።


  • መስማት እና ማየት አለመቻል

  ሔለን አዳምስ ኬለር የተወለደችው ሰኔ 27 ቀን 1880 ቱስኮምቢያ ፥ አላባማ ውስጥ ነበር። ወላጆቿ ካፕቴን አርተር ኤች ኬለር እና ካትሪን አደምስ ኬለር ነበሩ። አባቷ የጦር ሰራዊት አዛውንት (ከ1861 እስከ 1865 ድረስ በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ ለመለያየት የተዋጋው ሠራዊት አባል) ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ፥ በአካባቢው የሚታተም አንድ ጋዜጣ (the North Alabamian) አርታዒም ነበር። ሔለን ስትወለድ ጤነኛ ህጻን ነበረች። ስድስት ወር ስትሞላ ድግሞ መነጋገር ጀመረች። አንድ ዓመት ሲሞላት ከወላጆቿ ጋር መግባባት የምትችል ሲሆን መራመድም ችላለች። ሔለን የአስራ ስምንት ወር እድሜ ስትደርስ ከዓዕምሮ ጋር ግንኙነት ያለው ህመም ይታይባት ጀመር። ከፍ ያለ ትኩሳት ለብዙ ቀናት ከተመላለሰባት በሗላ ትኩሳቱ ጠፋ። ከዚህ ሃይለኛ ትኩሳት የተነሳ ሔለን መስማት የተሳናት እና ዓይነ ስውር ሆንች። በጣም አስቸጋሪ እና ለቁጥጥር አዳጋች ልጅ ሆነች። ደስተኛ ስትሆን ፥ መፍነክነክ እና መሳቅ ፤ ስትናደድ ድግሞ ፥ ማልቀስ እና እቃ ትሰብራለች። ሔለን ፍላጎቶቿን ከወላጆቿ ጋር ለመለዋወጥ ብዙ የራሷ የሆኑ ምልክቶችን ማበጀት ችላ ነበር።


  • የቅድመ ትምህርት

  ሔለን ስድስት ዓመት ሲሆናት እናትዋ መስማት ለተቸገሩ ሰዎች ስልጠና እየሰራች የነበረችውን ዶክተር አሌክሳንደር ግርሃም ቤልን (1847-1922) አነጋገረቻት። ቤል ከሄለን እና ከወላጆቿ ጋር ከተገናኘች በኋላ በቦስተን ፥ ማሳቹሴትስ ውስጥ የሚገኘውን የፔንክኪን መስማት እና መናገር ያቃታቸውን የሚረዳ ትምህርት ቤት እንዲያነጋግሩ መከረቻቸው። በመጋቢት ወር 1887 ዓ.ም በኢንስቲቱ ውስጥ አስተማሪ የሆነችው አን ሱሊቫን (1866-1936) የሄለን አስተማሪ ሆነች። አን ዕድሜዋ ሀያ አንድ ዓመት ሲሆን እሷ እራሷ የእይታ ውስንነት ነበረባት። ከአንድ ወር በኋላ ሱሊቫን ኬለርን "ውኃ" የሚለውን ቃል አስተማረቻት። ይህንን ያደረገችው የሔለንን የእጅ ጣቶቿን ተጠቅማ ነበር። ከዚህ በመነሳት ፥ ነገሮች ስሞች እንዳላቸው እና መምህሯ እነዚህን ስሞች በእጆቿ እንደጻፈቻቸው ተረዳች። ይህ ለሄለን ሰፊና አዲስ የመማር ዓለም ከፈተላት።


  አን ሱልቪያን ከሄለን ጋር ቀንና ሌሊት አብራት ነበረች። በዙሪያቸው የሚከናወኑ ነገሮችን ፥ ቃላትና ሃሳቦች በየጊዜው ትጽፍላት ነበር። ሔለን ፈጣን ተማሪ ነበረች። በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የእጅ ፊደል (የምልክት ቋንቋ) እና ብሬይል ፊደል ተማረች ፤ እናም ማንበብ እና መጻፍ ቻለች።


  • ትምህርት ቤቶችና ትምህርት

  ሔለን መናገር ለመማር ፈለገች እና በ1890 በቦስተን በሚገኘው በሆሬስ ማን መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ውስጥ ንግግር መማር ጀመረች። ትምህርቷን በትጋት ትሠራ ነበር። ከሃያ አምስት ዓመታት ከባድ ስራ እና ልምምድ በኋላ ሔለን ሌሎች ሊረዱት በሚችሉት ድምጽ መናገር ችላለች።


  ከ1894 እስከ 1896 (እ.ኤ.አ.) ሔለን ራይት ሁምሴን በሚባል መስማት ለተሳናቸው ትምህርት በሚሰጥ ትምህርት ቤት ትምህርቷን ተከታትላለች። ሔለን እውቀቷን ማዳበር በመቀጥል የሒሳብ ፥ የፈረንሳይኛ ፥ የጀርመንንና የጂኦግራፊ ትምህርቶችን ማሻሻል ቀጠለች። በዚህ መንገድ ሔለን የኮሌጅ ዝግጅቷን በማጠናከር ወደ ካምብሪጅ ት/ቤት (ለሴቶች እና ለወጣቶች) ገባች። አን ሱሊቫን በእያንዳንዱ ክፍል ከሔለን ጋር በመገኘት ሁሉንም ንግግሮች እና መጽሐፎት ትተረጉማለች። አሥራ ስድስት ዓመት ሲሞላት ፥ ኬለር ለራድክሊፍ ኮሌጅ የሚያበቃትን ፈተናዎች አለፍች። በ1904 በክብር ተመረቀች። ይህ ሁሉ የተደረገው በአን ሱልቫን የማስተማሪያ በፅሁፍን የመተርጎም እርዳታ ነው።


  • ሌሎችን መርዳት

  እንደ ወጣትነቷ መጠን ኬለር ስለ ዓለም ለመማር እና የሌሎችን ህይወት ለማሻሻል ቆርጣ ተነሳች። በማስተዋል ፥ በኃይል ፥ እና ለሰው ልጆች ባላት ጥልቅ ስሜት በዓለም ዙሪያ አስተምራለች። አስተሳሰቧን ወደ ኮንግረስ ለማስተላለፍ ሰርታለች ፥ የዓይነ ስውራንን ደህንነት ለማሻሻል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ደብዳቤዎችን ጽፋለች። ሆስፒታሎችን የጎበኘች ሲሆን ማየት የተሳናቸው ወታደሮችንም ትረዳ ነበር። ዓይነ ስውራን ደፋር እንዲሆኑና ህይወታቸው የተትረፈረፈ እና ፍሬያማ በማድረግ ለሌሎች እና ለራሳቸው ህይወትን እንዲኖሯ አስተምራለች።

  ሔለን ኬለር በጊዜዋ ከነበሩ ታላላቅ ሰዎች ማለትም ፤ አሌክሳንደር ግርሃም ቤል ፥ ማርክ ትዌይን (1835-1910) ፥ አንድርው ካርኒጌ (1835-1919) ፥ ጆን ዲ. ሮክፌለር (1839-1937) ፥ እና ፕሬዚደንት ግሮቨር ክሊቭላንድ (1838-1908) ፥ ካልቪን ኩሊጅ (1872-1933) ፥ እና ውድሮው ዊልሰን (1856-1924) ተርታ ለመሰለፍ በቅታለች። እንደ ሔለን ኬለር ጆርናል ከጨለማው የኋላው ህይወቴ እና ሃይማኖቴ የድንጋይ ግንብ መዝሙሮች እኔ የምኖርበት ዓለም እና የእኔ የህይወት ታሪክ የመሳሰሉትን መጽሃቶች ለመጻፍ ችላልች።


  ሱሊቫን እንደ ኬለር አማካሪ እና አጋር ሆፋ አገልግላለች። በ1968 ኬለር በሞተችበት ወቅት ስሟ የሰው ልጅን የመንፈስ ጥንካሬ ማሳያ ዓለም አቀፋዊ ምልክት ሆኗል።


  ምንጭ፤

  ታዋቂ ሰዎች

 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 months ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!

  የትውልድ ዘመን : ሚያዝያ 16 ፣ 1889

  ለንደን ፣ እንግሊዝ

  ሞት : ዲሴምበር 25 ፣ 1977

  እንግሊዛዊ ተዋናይ ዳይሬክተር እና ጸሐፊ


  የፊልም ተዋናይ, ዳይሬክተር እና ጸሐፊ ቻርሊ ቻፕሊን በፊልሞች ታሪክ ውስጥ ካሉት ዋነኞቹ ፈጣሪዎች አንዱ ነበር። የቻርሊ ቻፕሊን አስቂኝ አካሄድ እና አለባበስ በአለም ዙሪያ ካሉ ታዳሚዎች አድናቆት አሰገኝቶለታል።


  • አስቸጋሪ የሆነ የልጅነት ጊዜ

  ቻርለስ ስፔንቸር ቻፕሊን የተወለደው ሚያዝያ 16, 1889 በለንደን ፥ እንግሊዝ በሚገኝ አንድ ድሆች ወረዳ ውስጥ ነበር። የእናቱ ሐና ሂል ቻፕሊን ፥ ባለ ከፍተኛ ተሰጥዖ ነጋዴ ፥ ተዋናይ እና የፒያኖ ተጫዋች የነበረች ሲሆን አብዛኛውን ህይወቷን በአዕምሮ ህክምና ሆስፒታሎች ውስጥ እና በመመላለስ ነው ያሳለፈችው። አባቱ ቻርለስ ስፔንሰር ቻፕንሊን ትልቁ የመጠጥ ሱሰኛ ከመሆኑ በፊት ጥሩ ደስተኛ ዘፋኝ ነበር። ወላጆቹ ብፍቺ ከተለያዩ በኋላ ቻርሊ እና ግማሽ ወንድሙ ሲዴኒ አብዛኛውን የልጅነት ጊዜያቸው በማሳደጊያ ቤት ውስጥ ያሳለፉ ሲሆን ብዙ ጊዜ ይራቡና ጥፋት ካጠፉ ድግሞ ይገረፉ ነበር። በመጠኑ መጻፍ እና ማንበብ ከጀመረ በሗላ ትምህርቱን አቋርጦ ከኮሜዲያኖች ቡድን ጋር እየተዟዟረ ዝግጅቶችን ማቅረብ ጀመረ። በኋላ ላይ አስቂኝ ገጸ ባህሪያትን እየወከለ መተወን ጀመረ። በ19 ኛው እድሜው በእንግሊዝ ከሚታወቁ ተዋናዮች አንዱ ለመሆን በቅቷል።


  • ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት

  በ1910 ቻፕሊን ዝግጅቶቹን ለማቅረብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጓዘ። በዚህን ወቅት፥ በድምፅ አልባው የኪስቴል አስቂኝ ተከታታይ ፊልም እንዲተውን በፊልም አዘጋጅ ማክ ሴኔት (1884-1960) ተመርጧል። በነዚህ ቀደምት ፊልሞች ውስጥ ቻፕሊን የራሱን እና የታወቀበትን የትወና ዘይቤ ቀየረ። በመቀጠልም ቻርሊ ይሚታወቅበትን ዘ ትራምፕ (the tramp) የተባለውን ገጸ ባህሪ ፈጠረ።


  ቻፕሊን ከሠላሳ ያላነሱ ትንንሽ ፊልሞች ላይ ከተሳተፈ በሗላ ፥ የማክ ሴኔት ፍጥነት እና ውጥረት የበዛበት የፊልም አሰራር ዘዴ የራሱን ተሰጥዖ እየገደበበት እንደሆነ ተገነዘበ። በዚህም ምክንያት ወደ ኤሳኔይ ስቱዲዮ ለመሥራት ወሰነ። በዚህ ወቅት ከሰራቸው ፊልሞች ውስጥ የተወሰኑት His New Job The Tramp እና The Champion ሲሆኑ ሁሉም በአስቂኝነታቸው ይታወቃሉ። የ1917 ፊልሞቹን ጨምሮ One A.M. The Pilgrim The Cure Easy Street እና The Immigrant ከበፊቶቹም የትሻለ የኮሜዲ ይዘት የነበራቸው ነበሩ። በ1918 ቻፕሊን የራሱን ስቱዲዮ በማቋቋም ከብሔራዊ ፊልሞች (National Films) ከተባለ ድርጅት ጋር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ውል በመፈረም የድምጽ አልባ ፊልሞችን ለመስራት ተዋዋለ። ከነዚህ ፊልሞች ውስጥ የአንድ ውሻ ሕይወት (A Dog's Life) የተባለው ፊልም የአንድን ውሻ ህይወት ቻርሊ ከሚታወቅበት ገጸ ባህሪ ጋር ሲያወዳድር ፥ ትከሻ ክንዶች (Shoulder Arms) የተባለው ፊልም ደግሞ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን (ከ1914-18) ኣስቂኝ በሆነ መልኩ ያቀረበበት ነበር። ትንሹ ልጅ (The Kid) የተባለው ፊልሙ ደግሞ አሳዛኝ የሆነ የድህንት ኑሮን ይዳስሳል።


  • ዝና

  በ1923 ቻፕሌን, ዶ. ወ. ጊሪፍ ( D. W. Griffith) (1875-1948) ፥ ዳግላስ ፌርባንክስ (Douglas Fairbanks) (1883-1937) ፥ እና ሜሪ ፒፎርድ (Mary Pickford) (1893-1979) ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ዘመናዊ ፊልሞችን ለማምረት የተባበሩት አርቲስቶች (United Artists) የተባለ ድርጅት አቋቋሙ። የፓሪስ ሴት (1923) የተባለ ድራማ ፊልም ከሁለት የቻፕሊን አስቂኝ ፊልሞች ጋር በተከታታይ ለመስራት ቻሉ። ከዚህ በተጨማሪ ፥ ቻፕሊን የከተማ መብራቶች (City Lights) የተባለ ፊልም አስከትሎ መስራት የቻለ ሲሆን ፤ ይህ ፊሉም በብዙ ሃያሲያን ዘንድ ከምርጦች ስራዎቹ እንደ አንዱ ይቆጠርለታል። ከአንዶ ትይንት በስተቀር ፥ የከተማ መብራቶች (City Lights) ድምጽ አልባ ፊልም ነው።


  ዘመናዊው ጊዜያት (Modern Times) (1936) የተባለው ፊልሙ የዘመናዊውን ኢንዱስትሪ ጨካኝነት እና ስጋት ያሳየበት ሲሆን በፊልም ታሪክ ውስጥ በጣም አስቂኝ ገጠመኞችን እና የጨዋታ ቅደም ተከተሎችን ይዟል። ከሁሉም እጅግ አስቂኙ ትዕይንት ደግሞ የታወቀው የቻርሊ ገጸ ባህሪ ከተመጋቢ ማሽን ጋር ነው የሚያደርገው ግብግብ ነው። በታላቁ አምባገነን (The Great Dictator) (1940) ፊልም ውስጥ የቻንሊ ባህርይ የጀርመን ጦር ወታደራዊ መሪ አዶልፍ ሂትለር (1889-1945) ላይ ኃይለኛ ቧልት ያቀረበበት ነው። ይህ ፊልም የመጨረሻውን ፊልም ሲሆን የሚጥናቀቀውም በቻርሊ ቻፕሊን የፍቅር እና የነፃነት ንግግር ነው።


  ቻፕሊን እንደ ፊልም ዳይሬክተር እውነተኛውን ታላቅነት ያስመዘገበው በነዚህ በ1930 ዎቹ እና 1940ዎቹ የፊልም ትግበራዎች ነበር። በ1947 ቻፕሊን የሰራው Monsieur Verdoux የተባለው ፊልም እጅግ በጣም ጠንካራ የሞራል መግለጫዎችን ከያዙ እና በስክሪን ላይ ከታዩ ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው።  • የፖለቲካ አመለካከት

  በ1940 ዎቹ እና በመጀመሪያዎቹ 1950 ዎቹ ውስጥ ቻርሊን ገጥሞት የነበረው ቁጣ ከዚህ በፊት አግኝቶት ከነበረው ፍቅር እና ሙገሳ የማይተናነስ ነበር። የአሜሪካ ህዝብ በፖለቲካዊ አመለካከቱ ፥ በግል የህይወቱ ችግሮች እና በሌሎች መራራ ሁነታዎች ላይ ተሰጥዖውን በመጠቀም በገለጸበት መንገድ ተበሳጭቷል። እንደ አንድ ሶሻሊስት እና አምላክ የለሽነት ፥ ቻፕሊን ለአምባገነንነት ያለውን ጥላቻ በስራዎቹ በግልጽ አሳይቷል። ይህ ድርጊቱ በሰዎች ዘንድ ጥርጣሬን አስከትሎበት ነበር። ይህ የጥርጣሬ ስሜት Monsieur Verdoux የተባለውን ፊልሙን ከለቀቀ በኋላ የባሰውኑ እየጨመረ ሄዷል። ተቺዎች ፊልሙን ቢያመሰግኑትም የበለጠ ተወዳጅነትን የተረፈው ግን ከአሜሪካ ይልቅ በአውሮፓ በአውሮፓ የፊልም ታዳሚዎች ዘንድ ነበር። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ቻርሊ ሙሉ ጊዜውን Lending Limelight (1952) ለተባለው ስራው ሰጥቷል። የዚህ ፊልም ይዘት ለስለስ ያለ እና አንዳንዴም ሀዘን የቀላቀለ ሲሆን በህይወቱ ውስጥ ካጋጠሙት ክስተቶች ጋር ግንኙነት አለው።


  በ1952 ወደ አውሮፓ በእረፍት በነበረበት ጊዜ በዩኤስ የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኩል ቻፕሊን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት እንደማይችል ተነገረው። የዚህ ውሳኔ ምክንያት ደግሞ የብልግና ድርጊቶችን መፈጸም እና ፖለቲካዊ ጥርጣሬ ነበሩ። የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ያልነበረው ቻፕሊን ሁሉንም የአሜሪካ ንብረቶቹን በሙሉ በመሸጥ ከአራተኛዋ ሚስቱ እና ልጆቹ ጋር በጄኔቫ ፥ ስዊዘርላንድ መኖር ጀመረ። በ1957 ቻፕሊን በዩናይትድ ስቴትስ ያልታየውን የኒው ዮርክ ንጉስ (The King in New York) የተሰኘውን ፊልም ለመምራት ኢንግላንድን ጎብኝቶ ነበር። የቻርሊን የግል ታሪክ የያዘ መጽሃፍ በ1964 ታትሞ ነበር።


  • ዳግም ወደ አሜሪካ መመለስ

  በ1970 ዎቹ ሁኔታዎች ተለውጠዋል ቻፕሊን በፊልም ዙሪያ ላበረከተው ታላቅ አስተዋጽዖ እውቅና ተሰጠው። በ1972 በኒው ዮርክ ከተማ እና በሆሊዉድ ፥ ካሊፎርኒያ ውስጥ ልዩ እውቅናን ከመቀበል ባለፈ ልዩ የአካዳሚ ሽልማትን (Academy Award) ለማግኘት ችሏል። በ1975 እ.ኤ.አ. የእንግሊዝ ንግሥት ኤልዛቤት 2 (1926 ዓ.ም) የእንግሊዛዊያን ክብር የሰጡት ሲሆን ከሁለት ዓመት በኋላ ታኅሣሥ 25, 1977 ቻፕሊን በስዊዘርላንድ በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።


  ምንጭ፤

  ታዋቂ ሰዎች

 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 months ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!

  የትውልድ ዘመን ፡ ሐምሌ 26 ፣ 1856

  ደብሊን ፣ አየርላንድ

  ሞት : እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2 ፣ 1950

  ጸሃፊ እና ተቺ


  የብሪቲሽ ፀሐፊ እና ተቺያን ጆርጅ በርናርድ ሻው ከ 50 በላይ የሚሆኑ ድራማ እና ሶስት ጥራዝ የሙዚቃ እና የድራማ ትንተናዎችን አዘጋጅቷል። በርካታ ተቺዎች ከዊልያም ሼክስፒር (ከ1564 እስከ 1616) በሗላ የተከሰተ ታላቅ የእንግሊዝኛ ተዋናይ አድርገው ይቆጥሩታል።


  • ቀደምት ዓመታት

  ጆርጅ በርናርድ ሻው የተወለደው ሐምሌ 26 ቀን 1856 በዶብሊን አየርላንድ ነው። አባቱ ጆርጅ ካር ሲባል እናቱ ደግሞ ሉሲንዳ ኤሊዛቤት ጉርሊ ትባላለች። አባቱ የፋብሪካ ባለቤት የነበረ እና የመጠጥ ችግር የነበረበት ሰው ነበር። ሾው በልጅነቱ በአጎቱ አማካኝነት ስለ ጥንታዊ ጥበቦች ትምህርት ከወሰደ በሗላ ፥ የአስር ዓመት ልጅ በነበረበት ጊዜ በዳብሊን በሚገኘው የዊስሊያን ኪኒየር ትምህርት ቤት ገባ። ሻው ትምህርት ቤት ይጠላ የነበረ ቢሆንም ማንበብና መጻፍ ይወዳል። ስለ ሙዚቃ እና ስነ ጥበብ የሙዚቃ አስተማሪና ዘፋኝ ከነበሩት ከእናቱ ብዙ ነገሮችን ተማረ።


  ሻውል በ1871 በወር 4.50 ዶላር ደመወዝ  እየተከፈለው የቢሮ ተላላኪነት ስራ አገኘ። በ1876 እናቱ እና እህቶቹ በሚያስተዳድሩት በለንደን, እንግሊዝ ውስጥ የሚገኝ የሙዚቃ ትምህርት ውስጥ ለመስራት ስራውን ለቀቀ። በአስራ ስድስት ዓመት ዕድሜው ሻው ለአየርላንድ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ትችት እና ግምገማዎችን መፃፍ ጀምሮ ነበር። ሆኖም ግን በአራት ዓመታት ውስጥ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ ፥ አንዱ ብቻ ተቀባይነት አግኝቷል። ሻው በእናቱ እየተደገፈ ትችት መጻፉን ቀጠለ። ከዚህ በተጨማሪም ፥ የለንደንን ማኅበረሰብም በዘፈን ያዝናና ነበር።


  • የተለያዩ ጽሁፎች

  በ1876 እና 1885 መካከል ሻው አምስት መጽሃፎችን ጽፏል። ፀፀት የመጀመሪያው ለሃምሳ ዓመታት አልታተመም። ሌሎች አራቱ ደግሞ በተለያዩ መጽሔቶች ውስጥ ሊታተሙ በቅተዋል። የኢሶሻል ሶሺያሊስት (1884 ዓ.ም) በእንግሊዝ የመላው የማኅበራዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ታሪክ አካል ነው። የኬሸል ባይሮን ልምምድ (1882) በ1901 ተመርቆ በተለያዩ የድራማ መልኮች ቀርቧል። Irrational Knot ስለ ዘመናዊ ጋብቻ ገለፃ ሲሆን ከሄንሪኪስ ኢብሰን (1828-1906) የአሻንጉሊት ቤትጋር ተመሳሳይነት ነበረው። ይህ ሥራ የኛ ጥግ (Our corner) በሚባል መጽሔት ላይ ታተመ። ፍቅር በአርቲስቶች መካከል (1887-88) የተባለው ስራውም እንዲሁ በዚህ መጽሄት ላይ ቀርቧል።

  በ1879 ሻው የሶሻሊስት የውይይት መድረክን ተቀላቀለ። በማስከተል ደግሞ በ1884 ፌይሃን ማህበረሰብ የተባለ የሶሺያሊስት ቡድን ውስጥ ተቀላቀለ። በሻው አርትዖት የታተመው ፋቢያን ኢሴይስ (Fabian Essays) (1887) ፥ የኢኮኖሚክስን አስፈላጊነት (የሸቀጦችን ምርት ፥ ስርጭትን ፥ አጠቃቀምን እና አገልግሎቶች) እና የመደብ መዋቅር የሚያብራራ ጽሁፍ ነበር። በ1882 ሁለት ክስተቶች የሻውን የሶሻሊዝም ጉዞ አበሰሩ፡ አንደኛው የአሜሪካዊው ደራሲ ሄንሪ ጆርጅ እድገት እና ድህነት የተሰኘ ንግግር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የካርል ማርክስ (1818-1883) ዳስ ካፒታል (Das Kapital) የተባለው መጽሃፍ ነው። በ1914 ፥ ሻው የጦርነቱ የተለመደ ስሜት (Common Sense about the War) የተሰኘ ትችት የብሪታንያ መንግስት ላይ አቀረበ። የብሩኋ ሴት የካፒታሊዝም እና የሶሻሊዝም መመሪያ (The Intelligent Woman's Guide to Capitalism and Socialism) የተባለው እና በ1928 የታተመው የሻው ድርሳን እስካሁንም ድረስ በሶሻሊስት አስተሳሰብን ዙሪያ ከትጻፉ ድርሳናት መካከል ዋናው ነው።


  ከ1888 እስከ 1894 ዓ.ም ሾው ለተለያዩ መጽሄቶች እና ጋዜጦች ሙዚቃን የተመለከቱ የተለያዩ ትችቶች ጽፏል። በዚህ ወቅት መጨረሻ አካባቢ ለSaturday Review ትችቶችን በቋሚነት መጻፍ ጀመረ። በዚህ ሂደት ውስጥ ኢብሰንን (Ibsen) ለብሪሽ ህዝብ አስተዋውቋል። ከሻው ስራዎች ውስጥ Ibsenism መካከል Quintessence of Ibsenism በ1890 ፥ የጥበብ እሴት (The Sanity of Art) በ1895 ፥ እና ፍጹሙ ዋአኔራይት (The Perfect Wagnerite) በ1898 ለመታተም በቅተዋል።


  • የሻው ተውኔቶች

  የጋለሞታዎች ቤቶች (Widowers' Houses) የተሰኘው የሻው የመጀመሪያው ተውኔት በ1892 ተመርቋል። ሻው ይህንንም ሆነ ሌሎች የመጀመሪያ ስራዎቹን "ደስ የማይል" በማለት ልጿቸዋል። የሻዋ የመጀመሪያ የተሳዳ ተውኔት Arms and the Man and Candida የተሰኘው ሲሆን ፥ በ1894 ተመርቋል። ከሻው ስራዎችም መካከል ፥ በ1896 የተሰራው እና መቼም መናገር አችልም (You Never Can Tell) የተባለው የኮሜዲ ስራው እምብዛም ግምት ካልተሰጣቸው ስራዎቹ ውስጥ አንዱ ነው። በለንደን የሮያል ቲያትር ቤት ፥ የሻው ፥ የሼክስፒር ፥ እና የዩሪፒደስ ስራዎችን በ1904 እና 1907 መካከል በማሳየታቸው የተነሳ የሻው ስራዎች ተወዳጅነት ጨምሯል። ለአብነት ያህል ፥ አሥራ አንድ ያህል ስራዎቹ 701 ጊዜ ለመተወን በቅተዋል።


  በሃዘን ቤት (Heartbreak House), ወደ ማቱሳላ መመለስ (Back to Methuselah) (1921), ኤንድሮክል እና አንበሳው (Androcles and the Lion), እና ቅዱስ ዮሃንስ (Saint Joan) (1923) የተባሉት ስራዎቹ የምንግዜም ምርጥ የሾው ስራዎች ተብለው ይወሰዱለታል። ሻው ፥ ላበረከታቸው ፅሁፎች የ1925 የኖቤል ሽልማት ተሸልሟል። ሻው ፥ እስከ 1947 ድረስ ድራማዎችን መጻፍ ቀጥሎ ነበር። በዚህም መሰረት ፥ ቢሊዮን ብርቱዎች (Buoyant Billions) የተባለውን ስራውን በዘጠና አንድ አመቱ ነበር ያጠናቀቀው። ሽው ፥ በኖቬምበር 2 ፥ 1950 በእንግሊዝ አገር ውስጥ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አርፏል።


  ምንጭ፤

  ታዋቂ ሰዎች

 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 months ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!

  የትውልድ ዘመን : ሚያዚያ 8 ቀን 1938 እ.አ.አ

  ጋናዊ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማት


  የአለም አቀፍ ዲፕሎማቱ ኮፊ አናን የተባበሩት መንግስታት ሰባተኛ ጠቅላላ ሥራ አስፈጻሚ ሲሆኑ ይህንን ዓለም አቀፋዊ ድርጅት በመምራት የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ እና የኖቤል ተሸላሚ ናቸው። በጠንቃቃ ዲፕሎማሲያዊ ንግግራቸው የሚታወቁትን አናንን አንዳንድ ወገኖች ይህ ባህሪያቸው እንደ ደካማ ሊያስቆጥራቸው ይችላል ብለው ያስባሉ።


  • የአደባባይ ምሁር

  ኮፊ አታ አናን የተወለደው ሚያዝያ 8 ቀን 1938 በማዕከላዊ ጋና ፥ አፍሪካ ውስጥ ነው። ከ1960 ጀምሮ ጋና በብሪታንያ ጥገኛ የሆኑ የብሪታንያ ግዛቶች ቡድን የሆነው የጋራ ብልፅግና ቡድን አባልነት ላይ የተመሰረተች አገር ነች። ጋና ለ113 ዓመታት ያህል በታላቋ ብሪታንያ ትገዛ ነበር። አናን በሁለቱም ቤተሰቦቹ በኩል ከጎሳ አለቆች የተገኘ ነው። አባቱ የተማረ ሰው ስለነበር አናን ባሕላዊና ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤዎችን ልማድ እያደረገ አደገ። አናን እራሱን ”በጎሳ አለም ውስጥ ጎሰኛ ያልሆነ” በማለት ገልጾታል።


  አናን በጋና በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በኩማሲ ዋና ከተማ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ ትምህርቱን ተከታትሏል። በሃያ አመት ዕድሜው በማካሌስተር ኮሌጅ (Macalester College) ውስጥ ከፎርድ ፋውንዴሽን ባገኘው ስኮላርሺፕ የመጀመሪያ ዲግሪውን በኢኮኖሚክስ ሊያገኝ ችሏል። ይህንን ትምህርቱን በሚከታተልበት ውቅት ፥ በአለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ የተዋጣለት ሰው የመሆኑን ምልክት እያሳየ ነበር። አናን በ1961 የባችለር ዲግሪውን በኢኮኖሚክስ ከጨረሰ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ጄኔቫ ፥ ስዊዘርላንድ ፥ በመጓዝ በኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ዲግሪውን አግኝቷል።


  • ቀደምት ሥራ

  አናን በጄኔቫ የድህረ ምረቃ ትምህርቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት አባል ድርጅት የሆነው የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሠራተኞች ሆኖ ተቀጠረ። እንደተቀጠረ አካባቢ የባጀት እና አስተዳዳር መኮንን ሆኖ አገልግሏል። በመቀጠልም በሌሎች የስራ ሃላፊነቶች ወድ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ እና ኒው ዮርክ ከተማ ተዘዋውሮ ሰርቷል። አናን ፥ ምንም እንኳን ፥ በ1970 ዎቹ ውስጥ በአገሩ ጋና አለመረጋጋቶች ተፈጥረው ቢሆንም ከኮሌጅ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገር እንደሚመለስ ያስብ ነበር።


  አናን በማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ የአልፋሬድ ፒ ኤስሎን ፌሎው በመሆን በ1972 ትምህርቱን በማጠናቀቅ በማኔጅመንት የሳይንስ ማስተርስ ዲግሪ አግኝቷል። ከምርቃቱ በህላ ወደ ጋና ከመመለስ ይልቅ በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ለመስራት ወሰነ።


  • ከተባበሩት መንግስታት ጋር ሥራ

  እ.ኤ.አ. በ1974 በተባበሩት መንግስታት የድንገተኛ አደጋ ግብረ ሃይል ውስጥ የሲቪል አዛዥ ሠራተኛ በመሆን ወደ ካይሮ ፥ ግብፅ ተንቀሳቀሰ። አናን በ1974 አ.ም. ለጋናው የቱሪስት ገቢ ልማት ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ለአጭር ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስራቸውን ለቀው ነበር።


  አናን በ1976 አ.ም. እንደገና ወደ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተመለሰ። ለቀጣዮቹ ሰባት ዓመታት በጄኔቫ ከዩናይትድ ስቴትስ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጽ/ቤት ጋር ሰራ። በ1983 በኒው ዮርክ ከተማ ወደሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዋና መሥሪያ ቤት የበጀት አገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን ተመለሰ። ቆይቶ በ1980 ዎቹ ውስጥ በሰብአዊ ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ የዋናው ጸሃፊ ረዳት እና ለተባበሩት መንግስታት የደህንነት አስተባባሪ ሆኖ አገልግሏል። እ.ኤ.አ በ1990 በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ላሉት ለሌላ ዲፓርትመንቶች ፥ የፕሮግራም ዕቅድ ፥ የበጀት እና ፋይናንስ ኦፊሴላዊ ረዳት ሚኒስትር ሆኗል። አናን የተባበሩት መንግስታት በሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ በአብዛኛው በአሜሪካን በተለይም በተባበሩት መንግስታት ዋና መሥሪያ ቤት በኒው ዮርክ ሲቲ አብዛኛውን ጊዜውን አሳልፏል።


  አናን በዚህ ወቅት በተለያዩ የሰላም ማስከበር ስራዎች እና ሌሎች አስተዳደራዊ ህላፊነቶችን ተወጥቷል። የአናን የ1990 ዎቹ ዘመናትም ከዚህ ብዙም ልዩነት የላቸውም። እ.ኤ.አ በ1990 ከኩዌት ወረራ ጋር በተያያዘ ኢራቅ ውስጥ የነበሩ ታጋቾችን ለማስለቀቅ የቻለ ሲሆን ፤ ከአምስት ዓመታት በኋላ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ኃይል (UNPROFOR) ወደ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ድርጅት ሲቀየር ሂደቱን በበላይነት ምርቷል።


  አናን ያለውን ችሎታ በመገንዘብ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ በመሆን እ.ኤ.አ. በታሕሳስ 1996 ተሹሟል። እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 1 ፥ 1997 ለአራት አመት የስራ ዘመን አገልግሎቱን ማገልገል ጀመረ።


  • የተባበሩት መንግስታት መሪ

  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ በዓለም ላይ ካሉት በጣም አስገራሚ ከሆኑት ሥራዎች መካከል አንዱ ሆኗል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድረ ገጽ "የእኩልነት የዲፕሎማሲ እና የመብት ተሟጋች ... ዋና ጸሐፊው የዓለም ህብረተሰብ ፊት እንደ የተባበሩት መንግስታት አምሳያ ይታያል” ዋና ፀሐፊው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የዓለም አቀፋዊ የመንግስት ሰራተኞች አልቃ እና የበርካታ አለምአቀፋዊ የፓርላማ ስርዓት ዋና አስተዳዳሪ ነው።

  በዚህ የስር መደብ ውስጥ አናን እንደ WHO እና የተባበሩት መንግስታት የትምህርት, የሳይንሳዊ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የመሳሰሉ ቡድኖች እንቅስቃሴ የማይቆጣጠር ቢሆንም እንዲያስተባብር ይጠበቅበታል። በተጨማሪም "የቅድሚያ ዲፕሎማሲያዊ ልምድን" እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ይህም እርሱ እና የእሱ ሰራተኞች ዓለም አቀፍ ውዝግብን ለመከላከል ፥ ለመያዝ ወይም ለማቆም መሞከር አለባቸው። ከሁሉም በላይ አናን ዓለም አቀፍ ሰላም ለማስፈን ጥረት ማድረግ አለበት።


  ባንድ ወቅት አናን ለናሽናል ፕሬስ ክለብ በላከው መግለጫ "ጦርነት የዲፕሎማሲ ውድቀት ከሆነ ... ዲፕሎማሲ ... የመጀመሪያው የመከላከያ መስመር ነው። አሁን ያለው ዓለም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለጦርነት ሲያወጣ ፤ አንድ ወይንም ሁለት ቢሊዮን ስለ ሰላም የማያወጣው ለምንድን ነው? "


  • የአናን ሚና

  የአናን ዋና ጸሃፊነት ምርጫ እንደታወቀ፥ የሚከተለው ጥያቄ ትነሳ: - ይህ ሰው ለሥራው በጣም ጥሩ ሰው ነው? የዩኤስ ኒውስ ኤንድ ዎርልድ ሪፖርት እንደገለጸው "ለስላሳ ንግግር ተናጋሪ” መሆኑ እንደ ደካማ ጎኑ ሊቆጠር ይችላል። ሰዎች የአናንን ጥንካሬ ደጋግመው እንዲጠይቁ ያደረገው ሌላው ምክንያት ከ1992 እስከ 1996 ድረስ በተባበሩት መንግስታት በቦስኒያ ሰላም አስከባሪነት ላይ የሰጡት የአመራር ብቃት ነው። በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቦታው ቢኖርም ቦስኒያ የጎሳ ጦርነት (በሃይማኖቶች ወይም በባህላዊ ቡድኖች መካከል) ውስጥ ሆና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሞተዋል። የሰላም ማስከበር መሪ የሆነው ሰር ማርራክ ጎልደን ፥ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል … አናን ስለ የተባበሩት መንግስታት ፖሊሲ በብርቱነት አልተናገረውም። ሆኖም ግን አናን በዚህ አስተያየት ባለመስማማት እንደዚህ ብሏል … በተሳተፉ ሀገራት ማለትም በዩናይትድ ስቴትስ ፥ በብሪታንያ ፥ በፈረንሣይና በሩሲያ ላይ ወታደሮች ወደ ሰላም አስከባሪ ኃይል የመላል ፖሊሲያቸውን እንደገና እንዲያስቡበት አዘውትሮ እንደሚናገር ገልጿል። አናን ድምፁን በንዴት ድምፁን ከፍ አድርጎ ከመናገር ይልቅ ሞቅ ያለ ዲፕሎማሲን መርጧል። በ1998 ባግዳድ ፥ ኢራቅ ውስጥ በተካሄደው የጋዜጠኝነት ስብሰባ ፥ አናን “በዲፕሎማሲ በርካታ ስራዎችን ማከናወን ይቻላል ፥ ነገር ግን በእርግጠኝነት ዲፕሎማሲው በፍትሃዊነት እና በኃይል የተደገፈ ሲሆን የላቀ ተግባራትን ማከናወን ይቻላል።” ብለዋል።

  እ.ኤ.አ. በ1998 አናን የኢራቅን አስከፊ ሁኔታ የተገበሩበት ሁኔታ የብዙሃንን ትኩረት ሳበ። በዚያ ዓመት መጀመሪያ ላይ የጦርነት ማስፈራሪያዎች ሁሉ እውነተኛ መልክ ያዙ። ሳዳም ሁሴን ፥ ምንም እንኳን ቀድመው የተስማሙበት ቢሆንም፥ የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች የተወሰኑ የኢራቅ አካባቢዎችን እንዳይጎበኙ እገዳ ጣሉ። ከዚያ በኋላ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ሳዳም ሁሴን የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎችን እንዲያስገቡ ለማስገደድ ጠንከር ያሉ የማስፈራሪያ ቃላትን ተጠቅመዋል። አናን እንደ ዋና ጸሃፊነታቸው በፌብሩዋሪ 1998 ከኢራቅ መሪ ጋር ለመነጋገር ወደ ኢራቅ ሄዱ። ከአናን ጋር ከተነጋገረ በኋላ ሁሴን ቀድሞ ገደብ ተደርጎባቸው የነበሩትን ስምንት ቦታዎች ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆኑ ወሰነ። በአናን ጣልቃ ገብነት ምክንያት ጦርነትን ማስወገድ ተቻለ።


  • የአናን አዲስ ዓለም

  የአናን ለስላሳ የዲፕሎማሲ መርሆች እ.ኤ.አ. በ 1998 ከሳዳም ሁሴን ጋር ያቀረቡት ንግግር ውጤት ተጠናክሯል። አንዳንዶች የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች ግን ሌላ ቀውስ በለስላሳ ዲፕሎማሲ እና በቆራጡ ጋናዊ ሰው እንዴት እንደሚፈቱ ወደፊት ለማየት ይጓጓሉ።


  በ2001 የበጋ ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኮፊ አናን ለሁለተኛ ጊዜ ለአምስት ዓመት ያህል ዋና ፀሐፊነቱን እንደገና ተሾመ። እ.ኤ.አ. በጥቅምት 12, 2001 የኖቤል የሰላም ሽልማት ለተባበሩት መንግሥታት እና ኮፊ አናን በአንድነት ተሰጥቷል።


  ምንጭ፤

  ታዋቂ ሰዎች


 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መስራች ዲ/ ን ዳንዔል ክብረት ሲሆን አላማው ለኢትዮጵያ በጎ የሰሩ እና ለሌሎች አራያ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማበረታታት እና እውቅና መስጠት ነው። የሚከተለው ሃተታ ከበጎ ሰው ድረ-ገፅ ላይ የተወሰደ ሲሆን የድርጅቱን አላማው ባጭሩ ይገልፃል።

  " የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ኢንዱስትሪያሊስቶች፣ የዲፕሎማሲ ሰዎች፣ ወዘተ የማበረታታት፣ የማድነቅ፣ የመሸለምና ዕውቅና የመስጠት ባህል እምብዛም የለንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የመተቻቸትና የመናናቅ፣ የመመቀኛኘትና የመጓተት ልማዶች ጎልተው ይታያሉ፡፡ ይህንን መሰሉን ባህል ባለማዳበራችን የተነሣ የሚሠሩ ሰዎች ያመጡትን ለውጥ ዐውቀው ይበልጥ እንዲተጉ፣ ሌሎች ደግሞ የእነርሱን አርአያ ተከትለው ለሀገራቸው እንዲሠሩ አላደረግናቸውም፡፡ ትውልዱም የእርሱን ዘመን ጀግኖች እንዳያገኝ ዕንቅፋት ሆኖበታል፡፡ በዚህም የተነሣ የውጭውን አድናቂና ናፋቂ ሆኗል፡፡ ይህንን ልማድ ለመቅረፍና ሀገራዊ ጀግኖችን ለማውጣት፣ ለመሸለምና ትውልዱ እንዲያውቃቸው ለማድረግ መሥራት የመንግሥት ብቻ ኃላፊነት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ሊፈጽመው የሚገባ የዜግነት ግዴታው ነው፡፡ "


                  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መስራች ዲ/ ን ዳንዔል ክብረት

  የበጎ ሰው ሽልማት የተለያዩ ዘርፎችን ያካተተ ሲሆን የሚከተሉት አስር ዋና ዋና የእጩ መጠቆሚያ ዘርፎች ናቸው።

  1. ሰላም:- በዚህ ዘርፍ ለሀገራዊ ሰላም፣ ለሕዝቦች መግባባት፣ ለግጭቶች መፈታት፣ ማኅበረሰቡ ላቅ ያለ ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ የሠሩ ይሸለማሉ

  2. ሳይንስ:- በሕክምና፣ በቴክኖሎጂ፣በፊዚክስ፣ በኬሚስሪ፣ በምሕንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ ወዘተ የሠሩ ይሸለማሉ

  3. ኪነ ጥበብ:- በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች በአዲስ መንገድ፣ በልዩ አቀራረብ፣ የሥነ ጽሑፍን ደረጃ ከፍ ያደረጉ፣ በማኅረሰቡ ዘንድ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሥራ የሠሩ፣ ለኪነ ጥበባችን ዕድገት የተጉ ዜጎች ይሸለማሉ ሀ. ፊልም ለ. ሙዚቃ ሐ. ሥነ ጽሑፍ መ. ቴአትር ሠ. ሥዕልና ቅርጻ ቅርጽ

  4. የበጎ አድራጎት ሥራዎች:- በርዳታና ሰብአዊ አገልግሎት የሠሩ ይሸለማሉ

  5. ግብርና ንግድና የሥራ ፈጠራ:- በንግድ(ቢዝነስ)፣ በግብርና እና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሥራዎች በመፍጠር፣ አዳዲስ የሥራ ሐሳቦችን በማመንጨት የሠሩ ይሸለማሉ

  6. ስፖርት:- በስፖርቱ መስክ አርአያነት ያለውና በጎ ተጽዕኖ የሚያመጣ ሥራ የሠሩ ይሸለማሉ

  7. መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን መወጣት:- በተመደቡበት መንግሥታዊ የኃላፊነት ዘርፍ አርአያ የሚሆን ለውጥ ያመጡና ተገቢውን ሕዝባዊ አገልግሎት የሰጡ

  8. ማኅበራዊ ጥናት:- በማኅበራዊ ጥናት መስክ ተሠማርተው የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ ችግሮች የሚፈቱና አዳዲስ ግንዛቤ የሚያመጡ፣ ዕውቀት የሚጨምሩ ላቅ ያሉ ሥራዎችን የሠሩ ይሸለማሉ

  9. ሚዲያና ጋዜጠኝነት፡ በሚዲያና በጋዜጠኝነት መስክ ለውጥ አምጭና በጎ ተጽዕኖ አሳዳሪ ሥራ የሠሩ ይሸለማሉ

  10.  ቅርስና ባሕል:- ቅርስና ባሕልን በመጠበቅ፣ በማስተዋወቅ፣ በመሰነድና ዓለም ዐቀፍ ዕውቅና እንዲያገኝ በመሥራት ለውጥ ያመጡ ይሸለማሉ፡፡ 
  የሚከተሉት አስራ አምስት ነጥቦች ደግሞ እጩዎችን የመጠቆሚያ መመዘኛዎች ናቸው።

  1. የሚጠቆመው እጩ በሕይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ሰው ወይም ተቋም መሆን አለበት
  2. የምንጠቁማቸው ኢትዮጵያውያን በጎ ለውጥ አምጭ የሆነ ሥራ የሠሩ መሆን አለባቸው፣
  3. የዜጎችን ሕይወት በማሻሻልና ሀገርን በማሳደግ ሊጠቀስ የሚችል ነገር ያከናወኑ መሆን አለባቸው፣
  4. አንድ ሰው በተለምዶ ሊሠራው ከሚገባው ወይም ከሚችለው ሥራ ላቅ ያለ ሰብእና የሚታይበት ተግባር የፈጸሙ መሆን አለባቸው፤
  5. በአሠራር፣ በአስተዳደር፣ በጥናትና ምርምር፣ በኪነ ጥበብና በማኅበራዊ አገልግሎት አዲስ መንገድ ያመላከቱ፣ አዲስ አሠራር የዘረጉ መሆን አለባቸው፣
  6. የሀገርና የሕዝብን ችግር የፈታ ተግባር የከወኑ መሆን አለባቸው
  7. በተሠማሩበት መስክ መሥዋዕትነት ጠያቂ ግዳጅን የተወጡ፣ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን የሰጡ መሆን አለባቸው
  8. ይሁነኝ ብለው የሀገርንና የወገንን ስም የሚያስጠራ፣ ታሪካችንን፣ ባሕላችንን፣ ቅርሳችንን አጉልቶ የሚያወጣ የዜጋ ሥራ የሠሩ መሆን አለባቸው
  9. የማኅበረሰቡን ሞራላዊና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን ለሌሎች መጥፎ ምሳሌ በሚሆን መንገድ ያልጣሱና ለትውልዱ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  10. በተቻለ መጠን ከዚህ በፊት ሥራቸው ሊነገር፣ ሊዘከርና ሊታወቅ ያልቻለ
  11. ለሀገሪቱ ዕድገትና ሥልጣኔ ለውጥ አምጭ አስተዋጽዖ ያደረጉ
  12. ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ብቁ አመራሮችን የሰጡ፣ በአመራሮቻቸውም አካባቢያቸውን፣ ድርጅታቸውንና መሥሪያ ቤታቸውን የለወጡ፣
  13. አዲስ፣ የራሱ ወጥነት ያለውና ያልተደፈረ የሚመስለውን ሥራ ያከናወኑ፣
  14. የሀገሪቱን ክብርና ደረጃ ያስጠበቁ፣ የሀገሪቱንም መብት ያስከበሩ፣
  15. ሀገራቸውን በዓለም አደባባይ በበጎ ያስጠሩ፣ ስሟን ከፍ ያደረጉ

  ምንጭ:
  የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅት ድረ-ገፅ
  http://www.begosew.com/
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በ፳፻፭ ዓ/ ም በአምስት የተለያዩ ዘርፎች ፸ በጎ ግለሰብ ኢትዮጵያውያንን እና ፯ ተቇማትን ጥቆማ በመውሰድ የሚከተሉትን አምስት በጎ ሰዎች ሸልሟል።


                 በትምህርት መስክ - ንቡረ ዕድ ተፈራ መልሴ

  የርእሰ አድባራት አዲስ ዓለም ማርያም አስተዳዳሪ ናቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በትምህርት ያላደረሱት መስክ የለም፤ በሲመትም የታላቋ ደብር አለቃ ሆነዋል፡፡ ይህ እልቅናቸው እንደ ሌሎቹ ቤት ልሥራ፤ ዘር ልዝራ አላሰኛቸውም፡፡ ነገር ግን ሀገራዊ ጉዳይ ያሳስቸው ነበር፡፡ እርሳቸው አረጋዊ ናቸው፤ በእርጅና ጎንበስ ብለው ድካምን የሚጋፉት፤ እርሳቸው በዕድሜ ጣርያ ላይ ያሉ ናቸው፤ ዐርፈው መቀመጥ የሚያስፈ ልጋቸው፤ ግን እንዲህ አላደረጉም፡፡ በዚህ የእርጅና ዕድሜያቸው በመላው ዓለም እየዞሩ፣ እየለመኑና እያባበሉ ኢትዮጵያዊ ዕውቀት የሚገኝባቸው፣ ነገር ግን እንደ ዋልያና ቀይ ቀበሮ በመጥፋት ላይ ያሉት የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጠበቁ፣ ተሻሽለውም እንዲቀጥሉ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማሰባሰብ ተግተዋል፤ ድካም ሳያግዳቸው የሰው ፊት እያዩ ለአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሆን ገንዘብና ቁሳቁስ ሰብስበዋል፡፡ ይቀጥላል ...


                 በሚዲያ እና የሴቶች ኣስተዋጾ -- ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ

  በመረዋ ድምጽ፣ ልብን ሰርሥሮ በሚገባ፣ ቤተኛ በሚያደርግ የቃለ መጠይቅ ጥበብ እንደ መልካም ወገኛ በማጫወት የተካነች ናት፡፡ ለጋዜጠኝነት ሞያ ባላት ፍቅር ኢትዮጵያዊ መልክ ያላቸውን፣ ታሪክና ባህልን የሚያስታውሱንን ታላላቅ ሰዎቻችንን እንድናውቅ የሚያደርጉንን ፕሮግራሞች የሚያቅፍ የሬዲዮ ጣቢያ በመመ ሥረትና በመምራት፣ ታላላቅ ሰዎቻችንን ሞት ሳይቀድመን በፊት ቅርስ ሆነው እንዲቀሩ፣ የማይታወቁ ጀግኖቻችን ለአደባባይ በቅተው እንዲታወቁ በማድረግ፤ አንድ የተለየ ጣዕምና ሚና፣ አንድ የሚደመጥና የሚናፈቅ፣ አንድ ልዩ ቀለምና ጠባይ ያለው የሬዲዮ መሥመር ሸገር ሬዲዮን በመዘርጋት የተዋጣለት ተግባር እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ይቀጥላል...


         በማህበራዊ አገልግሎት -- የመቄዶኒያ አረጋውያንና የዓዕምሮ ህመምተኞች መርጃ ማዕከል መስራች ቢንያም በለጠ

  የ35 ዓመት ወጣት ነው፡፡ አያቱ በጎንደር ከተማ የታወቁ ነበሩ፡፡ ችግረኞችን በመርዳትና ሰው ለሌላቸው ሰዎች መጠጊያ በመሆን ነበር የሚታወቁት፡፡ እንዲያውም የተቸገረ ሰው ላመጣላቸው ሰው ወሮታውን በእህል ይከፍሉ እንደነበረ የከተማው ሰዎች ዛሬም ያስታውሷቸዋል፡፡ አባቱም በዚያው መንገድ ተጓዙና ሰው መርዳት ሆነ ነገር ዓለማቸው፡፡ በወቅቱ የሼል ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አባቱ አቶ በለጠ ደመወዛቸው 4000 ብር ነበር፡፡ በቤት ውስጥ ግን ልጆቻቸው ሽሮ እንኳን አጥተው ጦም የሚያድሩበት ጊዜ ነበር፡፡ ጠጥተውበት አይደለም፣ ቁማር ተጫዉተዉ ተበልተውም አልነበረም፡፡ ለችግረኞች የሚራሩ በመሆናቸው ለድኾች አከፋፍለው ስለሚጨርሱት እንጂ፡፡ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ያፈራል ነውና፤ ይህንኑ በጎ ነገር ልጃቸውም ወረሰው፡፡ ለታክሲ የተሰጠውን ገንዘብ በእግሩና በአውቶቡስ እየተጓዘ በመቆጠብ ችግረኛ ተማሪዎችን ይረዳበት ነበር፡፡ እንዲህ እየኖረና እየተማረ አድጎ አሥራ ሁለተኛ ክፍል አራት ነጥብ አመጣ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ገብቶ ሕግ ተማረ፡፡ ከዚያም ተመርቆ ጥቂት ጊዜ ሠራና አሜሪካ ገባ፡፡ ይቀጥላል ...


                 በኢኮኖሚ መስክ -- ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን

  የአፍሪካ የምግብ ችግር ከምርት ብቻ ሳይሆን ከምርቱ ገበያ ጋር የተያያዘ ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡ በዚህም የተነሣ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች ላይ ሠርተዋል፤ ተመራምረዋል፡፡ በዓለም ባንክ፣ ዋሽንግተን በሚገኘው ዓለም ዐቀፍ የምግብ ፖሊሲ ጥናት ማዕከል፣ እና በተባበሩት መንግሥታትም በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ በኢኮኖሚክስ ዲግሪያቸውን ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ፣ ማስትሬታቸውን ከሚችጋን ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፤ በአፕላይድ ኢኮኖሚክስ ደግሞ ፒ ኤች ዲያቸውን ከስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል፡፡ ለምግብ እህል እጥረት አንዱ ችግር የገበያው ሁኔታ ነው የሚከለውን የጥናት ውጤታቸውን እውን ይዘው ከነ መፍትሔው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ይቀጥላል ...


                 የወጣቱን የንባብ ባህል በማሳደግ -- ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ

  ደራሲ ነው፡፡ ሰባት ያህል መጻሕፍትን አቅርቦልናል፡፡ የተወለደው ወልቂጤ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚከታተልበት ጊዜ ‹ተስፋ› ብሎ በሰየማት አነስተኛ የመጻሕፍት መደብሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ እያከራየ የንባብ ባሕል እንዲዳብር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ እንደ ተከራዮቹ ሞያና የትምህርት ደረጃ ስለ መጻሕፍቱ አጭር ማብራርያ እየሰጠ፤አንብበው ሲመልሱም ስለ መጻሕፍቱ አስተያየት እየተቀበለ ያበረታታ ነበር፡፡ በወልቂጤ ከተማ ውጤታማነትን ለማበረታታት በራሱ ተነሣሽነት በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማቶችን ይሸልማል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሲሆን በዚህ የሥራ ድርሻው አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨትና በመተግበር ደራስያን እንዲጠቀሙ ድርሰትም እንድታብብ እያደረገ ነው፡፡ ይቀጥላል ...

  ምንጭ
  የበጎሰው ድረ-ገፅ እና የዳንዔል እይታ ድረ-ገፅ 
  http://www.begosew.com/index.php/4-2006-winner 
  http://www.danielkibret.com/2014/06/2006_10.html 
  ለሰፊ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል። 
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በ፳፻፮ ዓ/ ም በሰባት የተለያዩ ዘርፎች ከ፻፳ በላይ በጎ ኢትዮጵያውያንን ጥቆማ በመውሰድ የሚከተሉትን ሰባት በጎ ሰዎች ሸልሟል።


                 በባሕል፣ ቅርስና ቱሪዝም ዘርፍ - ሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ

  የሐረር ሸሪፍ ሙዝየም መሥራችና ባለቤት የተማሩት የአካውንቲንግ ሞያ የሠሩት በጭላሎ እርሻ ልማት ቢሆንም የሀገራችን ታሪክና ቅርስ ጉዳይ የሚቆጫቸው ሰው ናቸው፡፡ ከ23 ዓመት በፊት የሐረርን ታሪክ፣ ቅርስ፣ የወግ ዕቃዎች፣ በቁፋሮ የተገኙ ታሪካዊ መረጃዎች፣ መጻሕ ፍትና ሌሎችንም በቤታቸው ውስጥ ማሰባሰብጀመሩ፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ የሚያምናቸውና የሚያከብራቸው አብዱላሂ ሸሪፍ ሕዝቡ ሥራቸውን ተመልክቶ ያገኛቸውንና በእጁ የሚገኙትን መረጃዎችና ቅርሶች ይሰጣቸውነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ቤታቸውን ሙዚየም አድርገው ሲያሰባስቡና ሲያሳዩ የነበሩት አብዱላሂ ሸሪፍ ለሥራው ዋናው የገቢ ምንጫቸውም የራሳቸው ገቢ ነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ሲሠሩበት የነበረው ቤታቸው ‹‹በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግለሰብ የቅርስ ስብስብ›› ተብሎየተመዘገበ ሲሆን በ1990/91 ዓም ወደ ሌላ ቦታ ተዛወረ፡፡ የሼክ አብዱላሂ ሸሪፍ ሙዝየም የሐረር ገዥ የነበሩት ራስ ተፈሪ ወደ ነበሩበት ቤት በ1990/91 ዓም የተዛወረ ሲሆን ዛሬ ይህ ሙዝየም ‹‹ሸሪፍ የሐረር ከተማ ሙዝየም›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ በዚህ ሙዝየም ውስጥ ከ1200 በላይ ጥንታውያን መጻሕፍት፣ ከ400 ሰዓታትበላይ የሚወስዱ ጥንታውያን የድምጽ መረጃዎች፣ ጥንታውያን ሳንቲሞችን፣ ከመካከለኛው ዘመን ጀምረው የነበሩ የጦር መሣርያዎችን፣ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ ፎቶዎችን፣ የሐረርን የንግድ ግንኙነት የሚያሳዩ ሳንቲሞችን፣ መዛግብትን፣ የወግ ዕቃዎችን ሰብስበዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  በኪነ ጥበብ ዘርፍ - ታላቁ የጥበባት ባለ ሀብት ተስፋየ ሣሕሉ 

  ሰኔ 12 ቀን 1916 ዓም ባሌ ውስጥ ከዱ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ የትምህርት ዕድል ያገኙት ወላጆቻቸው ወደ ሐረር ከተዛወሩ በኋላ ነው፡፡ በአሥራ አራት ዓመታቸው አባታቸው አቶ መንበረ ወርቅ ለሚባ ሰው አደራ ሰጥተዋቸው ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡ አሳዳጊያቸውና ቤተሰቦቻቸው በጣልያን ጦርነት በማለቃቸው መጀመሪያ ጫማ በመጥረግ በኋላም በሆስፒታሎች አካባቢ በማገልገል ራሳቸውን ለመደገፍ ሞከሩ፡፡ ከዚያም ደግሞ በእቴጌ ሆቴል(ጣይቱ ሆቴል) ተቀጥረው ሠርተዋል፡፡ እዚሁ ሆቴል ሲሠሩ መጀመሪያ ክራርና ማሲንቆ ቀጥለውም ፒያኖ መጨዋት ጀመሩ፡፡ ከጣልያኖች ጋ በተፈጠረ አለመግባባት ከአዲስ አበባ ሐረር ተላኩ፡፡ እዚያ እያሉ ጣልያን ከኢትዮጵያ ተባረረ፡፡ በሐረርም የራስ ሆቴል የምግብ ቤት ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ በ1934 ዓም በጦርነት ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች ይሰብሰቡ ሲባል አባባ ተስፋዬ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ በዚሁ ዓመትም ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች የሚማሩበት ትምህር ቤት ገብተው መማር ጀመሩ፡፡ ይቀጥላል...


                 በሰብአዊ አገልግሎት ዘርፍ - ዶክተር በላይ አበጋዝ

  ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የልብ ሐኪም ዶክተር በላይ አበጋዝ የተወለዱት ህዳር 13 ቀን 1937 ዓ.ም በደሴ ከተማ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ያጠኑት ደግሞ ሕክምና ነው፡፡ በኋላም በሕጻናት ልብ ህክምና ስፔሻላይዝድ አደረጉ፡፡ ዶክተር በላይ ከ1973 ዓም ጀምረው ላለፉት 30 ዓመታት በሕጻናት ሕክምናና በሕጻናት ካርዲዮሎጂስትነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አገልግለዋል፡፡ ፔዲያትሪክስን በማስተማር፣ ስለ ሞያውም ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማሳተም ይታወቃሉ፡፡ከ1981 ዓም ጀምረው የአሜሪካ ፔዲያትሪክስ አካዳሚ አባል ሲሆኑ፣ በInternational Society of Hypertension in Blacks, The Pan African Society of Cardiology, The National Drug Advisory Board of Ethiopia አባል ሲሆኑ በEthiopian Medical Journal በአባልነት፣ በረዳት ዋና ጸሐፊነትና በሊቀ መንበርነት አገልግለዋል፡፡ ዶክተር በላይ አበጋዝ የማይረዱትና የማያግዙት የዓለም ክፍል የለም ለማለት ያስችላል፡፡ የHealing the Children USA, Save a Child's Heart ISREAL and Chain of Hope UK ተባባሪ ናቸው፡፡ ይቀጥላል...


                  በንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርናና ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ - ቤተልሔም ጥላሁን

  /ሮ ቤተልሔም ጥላሁን ሶል ሪብልስ የተሰኘው በአፍሪካ ታዋቂ ከሆኑት ጫማ አምራቾች አንዱን የመሠረቱና የሚመሩ ሰው ናቸው፡፡ ድርጅቱን የመሠረቱት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2005 ዓም ሲሆን ዋና ተግባሩም ኢትዮጵያ ውስጥ በባሕላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውል ይነበረውን በርባሶ ጫማ በዘመናዊ መንገድ አምርቶ ለዓለም ገበያ ማዋል ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዘነበ ወርቅ አካባቢ ተወልደው ያደጉት ወ/ሮቤተልሔም ጥላሁን በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎች በድህነት ምክንያት ብዙዎቹ ሥራ አጦች መሆናቸውን፤ ነገር ግን ማንም ያልተጠቀመበት ክህሎት ያላቸው መሆኑን በማስተዋል የእነዚህን ወገኖች አቅም ወደ ምርትና ገበያ ለመለወጥ ተነሡ፡፡ በዚህም መሠረት እኤአ በ2004 ዓም ከባለቤታቸውና ከቤተሰቦቻቸው ባገኙት የመነሻ ገንዘብ በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ከሚገኙ ታዋቂ የጫማ አምራቾች አንዱ የሆነውን ሶል ሪብልስ የተሠኘውን ኩባንያ መሠረቱ፡፡ በባሕላዊ መንገድ ይመረቱ የነበረውን የበርባሶን የአመራረት መንገድ በዘመናዊ መልክ በማምጣት ለአካባቢ ብክለት አስተዋጽዖ የማያደርግ፣ ካርቦን ዜሮ የሆነ ጫማ ለማምረት ችለዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ሀገራዊ ሰላምና ዕርቅ - ብጹዕ አቡነ ዮናስ

  ብጹዕ አቡነ ዮናስ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ ወደ አፋር አካባቢ የመጡት በ1972 ዓም ነው፡፡ የሁሉም አባት በመባል በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ የሚጠሩት አቡነ ዮናስ አያሌ የአፋር ልጆችን ፊደል ያስቆጠሩና ለከፍተኛ ማዕረግም ያደረሱ ናቸው፡፡ በተለይም በአፋር አካባቢ ያለው የመጠጥ ውኃ ችግር እንዲቀረፍ ገጠር ወርደው በማስተማር ሕዝቦ ችግሩን ራሱ እንዲቀርፍ አነሣስተዋል፡፡ ለአካባቢው አረጋውያን መኖሪያ 5227 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ እየሠሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 50 አረጋውያን በቦታው ይረዳሉ፡፡ ይህንን የአረጋውያን መርጃ ፕሮጀክት ለመደገፍም 7 ሄክታር መሬት ከመንግሥት ተቀብለው ከጃፓን ኤምባሲ ጋር በመሆን የአካባቢውን ሕዝብ አስተባብረው እያለሙ ናቸው፡፡ ይቀጥላል ...


                 በጥናትና ምርምር ዘርፍ - አምባሳደር ዘውዴ ረታ

  ጋዜጠኛ ዲፕሎማትና ደራሲ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተወለዱ፡፡ ቀድሞ ደጃዝማች ገብረ ማርያም ይባል በነበረውና ኋላ ‹‹ሊሴ ገብረ ማርያም›› ተብሎ በተሰየመው የፈረንሣይ ትምህርት ቤት የመጀመ ሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ከ1948 ዓ.ም እስከ 1952 ዓ.ም በፓሪስ የጋዜጠኝነት ሞያ ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ የሊሴ ገብረማርያምን ትምህርት ለጊዜው አቁመው እያሉ በ1945 ዓ.ም የራዲዮ ዜና አንባቢ ሆነው ሥራ ጀመሩ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አምባሳደር ዘውዴ ረታ በጋዜጠኝነት በዲፕሎማትነትና በመጨረሻም በደራሲነት በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ከ1945 ዓ.ም እስከ 1967 ዓ.ም በጋዜጠኝነት ሙያ በጋዜጣና ማስታወቂያ መሥሪያ ቤት የቤተ መንግሥት ዜና ጋዜጠኛና በራዲዮ ዜና አቅራቢ፣ የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣና የመነን መጽሔት ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ራዲዮ የብሔራዊ ፕሮግራም ዲሬክተር፣ የኢትዮጵያ ወሬ ምንጭ ዋና ዲሬክተር ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል፡፡ ይቀጥላል...


                  መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት - አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ

  አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ለሃምሳ ሁለት ዓመታት አገራቸውን በዲፕሎማሲ መስክ ያገለገሉ አንጋፋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዓመታት አገራችንን ወክለው በተባበሩት መንግሥታት፣ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በአፍሪካ ህብረት በሠሩባቸው ጊዜያት በዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ በሰብዓዊ መብት፣ በስደተኞች፣ ትጥቅ በማስፈታት፣ በጸረኮሎኒያሊዝምና በመሳሰሉት ሰፊ እውቀትና የሥራ ልምድ አላቸው፡፡ እ.አ.አ. በ1962 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዲፕሎማትነት ሥራቸውን የጀመሩት በተባበሩት መንግሥታት መምሪያ ውስጥ ሦስተኛ ጸሐፊ ሆነው ነበር፡፡ ከሦስት ዓመት በኋላ ዕድገት አግኝተው በሁለተኛ ጸሐፊ ማዕረግ ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት እንዲሠሩ ተመደቡ፡፡ በዚህ ኃላፊነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ እ.አ.አ. በ1970 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በቅድሚያ በአፍሪካ መምሪያ ቀጥሎም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ገለልተኛ አገራት መምሪያ ውስጥ በፖለቲካ ኦፊሰርነት ሠርተዋል፡፡ ይቀጥላል...

  ምንጭ:
  የበጎሰው ድረ-ገፅ እና የዳንዔል እይታ ድረ-ገፅ
  http://www.begosew.com/index.php/4-2006-winner
  http://www.danielkibret.com/2014/06/2006_10.html
  ለሰፊ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል።
 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  በኦሮሚያ ወለጋ የተወለደው አብዲሳ የኢትዮጲያን ጦር የተቀላቀለው በ14 አመቱ ሲሆን ጣልያን ኢትዮጲያን ስትወር አገሩን ለመከላከል በሚደረግ ውጊያ ላይ መሳተፍ ጀመረ። እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎች ከታጠቀው የጣልያን ጦር ጋር በሚደረገው ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሱማሊያ በኩል ወደ ሲሲሊ ተወስዶ በጣልያን አገር የጦር እስረኛ ተደረገ።


                  ሻምበል አብዲሳ አጋ

  በእስር ቤት ጠባዎች ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት አብዲሳ እዛው ታስሮ የሚገኝ ሁሊዮ የተባለ የዩጎዝላቪያ ምርኮኛ በጋራ እቅድ በማውጣት ከእስር ቤት ማምለጥ ቻለ። ከእስር ካመለጡ በኋላ ከፋሺስት ጣልያን ወታደሮች በመደበቅ እና በመሸሽ ፋንታ በአብዲሳ መሪነት እና እቅድ አውጪነት በሌሊት ታስረው ወደነበረበት እስር ቤት ተመልሰው ጠባቂዎቹ ላይ ጥቃት በመፈጸም የታሰሩትን እስረኞች በሙሉ ነጻ በማውጣት የኢትዮጲያውያንን ጀግንነት በአድዋ ብቻ ሳይሆን በጣልያን ምድርም ያስመሰከረ ድንቅ ተዋጊ ነበር። የአብዲሳ ጀግንነት በዚህ አላበቃም ከእስር ቤት ያስመለጧቸውን ሰዎች በማሰባሰብ የራሱን ጦር ካደራጀ በኋላ ጣልያኖችን በገዛ አገራቸው ያንቆራጥጣቸው ገባ። ከአድዋ ጀምሮ የኢትዮጲያውያንን ወኔ የተረዱት ጣልያኖች የአብዲሳን ጦር በፍርሃት ያዩ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች ከጣልያን ጦር ጋር በመዋጋት ብዙ ድሎችን እያስመዘገበ ነበር። ቆራጥነቱን የተረዱት ጣልያኖች የሚያረጉት ግራ ቢገባቸው ከበርካታ ስጦታዎች ጋር ጦሩን ይዞ የጣልያንን ሰራዊት እንዲቀላቀል መማጸን ጀምረው ነበር። ለፋሺስት ጦር መዋጋት አገር መክዳት እንደሆነ አስረግጦ የተናገረው አብዲሳ ትግሉን አፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት የሁለተኛው የአለም ጦርነት ተቀሰቀሰ። 

  የተባበሩት የአሜሪካ እና እንግሊዝ መንግስታት ከጀርመን ጋር ያበረችውን ጣልያንን እየተዋጉ በነበረ ሰዓት ስለ አብዲሳ ዝና ከሰሙ በኋላ ለጦሩ የሚገባውን ድጋፍ በማድረግ የፋሺስት ስርዓቱን ለማዳከም ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ሆኗቸው ነበር። በድጋፉ በመጠናከር ፋሺስቱን ሰራዊት ማርበድበድ የቀጠለው አብዲሳ የጣልያን ጦር ተሸንፎ ዋና ከተማዋ ሮም በአሜሪካን እና እንግሊዝ የሚመራ ጦር እጅ ስር ከወደቀች በኋላ የሚመራቸውን ከተለያዩ አገር የወጡ ወታደሮች በሙሉ ክንዳቸው ላይ የኢትዮጲያን ባንዲራ እንዲያስሩ በማድረግ የሃገሩን ባንዲራ እያውለበለበ ሮም ከተማ ሲገባ በአለም አቀፉ ህብረት ጦር ትልቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር። ከዛም በኋላ ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ በመሆን ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታ የጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። 

  ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግስታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። እብዲሳ ግን ኢትዮጲያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ህዝቡን እና መንግስቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ውድቅ አደረገ። በዚህ የተናደዱ ምዕራብውያንም በፈጠራ ወንጀል ከሰው ወደ እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ከተከፈለ በኋላ በክብር ወደ ሃገሩ ሊመለስ ችሏል። ወደ ኢትዮጲያ ከተመለሰ በኋላ ሰራዊቱን በቅንነት ያገለገለው አብዲሳ በኮረኔልነት ማዕረግ የአጼ ሃይለስላሴ ልዩ ጠባቂ ጦር እየመራ ቆይቶ ንጉሱ ከስልጣን ከወረዱ ከጥቂት አመታት በኋላ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

  ምንጭ: 
  • http://thearadaonline.com/2013/03/17/ያልተዘመረለት-ጀግና-አብዲሳ-አጋ/
  • በኢጣልያ በረሃዎች (ሻምበል አብዲሳ አጋ በአርበኝነት ጀብዱ የሰራ ኢትዮጵያዊ ታሪክ)

 • loader Loading content ...
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  አሰላ በድሮው የኢትዮጵያ አወቃቀር የአርሲ ዋና ከተማ ነበረች። በአሁኑ ወቅት ግን አርሲ ክፍለ ሃገር በሁለት ተከፍላለች -- ምዕራብ አርሲ እና ምሥራቅ አርሲ። አሰላ የምሥራቅ አርሲ ዋና ከተማ ስትሆን ሻሸመኔ ደግሞ የምዕራብ አርሲ ዋና ከተማ ነች።
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (13)


 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  እናመሰግናለን መስፍን! በጥይት መገበያየት እንደውም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እንደነበረ እዚሁ ሰዋስው ላይ ዓጼ ምኒልክ ይህንን አስመልክተው ያወጡትን አዋጅ አንብቤያለሁ። የመጀመሪያዎቹ ሁሉት ግን ራቅ ያለ ዘመን ላይ የነበሩ ሳይሆኑ አይቀሩም።
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  አንድ የጓደኛችን ሰርግ ላይ ፉከራ ሲፎከር አይቼ ተመችቶኝ ነበር :) በደህናው ቀን ዝምተኛ የነበሩት ወንዶች ሁሉ እሳት ጎርሰው እሳት ልሰው ሳያቸው ተገርሜ፣ ተገርሜ :)
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የሆነ ወቅት ላይ ይህንን መፅሃፍ በከፊል ለማንበብ ችዬ ነበር። ራስ ካሳ በጊዜያቸው ከነበረው አስተሳሰብ ትንሽ ወጣ የማለት ዝንባሌ ነበራቸው  ለማለት ያስደፍረኛል። ምን ያህሉን ፍልስፍናቸውን በራሳቸው ህይወት ላይ ኖረውታል የሚለውን ባላውቅም።
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  Great poem by Dr. Bedilu! Thanks for bringing it to sewasew, እሸቱ! I also like the explanation by Hon. Dr. Kebede Michael!
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  እናመሰግናለን መስፍን! በገመድ የሚሻገሩት ሰዎች ግን ጉደኞች ናቸው :) ሌላ መሻገሪያ የለም እንዴ?
 • @ቀዮ   1 year ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  እናመሰግናለን ቶላ! ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ሌሎች በርካታ ፅሁፎችም አሏቸው፤ እነዚህን ፅሁፎች በሌላ መጣጥፍ ይዘህ እንደምትመጣ ተስፋ አደርጋለሁ!
 • @ቀዮ   2 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ለ፳፻፮ ዓ/ም በጎ ሰው ሽልማት ዝርዝር ደግሞ ይህንን የሰዋስው መጣጥፍ መመልከት ይቻላል።
  http://www.sewasew.com/phrases/1344?withDetails=1
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቇንቇዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ባሳተመው የመዝገበ ቃላት መፅሐፍ ላይ እንዲህ በሚል ተተርጉሟል።

  ደብተራ ማለት ሁለት ትርጉም ሲኖረው አንደኛው የዜማ፣ ያቇቇም፣ የቅኔ ምሁር ማለት ሲሆን፤ ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ መፃፍ ገላጭ፣ ኮከብ ቆጣሪ በማለት ይፈታዋል።
 • @ቀዮ   3 years ago
  ብልህ እያንዳንዱን አጋጣሚ ከሌሎች ለመማር ይጠቀምበታል!
  ለምሳሌ: የከበቡሽ ልጅ እንደው መስታወቱን አታምነውም! መልኬ ጠፋኝ ነች :)
 • Load more...
loader Loading content ...