loader

Topics (20)


loader Loading content ...

Explanations (20)


 • @Becky   1 month ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ካሞሜል በጣም ጠቃሚ ዕፅዋት፣ ብዙ ጊዜ እንደ እንቅልፍ ጊዜ ሻይ ከመተኛት በፊት እንቅልፍን ለማምጣት ወይም የተቆጣን ጨጓራ ለማስታገስ የሚጠጣ ነው። የካሞሜል ሻይ መጠጫ ውስጥ ያለ ሞቅ ያለ እቅፍ ማለት ነው። ይሁን እንጂ ካሞሜል ከእንቅልፍ ጊዜ ሻይ የበለጠ ጠቀሜታ አለው፤ ትኩሳት፣ እብጠትን፣ ቁስለት(Ulcers)፣የጡንቻ መጫጫን፣ የወር አበባ መዛባት፣ የአጥንት ህመም እና የኪንታሮት በተለምዶ ለማከም ያገለግላል።


  ካሞሜል እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፦ ካሞሜል እንደ ሻይ የተለመደ ሲሆን ግን እንደ አልኮል፣ ማር ወይም ሽሮፕ ተደርጎ ለውጭአዊ ጥቅም ይውላል። በዋናነት ካሞሜል ለዳይፐር ሽፍታ፣ ኩፍኝ፣ የጆሮ ወይም የዓይን ኢንፌክሽን፣ የተዘታ የእንባ ትቦዎችን፣ ለሚቆጠቁጥ የዓይን ህመም እና ለቆዳ ሽፍታ ለማከም ሊያገለግል ይችላል። • loader Loading content ...
 • @Becky   2 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ከስሙ በስተቀር፣ ቃር (Heartburn)  ከልብ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።  አንዳንድ ምልክቶቹ ግን የልብ ድካም ወይም የልብ በሽታዎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ቃር  በጨጓራ  አሲድ  ምክንያት የሚመጣ የesophagus  - የጉሮሮዎ እና ሆድዎን የሚያገናኘ ቱቦ መቆጣት ነው።  ይህ በደረትዎ ቧንቧ ወይም ከደረት አጥንትዎ በታች  ማቃጠል ያስከትላል።


  የቃር  በሽታ  ምክንያቱ ምንድ ነው?

  የቃር ህመም ምልክቶች በታችኛው የጉሮሮዎ እና ሆድዎን የሚያገናኝ ቱቦ  lower esophageal sphincter (LES) የመዝጊያ (muscular valve)ችግር ምክንያት ሊጀምር ይችላል። በተለምዶ፣ በመሬት ስበት እርዳታ፣ (LES) የሆድ ውስጥ አሲድን ባለበት እንዳለ ያቆየዋል። በትክክል ሲሰራ ምግብን በሆድዎ ውስጥ እንዲገባ ይከፍታል ከዚያም እንደገና ይዘጋል። ሆኖም ብዙ ጊዜ የሚከፈት ከሆነ ወይም በደንብ ካልተዘጋ፣ የሆድ ውስጥ አሲድ ወደ ጉሮሮዎ እና ሆድዎን የሚያገናኝ ቱቦ በመፍሰስ የማቃጠል ስሜትን ሊያስከትል ይችላል።


  የእርስዎ (LES) መሆን እንዳለበት​​ የማይጠብቅ ከሆነ ለችግሩ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሁለት ነገሮች አሉ፦. አንደኛው ከልክ በላይ ምግብ መብላት፤ ሌላኛው ደግሞ ከልክ በላይ መወፈር, እርግዝና ወይም የሆድ ድርቀት በመኖሩ ምክንያት በሆድዎ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሲያደርግበት ነው። የተወሰኑ ምግቦችዎ (LES)  እንዳይጠብቅ ወይም የሆድ አሲድ እንዲጨምር ያደርጋሉ።  የሚከተሉትን ጨምሮ፦ ቲማቲም፣ ቆምጣጣ ፍሬዎች፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቀይ ሽንኩርት፣ ቸኮሌት፣ የቡና ወይም የካፌን ውጤቶች፣ አልኮል፣ፔፐርሜትንት፣ አንዳንድ ዘይት እና ቅባቶች (የእንስሳ ወይም የአትክልት) እንደ አንዳንድ መድሃኒቶችም እንዲሁ በከባድ የቃር ህመም ያስከትላል። ጭንቀትና እንቅልፍ ማጣት የሆድ አሲድ  እንዲጨምር  በማድረግ የቃር ህመም ሊያስከትል ይችላል። ነፍሰ ጡር ከሆኑ፣ ፕሮጄስትሮን ሆርሞን  (LES)  እንዲላላ  ስለሚያደርግ የቃር ህመም ሊያስከትል ይችላል። ማጨስ ደግሞ (LES)  እንዲላላ  እና የሆድ አሲድን ይጨምር ያደርጋል።

  የቃር  ህመም  ምን ያህል ይቆያል?

  ሊለያይ ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰዎች ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ሊሆን ይችላል፣ አንዳንድ ጊዜ ለበርካታ ሰዓታት ሊቆይ ይችላል። የቃር ህመም  በሳምንት አንድ ጊዜ እስከ 20% ለሚሆኑ አሜሪካውያን የሚያጋጥም ሲሆ ን  በነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ የተለመደ ነው። አልፎ አልፎ የቃር ህመም  ቢያጋጥም አደገኛ አይደለም።  ይሁን እንጂ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የቃር ህመም   gastroesophageal reflux disease  (GERD) በመባል የሚታወቀው አንዳንዴ ወደ ከባድ ችግሮች ሊያመራ ይችላል፦  የረጅም ጊዜ ሳል፣ የድምጽ መዘጋት (Laryngitis፣ የማቃጠል ወይም የጉሮሮዎ እና ሆድዎን የሚያገናኝ ቱቦ  ቁስለት፣ በጠባብ የጉሮሮዎ እና ሆድዎን የሚያገናኝ ቱቦ  ምክንያት በመዋጥ ችግሮች፣  የጉሮሮዎ እና ሆድዎን የሚያገናኝ ቱቦ ካንሰር የመያዝ ዕድል ከፍተኛ ነው።


 • loader Loading content ...
 • @Becky   3 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  አፄ በካፋ

   

  አፄ በካፋ የቀዳማዊ ወይም የትልቁ ኢያሱ አዲያም ሰገድ ልጅ ናቸው::  አያታቸው አፄ (ፃድቁ) ዮሐንስ፤ ቅድመ አያታቸው ደግሞ አፄ ፋሲል ናቸው:: አፄ በካፋ ስመ-ክርስትናቸው አፅመ-ጊዮርጊስ ሲሆን ስመ-መንግሥታቸው ደግሞ መሢህ ሰገድ አድባር ሰገድ በካፋ ይባላል:: አንዳንድ የአውሮፓ ፀሐፊዎች "በካፋ" የሚለውን ስማቸውን ትርጉም ቆራጥ አንድ ጊዜም ቢሆን ከወሰነ ወደኋላ የማይል የማይራራ ብርቱ ሰው መሆኑን የሚያሣይ ነው ሲሉ ፅፈዋል:: 

  "በካፋ" የሚለው ቃል ምንጩ ግዕዝ ሲሆን ትርጉሙም ቀደም ሲል የተገለፀው ነው:: አፄ በካፋ ወደሥልጣን እስከመጡ ጊዜ ድረስ የኖሩት በወህኒ አምባ ነበር:: በወህኒ አምባ በቆዩባቸው አመታት ቅዱሣት መፅሃፍትን ተምረው፣ የዳዊትን መዝሙራትን ሙሉውን በቃላቸው አጥንተው የበሰለ እውቀት መያዛቸው ተመዝግቧል:: አፄ በካፋ ከሚታወሱባቸው ተግባሮቻቸው አንደኛው ጥፋት ሲሰሩ ለተገኙ ስዎች ያደረጉላቸው ምህረቶች ናቸው:: አፄ በካፋ ከወህኒ አምባ ተጠርተው እንዲነግሡ በተደረገ ጊዜ ራስ ጊዮርጊስ የተባሉ ሰው አቤቶ ወልደጊዮርጊስ ነው መንገሥ ያለበት ብለው የከረረ ተቃውሞ አስነስተው ነበር:: አፄ በካፋ ግን ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለራስ ጊዮርጊስ ይቅርታ አድርገውላቸው ፤ ማደሪያ ቦታ በግዛትነት ሰጥተው ተቃውሟቸውን እንዲያነሱ አድርገው በደስታ አኖሯቸው:: 

  አንድ ጊዜ ደግሞ አፄ በካፋ ውስጥ ውስጡን ጉምጉምታና ተቃውሞ አለ ብለው ገምተው ነበርና የመ ጨረሻውን ውጤት ለማወቅ በመፈለግ በመጀመሪያ "በጠና ታመዋል" ቀጥሎም "ሞተዋል" የሚል ወሬ በመላ ከተማው እንዲነዛ አደረጉ:: በመጨረሻ ከሞት አገር እንደተመለሱ መስለው በመቅረብ "ሞተዋል" በተባለ ጊዜ ደስታ ፈንቅሏቸው ነበር የተባሉትን ሰዎች ሰብስበው ከተግሳፅ ጋር ምህረት ማድረጋቸው ይነገራል:: ለሶስተኛ ጊዜ ደግሞ ጠላታቸው ጃዊ የሚባለው ወረዳ ህዝብ ግብር አንከፍልም ብለው በሸፈቱ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ ምክር ተደርጐላቸው ተማሩ:: ነገር ግን በሚቀጥለውም የግብሩን ጊዜ ጠብቀው ሸፈቱ:: በዚህ ጊዜ የንጉሥ-ነገሥቱ ጦር ዘምቶ አካባቢውን ቁም ስቅሉን ማሳየት ሲጀምር ህዝቡ ተሰብስቦ በለቅሶና በእምባ ምህረትን ጠየቀ:: አፄ በካፋም የተለመደውን ምህረት አደረጉ:: እነዚህ ሶስቱ የምህረት ሥራዎቻቸው በሰባት አመታት የግዛት ዘመናቸው ጊዜ መፈፀሟቸውን በታሪክ ተፅፎላቸዋል:: 

  በአፄ በካፋ ዘመን የማዕከላዊ መንግሥት ሥልጣን እየደከመ የሄደበት ጊዜ ነበር። የአገሪቱን ህልውና ከውድቀት ለማዳን በያካባቢው የነበሩ መሣፍንትን እንቅስቃሴ ነፃነት አውቆ ለመቀበል የተገደዱበት ወቅት ነበር:: አፄ በካፋ በዘመናቸው ካሠሯቸው ቤተ-ክርስቲያናትና የሳቸውንም ሥም ከሚያስጠሩት አንዱ በጐንደር ከተማ መሃል የሚገኘው የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ-ክርስቲያን እንደሆነ ተዕፏል:: የአፄ በካፋ ስም ሲነሣ ከሳቸው ህልፉት በኋላ ገናን ስለ ነበሩት ስለባለቤታቸው እቴጌ ምንትዋብ ሳይወሳ አይታለፍም:: አፄ በካፋ ማንነታቸውን ሳያሳውቁ ወደቋራ በተጓዙ ጊዜ በጠና ታመው በእቴጌ ምንትዋብ ቤተሰብ ቤት ይተኛሉ። አስታመው ያዳኗቸው ግን ወጣቷ ምንትዋብ ነበሩ:: አፄ በካፋም በወጣቷ መልካም ሥራና በቁንጅናዋም ተስበው  ̈ይቺ የኑሮ ጓደኛዬ መሆን አለባት“ ብለው እንዳገቧቸው በታሪክ ተፅፎ ይገኛል:: 

  አፄ በካፋ ከሞቱ በኋላ ከልጃቸው ከዳግማዊ ኢያሱ ጋር ሆነው ብዙ ዓመታትን የሥልጣኑ ተካፋይ ሆነዋል:: የእቴጌ ምንትዋብ ልጅ ቋረኛው ኢያሱ የሚል ስም ተጨምሮላቸው ነበር:: እቴጌ ምንትዋብ እጅግ የተመሰገኑበት ተግባራቸው "ደብረፀሐይ” በሚል የሚታወቀውን ቤተ-ክርስቲያን ገዳም በማሰራታቸው ነው:: ጐንደር ከተማ ሄዶ የአፄ በካፋ ባለቤት እቴጌ ምንትዋብ ያሰሩትን የቁስቋም ቤተ-ክርስቲያን ሳይጐበኝ እና ሳያመሰግን የሚሄድ የለም:: አፄ በካፋ በዘመነ-መንግሥታቸው ከሚታወቁባቸው ቅጣትን ከማቅለል ተግባራቸው ጋር በተያያዘ አንድ ሲፃፍና ሲነገር የኖረ ታሪክ አላቸው:: መሉውን የአፄ ዳዊትን ዘመን በግዞት ወህኒ አምባ ተቀምጠው ኖረው በዙፋን ላይ የተቀመጡት በቅባቶችና በተዋህዶዎች መካከል የተለመደው ኃይማኖታዊ ክርክር ተነስቶ ጠባቸው ወደደም መፋሰስ የደረሰበት ጊዜ ነበር:: በአፄ ዳዊት ዘመን አዛዡ ጃዊ የሚባለው የቅባት ወገን ስለ ነበር የተዋህዶ አማኞችን እያሳደደ ይደበድብ ነበር:: አካለ ጎዶሎም የሚያደርገው እና የሚገለው ሰውም ብዙ ነበር:: አፄ በካፋ በእምነታቸው ከተዋህዶ ወገን ስለሆነ በአፄ ዳዊት ዘመን በደል የደረሰባቸው ሁሉ በደል አድራሾቹን ይበቀልልናል ብለው ጠብቀው እንደነበር በታሪካቸው ተፅፏል:: ይሁን እንጂ የበሰሉ አማካሪዎች ስለነበሯቸው በቀልን ከመፈፀም ተቆጥበዋል:: ሆኖም ግን ጥር 9 ቀን 1719 ዓ.ም. የሁለቱም ፀብ መርምሮ እልባት ለማበጀት ጉባዔ ተደርጐ እንዲከራከሩ ፈቅደው ነበር:: በክርክሩም ተዋህዶዎች ማሸነፋቸው ቢታወቅም ግን በቅባቶች ላይ ምንም ዓይነት የአካል ቅጣት እንዲደርስባቸው አላደረጉም:: ለቅጣቱም መቅለል ከጐናቸው "መብረቅ” እና “ነጐድጓድ” የሚባሉ ሊቆችና የቅኔ አዋቂዎች ስለ ነበሩ የነሱ ምክር ስለተጨመረበት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ:: 

  አፄ በካፋ በዘመናቸው ጐንደር ሩፋኤልንና ደፈጫ ኪዳነ-ምህረትን መትከላቸው በታሪካቸው ተፅፏል። ከዚህም ሌላ የፅህፈት ሆሄያት ተጠብቀው እንዲፃፉ ጥብቅ መመሪያ ወጥቶ በተግባር የዋለው በእሣቸው ዘመን ነው። በመመሪያው መሠረትም አንድ ሰው ሲፅፍ ኣሳስቶ ጥቅም ላይ አውሎ ከተገኘ እጁን እስከ መቆረጥ የሚደርስ ቅጣት ይወሰድበት ነበር።

   

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @Becky   4 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘኢትዮጵያ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ባለቤት እና በአደዋ ጦርነት ከነበሩ የጦር አዛዦች አንዷ ነበሩ:: እቴጌ ጣይቱ ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም. ጐንደር ውስጥ በደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ:: እቴጌ ጣይቱ በአባታቸው ከጐንደር እና ከወሎ በእናታቸው ከጐጃም የሚወለዱ ሲሆን የአፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ እና ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ-ነገሥት ዘኢትዮጵያ በተባሉት እና በሌሎችም መፅሃፍት በዝርዝር ከቀረበው የዘር ሃረጋቸው ለማረጋገጥ እንደሚቻለው ከቅድመ-አያታቸው ጀምሮ ያለው ትውልዳቸው እንዲህ ይቆጠራል:: ትልቁ ራስ ጉግሣ የጐንደሯን ባላባት ወ/ሮ ማሪቱን አግብተው ወ/ሮ ሂሩትን፣ ወ/ሮ ተክሌንና ወ/ሮ አስቴርን ይወልዳሉ:: ወ/ሮ ሂሩት ከራስ ገብሬ እና ከወ/ሮ ሣህሊቱ የሚወለዱትን ደጃዝማች ኃይለማርያምን አግብተው ደጃዝማች ብጡልን፣ ደጃዝማች መርሶንና ሌሎችንም ይወልዳሉ:: ደጃዝማች ብጡል የጐጃም ደብረ መዊዕ ባላባት የሆኑትን ወ/ሮ የውብዳርን አግብተው እቴጌ ጣይቱንና ሌሎችንም ይወልዳሉ:: እቴጌ ጣይቱ የአባታቸው አያት በሆኑት በወ/ሮ ማሪቱ በኩል የአፄ ፋሲል ተወላጅ ከሆኑት ከአፄ ተክለጊዮርጊስ (ፍፃሜ መንግሥት) ይወለዳሉ:: የእቴጌ ጣይቱን የዘር ሃረግ በተመለከተ ዶ/ር መረራ ጉዲና በመጋቢት ወር 1987 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው "ጦቢያ” መፅሄትና ከዚያም በኋላ ባሳተሙት ፅሁፍ አንድም የሚያቀርቡት መረጃ ሳይኖራቸው "እቴጌ ጣይቱ ብጡልና ንጉሥ ሚካኤል ከኦሮሞ ይወለዳሉ" ሲሉ ፅፈዋል:: ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ እንዲህ ያለ ፅሁፍ በማስፈራቸውም በሪሁን ከበደ የአፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ በሚለው መፅሃፋቸው ሰፊ ትችት በማቅረብ እቴጌ ጣይቱም ሆኑ ንጉሥ ሚካኤል የአማራ ተወላጅ መሆናቸውን ፅፈዋል:: የንግሥ ታት ታሪክና የፍቅር ታሪኮች የተባለው መፅሃፍ ደራሲ እንዲሁ የዶ/ር መረራን የተዛባ ፅሁፍ የበለጠ አዛብተው "እቴጌ ጣይቱ ግማሽ የኦሮሞ ዘር ከአላቸው መሳፍንት ቤተሰብ ተወለዱ " ሲሉ ፅፈዋል:: "አንዳንድ ፖለቲከኞች ያልተፈጠረውን ታሪክ እንደ ተፈጠረ አድርገው የሚፅፉት ለምንድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ አስተያየት ሰጭዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ይህንን መሰሉን የማይገባ ተግባር የሚፈፅሙት ትክክለኛው ታሪክ በህዝብ ዘንድ እንዳይታወቅ ሆን ብለው በመጋረድ አዲሱ ትውልድ ትክክለኛው ግንዛቤ እንዳይኖረው ለማድረግ ነው:: ይህን መሰሉን ዓላማ ከሚያራምዱ ወገኖች አስተሳሰብ ውጭ የእቴጌ ጣይቱ ትውልድ በተጨባጭ ሲመረመር ግን ከጐጃም፣ ከጐንደርና ከወሎ የአማራ ብሄረሰብ የወጣ ታሪክ የላቸውም::

  እቴጌ ጣይቱ የ13 ዓመት ጉብል በነበሩ ጊዜ አባታቸው በጦርነት ላይ በመሞታቸው ደብረ ታቦርን ለቀው ወደ እናታቸው አገር ወደጐጃም በመምጣት የእንጀራ አባታቸው በሚያስተዳድሩት እና ደብረ መዊዕ በሚገኘው ደብር ቀደም ሲል ጐንደር ውስጥ በማህደረ-ማርያም ጀምረውት የነበሩትን ትምህርታቸውን እየተማሩ ተቀመጡ:: የአፄ ቴዎድሮስ የአስተዳደር ዘመን እንደተጋመሰ የንጉሠ-ነገሥቱ የወታደር አዛዥ ከነበሩት ከአንዱ መኰንን ጋር ተጋቡ:: የአፄ ቴዎድሮስ ዘመን አብቅቶ የአፄ ተክለጊዮርጊስ ሁለተኛ ዘመን በተተካ ጊዜ ከአፄ ዮሐንስ አራተኛ (ያኔ ደጃዝማች) የጦር አለቆች አንዱን አግብተው ለተወሰነ ጊዜ ወደትግራይ ሄደው ተቀምጠዋል:: በመጨረሻ ባለቤ ታቸው በአፄ ዮሐንስ ተይዘው በታሠሩ ጊዜ እንደገና ወደጐጃም ተመልሰው በሞግዚታቸው እንክብካቤ እየተደረገላቸው በደብረ መዊዕ ደብር ገብተው ቀድሞ ያቋረጡትን ትምህርት ቀጠሉ:: በደብሩ ፅህፈትን፣ ንባብን፣ ግዕዝና የአማርኛ ቅኔን ሲማሩ ከደብሩ ውጭ ደግሞ በገና መደርደርና የሰንጠረዥ ጨዋታን እንደ ተማሩ ከንቲባ ገብሩ ደስታ የኢትዮጵያ ቅርስ በተባለው መፅሃፍ ተፅፏል:: በዚህ መፅሃፍ እንደተብራራው እቴጌ ጣይቱ በደብሩ የሚሰጠውን ትምህርት እንዳጠናቀቁ በሊቃውንቱ በጥንቃቄ ተመርጠው በሚቀርቡላቸው አርዕስተ ነገሮች በጥልቀት እንዲከራከሩ ተደርገው ችሎታቸውን በብቃት አስመስክረዋል::

  እቴጌ ጣይቱ (ያኔ ወ/ሮ) ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በጥበብና በህይወት ፍልስፍና የላቀ ችሎታ ባለቤት መሆናቸው እየታወቀ መጣ:: ፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ እንደፃፉት ይህንን የጣይቱን ዝና ከሰሙ ልዑላን መካከል አንዱ በጐንደር ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር ይኖሩ የነበሩት ወጣቱ ምኒልክ ተጠቃሽ ናቸው:: አቤቶ ምኒልክ ስለ እቴጌ ጣይቱ ዝና የሰሙት አብረው ይኖሩ ከነበሩት አሉላና ወሌ ብጡል ይባሉ ከነበሩት የእቴጌ ወንድሞች ነው:: በወቅቱ የምኒልክ ሞግዚት የነበሩት አቶ ናደው (በኋላ ደጃዝማች) ከሌሎች ቅርብ ሰዎቻቸው ጋር ተማክረው ጣይቱንና ምኒልክን ለማጋባት ሙከራ አድርገው ነበር:: የእቴጌ ዘመዶችም በጉዳዩ ላይ ከመከሩ በኋላ ሁለቱን የነገሥታት ዘሮች እንዲጋቡ ቢያደርጉ የአፄ ቴዎድሮስ ወገኖች በበጐ እንደማይተረጉሙት በማሳወቅ የጋብቻውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ይቀራሉ:: ምኒልክ ሰኔ 24 ቀን 1857 ዓ.ም. ከመቅደላ አምባ አምልጠው ሸዋ ከገቡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የእቴጌ ጣይቱ ወንድሞች ራስ ወሌ (ያኔ ባላምባራስ) እና ልጅ (በኋላ ፊታውራሪ) አሉላ ብጡል ከራስ መንገሻ አቲከም ጋር በመሆን ለንጉሥ ምኒልክ ገቡላቸው:: ንጉሥ ምኒልክ ሸዋ ውስጥ ስልጣናቸውን አደላድለው ወlሮ ባፈናንም አግብተው ለ12 ዓመታት እንደቆዩ ከቀን ወደቀን ዝናቸው እየገዘፈ የሚሰማውን ጣይቱ ብጡልን ለማግባት ውሳኔ ላይ ደረሱ:: ፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴና ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴ በፃፉት ታሪክ እንዳብራሩት ንጉሥ ምኒልክ በሚያዚያ ወር 1869 ዓ.ም. ወደ ባህር ዳር ተጉዘው በእናታቸው በወlሮ የውብዳር ቤት ዘመድ ወዳጅ በታደመበት ከወ/ሮ ጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጩ:: በ1971 ዓ.ም. አለቃ ተክለማርያም ወልደሚካኤል በሚባሉ የንጉሥ ምኒልክ ቅርብ ሰው የሚመሩ ደንገጡሮችና አጃቢዎች ተልከው ከወራት አድካሚ ጉዞ በኋላ ጣይቱን አጅበው ከጐጃም ደብረብርሃን በደረሱ ጊዜ ንጉሥ ምኒልክ የደመቀ አቀባበል አደረጉላቸው:: ንጉሥ ምኒልክ በዚያን ጊዜ ከወ/ሮ ባፈና ጋር የሚያደርጉትን ፍቺ አላጠናቀቁም ነበርና ጣይቱ በወንድማቸው በራስ ወሌ ቤት እንዲያርፉ ተደረገ:: ጋብቻቸው ሳይፈፀምም ለአራት አመታት ቆየ:: የእቴጌ ጣይቱና የንጉሥ ምኒልክ ጋብቻ በፍጥነት እንዳይፈፀም ምክንያት ከሆኑት መካከል በግዛት ይገባኛል ተከታታይ ጦርነቶች ስለነበሩ እና አንዳንድ ወግ አጥባቂ የሸዋ መኳንንት ደግሞ "የእቴጌነቱ ቦታ ተላልፎ ለሰሜኖች መሰጠት የለበትም" የሚል አቋም ይዘው በመከራከራቸው እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች አሉ:: ንጉሥ ምኒልክ ግን እቴጌ ጣይቱን እንዲያገቡ የሚያስገድዷቸው በርካታ ምክንያቶች ስለ ነበሩ በሃሣባቸው ፀኑ::

   - አንደኛው ምክንያታቸው እቴጌ ጣይቱ የተማሩ፣ ብልህና ቆንጆ ሴት ስለነበሩ ነው::

  - ሁለተኛው ምክንያታቸው እቴጌ ጣይቱ በጐጃም፣ በጐንደርና በወሎ ከሚገኙ ታላላቅ መኳንንት የሚወለዱ እና ከትግራይ መኳንንት ጋርም ቤተሰባቸው ከቅድመ-ኢያታቸው ከራስ ገብሬ ዘመን አንስቶ የጋብቻ ዝምድና የፈጠሩ ናቸው:: በዚያም ላይ ቅርብ ቤተሰቦቻቸው በተለይም አባታቸው ራስ ብጡል፣ አያታቸው ደጃዝማች ኃይለማርያም እና ቅድመ-አያታቸው ራስ ገብሬ በመላው በጌምድር (ከፊል ወሎን ይጨምራል) የታወቁ መሪዎች ነበሩ:: የአባታቸው ወንድም ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያምም አማቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እስከ ሚነግሱ ድረስ ሰሜኑን ኢትዮጵያን እስከ ምፅዋ ድረስ ለ34 ዓመታት ገዝተዋል:: ይህን ሁሉ ታሪክ የሚያውቁት ንጉሥ ምኒልክ እቴጌ ጣይቱን ማግባት ማለት ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጋር መዛመድ ማለት መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁ ነበር::

  - ሶስተኛው ምክንያታቸው ደግሞ ከዘመነ-መሳፍንት አንስቶ ትንቢት ነበር:: ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የህይወት ታሪክ በተባለው መፅሃፋ ቸው ይህንኑ ስለእቴጌ ጣይቱ የተነገረውን ትንቢት አስመልክተው ሲፅፉ እንዲህ ብለዋል:: "ጣይቱ በምትባል ሴት የኢትዮጵያ መንግሥት ታላቅ ትሆናለች እየተባለ ሲነገር ይኖር ነበርና ከአፄ ምኒልክ አስቀድሞ የነበሩ አንዳንድ ነገሥታት ስሟ ጣይቱ የምትባል ሴት እየፈለጉ ማግባት ጀምረው ነበር:: ነገር ግን ጊዜው አልደረሰም ነበርና አልሆነላቸውም:: ዘመኑ በደረሰ ጊዜ ግን አፄ ምኒልክ እቴጌ ጣይቱን አገቡ:: እቴጌ ጣይቱም አዕምሯቸው እንደ ወንድ ነበረና በመንግሥቱ ስራ ሁሉ አፄ ምኒልክን ይረዱ ነበር:: እንደንግሩም ቃል ኢትዮጵያ በእቴጌ ጣይቱ ዘመን ታላቅ ሆነች” ብለዋል :: ይህን ሁሉ አጥንተው የሚያወቁት ንጉሥ ምኒልክ ሚያዚያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም. በአንኮበር መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ጋር በቁርባን ጋብቻውን ፈፀሙ:: አምስት ዓመታት ቆይቶም ጥቅምት 27 ቀን 1882 ዓ. ም. ጣይቱ ብጡል እቴጌ ተብለው ተሠየሙ:: በዚህ ጊዜ ንጉሥ ምኒልክ "ንጉሠ-ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ከተባሉ ሶስተኛ ቀናቸው ነበር:: አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በተሰኘው መፅሃፋቸው እቴጌ ጣይቱ ለዚህ ታላቅ ሥልጣን በበቁ ጊዜ የተፈጠረውን ስሜት ሲገልፁ "የሸዋ ቤተ-መንግሥት ዓለሙ የዚህን ቀን ተጀመረ:: የሸዋ ቆሌ፣ የሸዋ ደስታ የዚህን ቀን ተጀመረ:: የሸዋ ቤተ-መንግሥት ከጣይቱ ወዲያ (በኋላ) ውቃቢ ገባው፣ ግርማና ውበት ተጫነው፣ ጥላው ከበደ፣ የእውነተኛው አዱኛ፣ የእውነተኛው ደስታ ከጣይቱ ብጡል ጋር ገባ” ብለዋል :: 

  እቴጌ ጣይቱ አፄ ምኒልክን ካገቡ በኋላ ያልተሳተፉበት ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ የለም:: አፄ ምኒልክ አዳዲስ ሥልጣኔዎችን ለማስገባት ቁርጠኛ አቋም ይዘው በተንቀሳቀሱበት ጊዜ ዋና አማካሪያቸውና አጋራቸው እቴጌ ጣይቱ ናቸው:: በተለይም ዘመናዊ ትምህርት ቤት ሲያቋቁሙ፣ የባቡር ሃዲድ ሲዘረጉ፣ ውሃ በመዘውር እንዲቀዳ ሲያደርጉ፣ በቀጭኑ ሽቦ በስልክ ግንኙነት በተጀመረ ጊዜ፣ ተሽከርካሪዎች ወደአገር ቤት በመጡ ጊዜ፣ የእህል ወፍጮ ሲተከልና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ሁሉን ነገር ከሠይጣን ሥራ ጋር እያያያዙ አፄ ምኒልክን ለመቃወም ከሚነሱ ወገኖች ጋር ቀድመው በግንባር ይጋፈጧቸው የነበሩት እቴጌ ጣይቱ ነበሩ:: እቴጌ ጣይቱ አፄ ምኒልክ በሚታደሙባቸውም ሆነ በማይታደሙባቸው የፖለቲካና የሃይማኖታዊ ክርክሮች ላይ እየተገኙ የመንግሥታቸውን አቋም እያስረዱ ይከራከራሉ:: አፄ ምኒልክ ብዙ ወራት ለሚጠይቁ ዘመቻዎች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የመንግሥቱ አይንና ጆሮ ሆነው አገልግለዋል:: የእቴጌ ጣይቱ ሥም ዘላለም ሲያስጠሩ ከሚኖሩ ተግባሮቻቸው መካከል አዲስ አበባ ከተማን መቆርቆራቸውና መጠሪያ ስሟንም ለመሰየም መቻላቸው ነው:: 

  እቴጌ ጣይቱ የመጀመሪያውን ዘመናዊ ሆቴል መስራቿም እሳቸው ናቸው:: እነ ክሪስ ፕሩቲ እንደፃፉት እቴጌ ጣይቱ የባልትና ሙያንና የሽመናን ጥበብም ለቤተ-መንግሥቱ ሥራ ቤቶች በማስተማር ግንባር ቀደም ነበሩ:: እቴጌ ጣይቱ በፖለቲካዊ ህይወታቸው የሰመረ ሥራ ሰርተዋል ተብሎ ከሚነገርላቸው አንዱ የተራራቁትን ወገኖች በፖለቲካዊ ጋብቻ ለማቀራረብ ያደረጉት ጥረት ነው:: ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ከፃፉት ታሪክ ለመረዳት እንደሚቻለው የሸዋ መኳንንት የሰሜኑን ወገን እንደ ዳር አገር በመቁጠር ከአገራዊ ጉዳይ ሁሉ የማራቅና ብቻቸውን የመወሰን አዝማሚያ ይታይባቸው ነበር:: ይህ ድርጊት ውሎ ካደረ በሸዋና በሰሜኖች መካከል ደም አፋሳሽ ጠብ ውስጥ ሊያስገባቸው ይችላል ብለው የገመቱት እቴጌ ጣይቱ የጐንደርን፣ የጐጃምን፣ የወሎንና የትግራይን መኳንንት ከሸዋ መኳንንትና ወይ ዛዝርት ጋር እያጋቡ ማስተሳሰር ቀጠሉ:: እቴጌ ጣይቱ በፖለቲካዊ ጋብቻ እንዲጣመሩ ካደረጓቸው መካከል ለምሣሌ ቀጥሎ የተጠ ቀሱትን መመልከት ይቻላል ::

  1. የወንድማቸውን ልጅ ራስ ጉግሣ ወሌን ከእንጀራ ልጃቸው ንግሥት (ያኔ ወ/ሮ) ዘውዲቱ ምኒልክ ጋር፣

  2. የወንድማቸውን ልጅ ወ/ሮ ከፈይ ወሌን ከራስ መንገሻ ዮሐንስ

  3. የወንድማቸውን ልጅ ወ/ሮ ከፈይን ከመጀመሪያ ባላቸው ከተፋቱ በኋላ ከራስ ናደው አባወሎ ጋር፣

  4. የወንድማቸውን የልጅ ልጅ ወ/ሮ አስቴር (ፅጌሮማን) መንገሻን (የወ/ሮ ከፈይና የራስ መንገሻ ልጅ) ከልጅ ኢያሱ ጋር አጋብተዋል፣

  5. የወንድማቸውን ልጅ ወ/ሮ ምንትዋብ ወሌን ለራስ መኰንን ወልደ ሚካኤል ድረዋል፣

  6. የእህታቸውን የወ/ሮ ወለተማርያም ብጡልን ልጅ ወ/ሮ አሰለፈች ወንዴን ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ታላቅ ወንድም ለደጃዝማች ይልማ መኰንን ድረዋል:: ከጋብቻውም ልዕልት የሻሸወርቅ ተወልደዋል::

  7. ደጃዝማች ይልማ መኰንን በ1900 ዓ.ም. በሞቱ ጊዜ ወ/ሮ አሰለፈች ወንዴን ለልዑል ራስ ተክለሃይማኖት ድረዋል::

  8. ሌላዋን የወንድማቸውን የልጅ ልጅ ወ/ሮ አልማዝ መንገሻን (የራስ መንገሻ ዮሐንስና የወ/ሮ ከፈይ ወሌ ልጅ) ከልጅ ኢያሱ ቀጥሎ ቅርበት ለነበራቸው ለደጃዝማች ታዬ ጉልላቴ ድረዋል ::

  9. የአፄ ምኒልክ ልጅ ወ/ሮ ሸዋረጋና ንጉሥ ሚካኤል እንዲጋበ ጥያቄ በቀረበ ጊዜ ጋብቻው እንዲፈፀም ትልቁን ሚና ተጫውተዋል::

  10. የእህታቸውን ልጅ ደጃዝማች አያሌው ብሩን፣ ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስን፣ ራስ አባተንና ሌሎች ትልልቅ መኳንንትን ሁሉ ሚስት እያጩ ያጋቧቸው እቴጌ ጣይቱ ናቸው::

  ነጋድራስ ገብረህይወት እንደፃፉት እቴጌ ጣይቱ የሸዋን መኳንንት እና የሰሜን መኳንንትን በጋብቻ ሰንሰለት እንዲቆራኙ አድርገዋል:: እቴጌ ጣይቱ በሚፈፅሙት ተግባር ሁሉ አፄ ምኒልክ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ አድሮባቸው አያውቅም:: አፄ ምኒልክ በክፉውም በበጐውም በሃሣባቸውና በጉልበታቸው ያለመታከት እና ያለመሰልቸት የሚረዷቸውን ባለቤታቸውን እቴጌ ጣይቱን እንደ ሚስት ብቻ ሳይሆን እንደእህትም ይመለከቷቸው ስለነበር "እህተ-ጌ” ብለው በቁልምጫ ይጠሯቸው እንደነበር ታሪካዊ መረጃዎች ያስረዳሉ:: 

  እቴጌ ጣይቱን በፖለቲካዊ ተግባራቸው ዘላለም ሲያመሰግናቸው የሚኖረው ጣሊያኖች በውጫሌ ውል ካሰፈሩት ነጥቦች በአንቀፅ 17 ስር የተቀመጠውን የጣሊያንኛ ትርጉም ኢትዮጵያን በሚጐዳ መልኩ ጥቅም ላይ አውለው በተገኙ ጊዜ የያዙት የማያወላውል አቋም ነው:: አንቶኔሊ የተባለው የጣሊያናዊ ትርጉም ኢትዮጵያን በሚጐዳ መልኩ አዛብቶ ጥቅም ላይ አውሎ በተገኘ ጊዜ የያዙት አቋም ነው:: አንቶኔሊ የተባለው የጣሊያን ዲፕሎማት በቤተ-መንግሥት ተጠርቶ ከአፄ ምኒልክና ከእቴጌ ጣይቱ ፊት ቀርቦ በውጫሌው ውል ከተካተቱት ነጥቦች መካከል በአንቀፅ 17 ሥር የሰፈረውን ትርጉም የሮማ መንግሥት ስህተቱን እንዲያስተካክል በተጠየቀ ጊዜ የአገሩን መንግሥት ክብር የሚነካ ስለ ሚሆን ይህ እንደማይደረግ በግልፅ ተናገረ:: በዚህ ጊዜ እቴጌ "ያንተ ፍላጐት ኢትዮጵያ በሌላ መንግሥት ፊት የኢጣሊያ ጥገኛ መሆኗን ለማሳወቅ ነው:: ነገር ግን ይህን የመሰለው የምኞት ሃሳብ አይሞከርም:: እኔ ራሴ ሴት ነኝ:: ጦርነት አልፈልግም :: ነገር ግን ይህን ውል ብሎ ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ " ሲሉ ተናገሩ:: 

  በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል እሰጥ አገባው ቀጥሎ ከቆየ በኋላ ጦርነቱ አይቀሬ ሆነና አፄ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ወደ አደዋ ጦርነት ሲዘምቱ ኑሯቸውም ሆነ ህልፈታቸው ከባለቤታቸው ሊነጠል እንደማይችል የተገነዘቡት ጣይቱ በራሣቸው የሚመራ 3,000 እግረኛ ጦር እና 6,000 ፈረሰኛ አስከትለው ከባለቤታቸው ጐን ተሰልፈው ውጣ ውረድ የበዛበትን ጉዞ ጀመሩ:: የውጭም የውስጥም ደራሲዎች እንደፃፉት በአደዋ ጦርነት ከጉዞው መነሻ አንስቶ እስከ ጦርነቱ ጊዜ ድረስ እቴጌ ጣይቱ ቀን ከባለ ቤታቸው ጐን ተሰልፈው ለሠራዊቱ፣ ለስንቅና ትጥቅ አቅራቢ ዎችና ለደጀኑ ሁሉ መመሪያ እያወረዱ ሌሊት ደግሞ ያለእረፍት የፀሎት መፅሃፍትን በመድገም ያሳልፉ ነበር:: የአደዋ ጦርነት ከመደረጉ ከጥቂት ቀናት በፊት በእንዳ ኢየሱስ ተከበው የነበሩ የጠላት ወታደሮች የሚጠቀሙበትን ውሃ ለመቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ እቴጌ ጣይቱ ከባለቤታቸውና ከሌሎች የጦር አበጋዞች ጋር ለምክክር ተቀምጠው ነበር:: አፄ ምኒልክም በእቴጌ ጣይቱ ምክር ተስማሙ:: ወዲያው እቴጌ ጣይቱ አሽከሮቻቸውን ጠርተው «እናንተ ከዕርዱ ውስጥ ገብተን ካልተዋጋን በማለት ስትመኙ ነበር:: ነገር ግን ለብዙ ሠራዊት ጥቂት ሥፍራ ስለማይበቃው ከጠላት ተኩስ ይልቅ እርስ በርሳችሁ ትተላለቃላችሁ:: ከውሃው ላይ ሰፍራችሁ ውሃውን እንዳይቀዳ ብትጠብቁ መልካም ነው:: ከጉድጓድ ሄደን እንዋጋለን የምትሉ ከሜዳው ላይ ሞትን እንደ ማትፈሩ ተስፋ አደርጋለሁ» ብለው የማነቃቂያ ንግግር ካደረጉ በኋላ «ይህንን ትዕዛዜን የፈፀመ በህይወት ያለውን እሽልማለሁ ፣ የሞተውንም ተዝካሩን አወጣለሁ፣ ልጁንም አሳድጋለሁ እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ይሁን» ብለው ለግዳጅ ማሰማራታቸውን እራሳቸው ጣሊያኖች ስለ እቴጌ ጣይቱ በፃፉት መፅሃፍ አትተዋል። እቴጌ የሰጡትን አመራር ተከትለውም የቅርብ ወታደሮቻቸው ጠላት ውሃ የሚጠጣበትን ምንጭ በቁጥጥር ስር አዋሉት:: የጠላት ወታደሮችም እጃቸውን መስጠት ብቸኛው የቀረው አማራጫቸው ሆነ:: እቴጌ ጣይቱ የሚመሩት 3,000 እግረኛ ጦር በመቀሌ ጦር ነት ያስመዘገበውን ድል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በተደረገው ትልቁ የአደዋ ጦርነትም በመድገም ትልቅ ጀብዱ ሰራ:: ዋናው ጦርነት ከመደረጉ በፊት ባሻ አውዓሎም የተባሉ ኢትዮጵያዊ የጣሊያን ሰላይ የነበሩ ወደኢትዮጵያ ወታደሮች መጥተው ፈቅ ደው እጃቸውን ሰጡ:: ከአፄ ምኒልክ ፊት ቀርበውም «የጠላት ወታደር ባለብዙ መሣሪያ ነው:: ይልቁንም ባለ ብዙ መድፎች ነው:: አሁን በሚገኝበት ተራራማ ቦታ ላይ እስካለ ድረስ አይቻልም:: እኔ ግን አንድ ነገር ልሰራ አስቤአለሁ እሱ ከዕርዱ እንዲወጣ አደርጋለሁ:: እናንተ ቦታውን እንደለቀቃችሁ አስመስሉ:: ራቅ ብላችሁም አድፍጡ፣ እኔ ወደነሱ ሄጄ የአፄ ምኒልክ ወታደሮች የሚበሉት በማጣታቸው ቦታውን ለቀው ወደኋላ መጓዝ ጀምረዋል ብዬ እነግራቸዋለሁ:: እነሱ ያኔ ቃሌን አምነው እንደሚከተሏችሁ እርግጥ ነው» ሲሉ መላ ያቀርባሉ:: በቀረበው መላ የተደሰቱት አፄ ምኒልክም የእቴጌ ጣይቱን አስተያየት ይጠይቃሉ:: እቴጌ ጣይቱም በእርግጥ ባሻ አውዓሎም አጥባቂ የክርስትና እምነት ተከታይ መሆናቸውን አጣርተው ከተረዱ በኋላ የሚበላ ምግብ አቀረቡላቸው:: እንዲህም አሏቸው «እኔ አሁን የማቀርብልህ ምግብ የእግዚአብሄርን ስም ጠርቼ ነው :: አንተም የእግዚአብሄርን ስም ጠርተህ ሥጋ ወደሙ እንደ ምትቀበል አድርገህ ቁጠረው:: የተናገርከውን ሁሉ በእርግጥ የምትፈፅም መሆኑን ተናግረህ ማልና የቀረበልህን ምግብ ብላ» አሏቸው:: ባሻ አውዓሎምም መሃላውን ፈፅመው የቀረበላቸውን ምግብ ተመገቡ:: ባሻ አውዓሎምም ወደ ጠላት ወታደሮች ተመልሰው ገብተው እንደቃላቸው አደረጉ:: ጦርነቱም ተጀመረ:: ጦርነቱ በተጀመረ ጊዜ እቴጌ ጣይቱ የነበራቸውን ተግባራዊ እንቅሥቃሴ አስመልክተው ፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ ሲፅፉ እንዲህ ብለዋል:: "ጦርነቱ ሊጀመር ሲል እቴጌ ጥቁር ጥላ አሲዘው ዓይነ-ርግብዎን ገልጠው በእግርዎ ሲሄዱ ነበር:: ሴት ወይዛዝሩም የንጉሠ-ነገሥቱም ልጅ ወ/ሮ ዘውዲቱ፣ ደንገጡሮችም ተከትለውዎ ነበር :: የኋላው ሰልፍ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩት ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ:: 'አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል ... ድሉ የእኛ ነው' አሉ:: ጦሩ እቴጌን ባየ ጊዜ ሴት ሲያጠና ወንድ መሸሽ አይሆንለትም እና ፀጥ አለ:: እቴጌም ነፍጠኞችዎን በግራ በቀኝ አሰልፈው በዚያው ቀን እንደ ተመረጠ እንደጦር አርበኛ ሆነው ዋሉ:: የእቴጌም መድፈኞች እቴጌ በቆሙበት በስተቀኝ መልሰው መልሰው መድፍ ሲተኩሱ በመካከል የመጣውን የጣሊያንን ሰልፍ አስለቀቁ" ብለዋል:: 

  እቴጌ ጣይቱ እንደ ፖለቲካውና እንደ ጦር ሜዳው ገድል ሁሉ በሃይማኖታዊ ጉዳይም ያበረከቱት አስተዋፅኦ ብዙ ነው:: እቴጌ ጣይቱ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የዴር ሡልጣን ገዳም ግብፃውያን ያዘጉ ትን ጥንታዊ በር አስከፍተው የፈረሰውን አሰርተውና ያረጀውን አሳድሰው በ1898 ዓ.ም. አስረክበዋል:: በመነኮሳቱ መካከል መከፋፈል በተፈጠረ ጊዜ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ የሚከተለውን ደብዳቤ ፅፈው ላኩ:: "የተላከ ከእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ:: ይድረስ ከማህበር ዴር ሡልጣን ወደብረገነት ዘኢየሩሳሌም:: እንዴት ሰንብታችኋል? እኔ እግዚአብሄር ይመስገን ደህና ነኝ:: እናንተ ብትስማሙ እርስ በርሳችሁ ብትፈቃቀሩ አንድነታችሁን ብታፀኑ ይሻላል እንጂ ትግሬ የብቻ ነው፣ ሸዋ የብቻ ነው፣ በጌምድር የብቻ ነው ፣ ጐጃም የብቻ ነው፣ እያላችሁ ጐሣ እየለያችሁ ብት ጣሉ ምን ትረባላችሁ? እኛስ በኢየሩሳሌም ነገር ይህንን ያህል መድከማችን ያንን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድ እና ከቤቱ የሚገባውን ኪራይ እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ እየበላችሁ ለእኛም የጌታችን ደም ከፈሰሰበት ላይ ዳዊት እንድትደግሙልን፣ እንድታዝኑልንና እናንተም አንድነታችሁን እንዲፀና ብለን ነው እንጂ ገንዘብ ተርፎን፣ በአገራችን በኢትዮጵያ የምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም:: አሁንም ስለእግዚአብሄር ብላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ:: ለእኛም ዳዊት ድገመውልን” ሲሉ ተማጥነዋል:: ከዚሁ ከሃይማኖታዊ ተግባራቸው ጋር በተያያዘ እቴጌ ጣይቱ የእንጦጦ ማርያምን ቤተ-ክርስቲያን በአሠሩ ብጡል በተባለው መፅሃፍ እንደተብራራው የእንጦጦ ማርያም ታቦት የመጣችው ጐጃም ውስጥ የእቴጌ ጣይቱ እናት ከሚኖሩበት ከደብረ መዊዕ ነው:: ንጉሥ ተክለሃይማኖት በእንባቦ ዘመቻ ጊዜ ወደጦር ሜዳ ይዘው ካመጧቸው ፅላቶች አንዷ ናት:: በጦርነቱ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ድል እርቋቸው ቆስለው በተማረኩ ጊዜ ፅላቶቹም አብረው ተያዙ:: ሁኔታው ተረጋግቶ ንጉሥ ምኒልክ ፅላቶችም ወደጐጃም እንዲመለሱ አዘዙ:: በዚህ ወቅት እቴጌ ጣይቱ ከባለቤታቸው ፊት ቀርበው "ታቦቷ የእመቤቴ ፍቃድ ሆኖ ከአያቶቼ መቅደስ ካለሁበት ድረስ ከመጣች ከዚሁ ቤተ ክርስቲያን አሰርቼ እደብራታለሁና ለኔ ትሰጠኝ" ብለው የደብረ መዊዕ ማርያም ፅላት ብቻ እንዲሰጣቸው ጠየቁ:: በጥያቄአቸው መሠረት ተፈቀደላቸውና እቴጌ ጣይቱ በእንጦጦ ተራራ ላይ ህንፃዋ እንዲሠራ መሠረት ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ እግር በእግር ተከታትለው በ1878 ዓ.ም. የቤተ-ክርስቲያኑ ግንባታ ከፍፃሜ ደረሰ:: ህንፃው እንደ ተጠናቀቀ መስከረም 21 ቀን 1878 ዓ.ም. መመረቅ አለበት ብለው አፄ ምኒልክን ገፋፉ:: አፄ ምኒልክ የምረቃው በዓል ክረምቱ ካለፈ በኋላ እንዲደረግ ቢጠይቁም እቴጌ ጣይቱ መስከረም 21 ቀን መሆን አለበት ብለው አጥብቀው በመከራከራቸው ስምምነት ላይ ተደረሰና ዝግጅቱ ቀጠለ:: ሐምሌ 27 ቀን 1988 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው "አዲስ ዘመን" ጋዜጣ ከተፃፈው ታሪክ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በምረቃ በዓሉ ይገኙ ዘንድ በመላ አገሪቱ የሚገኙ አገረ ገዥዎች፣ መኳንንት፣ ሽማግሌዎችና የሃይማኖት ሰዎች ጥሪ ተደረገላቸው:: በዋዜማውም ከመላ አገሪቱ የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ይበቃሉ የተባሉ 5,395 ሰንጋዎች ለእርድ ቀረቡ:: ተቀጣጣይ ዳስም ተጣለ:: ዝግጅቱ ሁሉ ተጠናቆ እንግዶች ከየዳር አገሩ መግባት እንደጀመሩ አፄ ምኒልክ የፈሩት ችግር መጣና በዋዜማው ላይ የክረምቱ ዝናብ የሚያገረሽበት እስኪመስል ድረስ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ:: በቂ መጠለያ ባልተሰራበት የተዘጋጀው ድግስ ሊበላሽ መሆኑን የተገነዘቡት አፄ ምኒልክ ክረምቱ እስኪወጣ ይቆይ ያሉት ይህ ዓይነቱ ችግር እንዳይደርስ በመፍራት መሆኑነ ጠቅሰው እቴጌ ጣይቱን ይወቅሳሉ:: እቴጌ ጣይቱም ይህ ሁሉ ድካም ተደክሞ የተደገሰው ድግስ እንዳይበላሽ እና የንግሥ በዓሉም በእለተ-ቀኗ እንዲደረግ እራሷ እመቤታችን ማርያም የመጣውን ዝናብ ለማስቆም መራዳት እንደሚገባት ለተሰብሳቢዎች ተናገሩ:: አያይዘውም በቀጥታ ለቅድስት ድንግል ማርያም ደብዳቤ መፃፍ እንዳለበት ያስገነዝባሉ:: ወዲያው ፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ ተጠርተው መጥተው "ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም" በሚል ርዕሥ የመጣውን ዝናብ ክብረ-በዓሉ እስኪፈፀም ድረስ እንድትከላከል የመማፀኛ ደብዳቤ ተፃፈ:: የተፃፈውም ደብዳቤ ለቄሰ ገበዙ ከተሰጠ በኋላ በማርያም ምስል ላይ አስቀምጠው ለረጅም ሰዓታት ፀሎት እንዲያደርሱበት ተደረገ:: ፀሎቱ እየተካሄደ እንዳለ እንጦጦና አካባቢዋን የከበባት የደመና ቁልል በኃይለኛ ነፋስ ተጠራርጐ ተወሰደ:: ክብረ-በዓሉም እቴጌ ጣይቱ በፈለጉት ሁኔታ ተፈፀመ:: 

  እቴጌ ጣይቱ በዚህ መልኩ አገራዊ ተልኳቸውን እየተወጡ እያሉ ባለቤታቸው አፄ ምኒልክ በጠና ታመመውና ከህዳር ወር 1902 ዓ.ም. አንስቶ ከቤት ዋሉ:: ጤናቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እንዳወቁም የልጅ ልጃቸውን ልጅ ኢያሱን አልጋወራሽ ብለው ራስ ቢትወደድ ናደውን ሞግዚት አደረጓቸው:: ብዙም ሳይቆይ በራስ ቢትወደድ ተሰማ፣ በአቡነ ማቴዎስ፣ በደጃዝማች ገ/ሥላሴና በሌሎችም መኳንንት ተባባሪነት የሚመራ አድማ ተነሳባቸው:: ጣይቱ ብጡል በተባለው የታደሰ ዘወልዴ መፅሃፍ እንደተገለፀው ራስ ቢትወደድ ተሰማ ፊት ለፊት የመንግሥቱን ሥራ ያለማምዱን እያሉ እየጠየቁ ከበስተጀርባ ደግሞ ባለቤታቸውን ከማስታመም ውጭ በመንግሥቱ ሥራ አይግቡብን እያሉ ይዶልቱ ነበር:: ይህን ከመድረክ በስተጀርባ ያለውን ሴራ በነበራቸው መረጃ ጠንቅቀው የሚያውቁት እቴጌ ጣይቱ ቀደሞ ይዶልቱባቸው የነበሩትን አቡነ ማቴዎስ፣ ደጃዝማች ገ/ሥላሴ ባሪያጋብርንና ራስ ተሰማ ናደውን ብዙ መኳንንት በተሰበሰቡበት እየሰሩ ያሉትን ስህተት በይፋ አንስተው ወቀሷቸው:: ብዙም ሳይቆዩ መኳንንቱ በእቴጌ ላይ የሚያደርጉትን ተቃውሞ አጠናክረው በመቀጠል እና ኃይል ለማሳጣት በሚል ወንድሞቻቸውን እነ ደጃዝማች ብሩንና ራስ ጉግሣ ወሌን፣ አማቾቻቸውን እነደጃዝማች ታዬ ጉልላቴን የእስራት እርምጃ ወሰዱባቸው:: እቴጌ ጣይቱ የየጁ ገዥ ወደነበሩት ወደ ወንድማቸው ወደራስ ወሌ ለመሄድ ይችሉ ዘንድ ጥያቄ ቢያቀርቡም የአካባቢውን ህዝብ በወንድማቸው አስተባባሪነት አነሳስተው ጦርነት ይከፍቱብናል ተብለው ስለተፈሩ ባለቤታቸውን እያስታመ እንዲቀመጡ ወሰኑባቸው:: ታህሳስ 3 ቀን 1906 ዓ.ም. አፄ ምኒልክ አረፉ:: በ1908 ዓ.ም. በልጅ ኢያሱ ትዕዛዝ እቴጌ ጣይቱ በግዞት እንጦጦ ማርያም ወጥተው እንዲቀመጡ ሲደረጉም ዘውዲቱ ምኒልክንም በተመሳሳይ ከከተማ እንዲወጡ አደረጉ:: እቴጌ ጣይቱ አፄ ምኒልክ ከሞቱ በኋላ ከቤተ-መንግሥት እንዲወጡ በተጠየቁ ጊዜ "መከሬን ከትቻለሁ:: እንግዲህ እኔ እዚህ ምን አለኝ ጌታዬ! እኔም በተራዬ እከተልወታለሁ " የሚል ቃል መናገራቸው ተመዝግቧል:: 

  እቴጌ በእንጦጦ በግዞት ቢቀመጡም ልጅ ኢያሱን ጨምሮ ሁሉም መኳንንት የሚገባቸውን ክብር እንዳልነፈጓቸው በህይወት ታሪካቸው ተፅፎ ይገኛል:: የልጅ ኢያሱ ዘመን አብቅቶ ንግሥት ዘውዲቱ መተካታቸው በተነገረ ጊዜ ንጉሥ ሚካኤል ለጦርነት መዘጋጀታቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ መኳንንቱ ወሎ ድረስ ሄደን እንዋጋ ከሚል ውሳኔ ላይ ቢደርሱም ሊያጋጥማቸወ ስለሚችለው አደጋ ለመገመት አልቻሉም ነበርና የእቴጌን ምክር ለመጠየቅ ወደ እንጦጦ ወጡ:: እቴጌም “ጥሩ ምክር አልመክራችሁም:: የወሎ መሬት በተፈጥሮው ምሽግነት አለው:: ብዙ ሰው ታስፈጃላችሁ:: ከዋድላ፣ ከድላንታ ጦር እየተስፋፋ ይወጋችኋል:: እንደምንም ብላችሁ ወደ ሸዋ እንዲመጡ አድርጉ:: ሚካኤል ጀግና ነው:: ግን ችኩል ነው:: ይመጣላችኋል" የሚል ምክር ሰጥተዋል:: 

  ከጥር ወር 1910 ዓ.ም. አንስቶ እንደዋዛ የጀመራቸው ህመም ጠናባቸውና የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ.ም. ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ:: የማረፋቸው ዜና እንደተሰማ በቤተ-መ ንግሥቱ 25 ጊዜ መድፍ ተተኮሰ:: አዲስ አበባ ያሉት መኳንንት በልዑል አልጋወራሽ ተፈሪ መኰንን የሚመራው የጦር ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ተሰልፎ እና የአዲስ አበባ ህዝብ ግልብጥ ብለ ወደ እንጦጦ ማርያም በመወጣት ሥርዓተ ቀብራቸው እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተፈፀመ:: በዕለቱም ከተገጠመላቸው የለቅሶ ግጥም አንዱ እንዲህ የሚል ነበር::

  የኢትዮጵያ ብርሃን እቴጌ ጣይቱ፣

  ስትታኮስ ውላ አድዋ ጦርነት፣

  ታምራት አሳየች ግሩም ድንቅ የሆነ፣

  ያ ሁሉ ቁስለኛ በጥላዋ ዳነ፡፡

  እቴጌ ጣይቱ ቁመው በአሰሩት በእንጦጦ ማርያም ቤተ-ክርስቲያ ቢቀበሩም በኋላ በንግሥት ዘውዲቱ ትዕዛዝ አፅማቸው ፈልሶ መጥቶ ከባለቤታቸው ከአፄ ምኒልክ አፅም ጐን በባዕታ ገዳም እንዲያርፉ ተደርጓል:: እቴጌ ጣይቱ ከሞቱ በኋላ ብዙ ደራሲዎች እየደገፉና እየነቀፉ መፃፋቸውን ቀጥለዋል:: አንዳንድ ፖለቲከኞች እቴጌ ጣይቱ ያራምዱት የነበረው ሰሜነኞችን በአንድነት የማስተባበር ህልምና እሳቸውም የሰሜነኞች በሙሉ የጋራ ጉዳይ ተወላጅ ሆነው መገኘታቸው አደገኛ ነው ብለው ስላሰቡ የእሳቸው ታሪክ የሚጋርድ ክርክር እያነሱ አስተሳሰባቸውን ለማጥቆር ሲጥሩ ይታያሉ:: በእናታቸው እናት በኩል ዝምድና ያላቸው ደጃዝማች ዘውዴ ገ/ሥላሴም አባታቸው የአደዋን ቂም በያዙ ጣሊያኖች ምክር እየተገፉ በእቴጌ ጣይቱ ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ ያደርጉ የነበሩበትን ሁኔታ ሳይመረምሩ በመከተል ባገኙት የመገና ብዙሃን ሁሉ እያጥላሉ ሲናገሩ ተደምጠዋል::

  ወ/ሮ ጊፍቲ አባሲ የተባሉ ፖለቲከኛም በ1997 ዓ.ም. ለሌላ ዓላማ የተሰጣቸውን መድረክ ተጠቅመው ይህ ትውልድ እቴጌ ጣይቱንና ንግሥተ ሣባን እንደ አርአያ ሊቆጥራቸው አይገባም ሲሉ ቀስቅሰውባቸዋል:: ባል ተጨበጠ እና ሃቅነት በሌለው ሁኔታ የእቴጌ ጣይቱን ታሪክ እያዛቡ ለማቅረብ ከሞከሩት ግለሰቦች ይልቅ ትክክለኛ ምግባራቸውን እያወሱ የፃፉ እጅግ የላቀ ቁጥር ያላቸው ናቸው:: የእቴጌ ጣይቱን ታሪክ በከፊልም ሆነ በተሟላ መልኩ ከፃፉት መካከል እነዚህ ይገኛሉ።

  - ፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ ወልደአረጋይ፣

  - ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ፣

  - ነጋድሪስ ገብረህይወት ባይከዳኝ፣

  - ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ፣

  - ብላታ መርስዔ ኃዘን ወልደቂርቆስ፣

  - ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴ፣

  - ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣

  - ጳውሎስ ኞኞ፣

  - በሪሁን ከበደ፣

  - ክሪስ ፕሩቲ ፣

  - ኰሎኔል ዳዊት ገብሩ፣

  - እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም በስም ያልተጠቀሱ ነባርና ወጣት ደራሲዎች የተረዱትን ያህል የእቴጌ ጣይቱን ታሪክ ፅፈዋል:: የሚነዛባቸውን አሉባልታም በመረጃ አስደግፈው አስተባብለዋል:: ከተጨባጩ ታሪክ በተጨማሪ የእቴጌ ጣይቱ ታሪካዊ ተውኔት በጌትነት እንየው ተፅፎ በቶማስ ቶራ ተዘጋጅቶ በአዲስ አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ ለተመልካች በመቅረቡ የሰሩት ገድል በህዝብ ዘንድ የመታወቅ እድል አግኝቷል:: ለተመልካች የመቅረብ እድል ባይኖረውም በ1994 ዓ.ም. የሶስተኛ ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረችው ወ/ት እድገት አየለ ብዙ የታሪክ መፅሃፍትን በማንበብና ታሪካዊ ተውኔት በመፃፍ እቴጌ ጣይቱን ለመዘከር ሞክራለች:: የሚፈለገውን ያህል ባይሆንም እንደ ራሄል ዮሐንስ ያሉ ድምፃውያን በእቴጌ ጣይቱ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ዜማዎችን እያቀናበሩ በማንጐራጐር ገድላቸውን ለአዲሱ ትውልድ ለማሳወቅ ጥረት አድርገዋል::

  ጣይቱ ብጡል በምስል  

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

 • loader Loading content ...
 • @Becky   4 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  አቶ ውብሸት ወርቅአለማሁ የልማዱን እውቀት ከዘመናዊ አጣምረው በመቅሰም አመኔታ የሚጣልበት የማስታወቂያ ሥራ የሚሠሩ ትልቅ ባለመውያ ናቸው:: የአቶ ውብሽት የማስታወቂያ ድርጅት በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የሚያቀርባቸው ማስታወቂያዎች ልዩ የሚያደርጋቸው "ከግነት እንዲያም ሲል ከሸት የፀዱ፣ ግርማ ሞገስ ያልተለያቸውና ተውኔታዊ አቀራረብ የሚንፀባረቅባቸው ስለሆኑ ነው ̈ ሲሉ አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች ብዙ ናቸው :: አቶ ውብሸት ከአባታቸው . ከአለቃ ወርቃለማሁ ወልዴ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ተናኘወርቅ አበሩ በ1936 ዓ.ም. በመንዝና ይፋት አውራጃ ማፉድ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ:: እድሜአቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ደብተራ ሸዋ ለማ የሚባሉ አስተማሪ ተቀጥረውላቸው ለዲቁና ማዕረግ እስኪበቁ ድረስ ተማሩ:: ከስኬት በስተጀርባ በተባለው መፅሃፍ ስለአቶ ውብሸት ታሪክ ከተፃፈው ለመረዳት እንደሚቻለው የማስታወቂያ ሥራ ን የጀመሩት በዚያው ተወልደው ባደጉበት ማፉድ አምሀ ኢየሱስ በተባለ ገበያ ነው:: አዘውረው የሚያሻሽጡትም የቀንድ ከብቶችን ነበር:: የማስታወቂያ ዘዴአቸውም ትኩረት ለመሳብ ቆርቆሮ እያንኳኩ "አዋጅ አዋጅ! ... ያልሰማህ ስማ! ... የሰማህ አሰማ! ... ይኸ ንጋ ጥሩ ነው ... በሽታ የሌለበት ከብት ነው ... ይችን መና የገዛህ እንደሆነ ጮማ ነች! ... ይችን ጥገት ላም የገዛህ እንደሆን ለልጆችህ ወተት ትሰጣለች ... ̈ እያሉ የገዥውን ፍላጐት ማነሳሳት ነበር:: የግብይት ሂደቱ ፍፃሜ ላይ ከደረሰ አንድ ማሪያተሬዛ (ጦገራ) ብር ይከፈላቸው እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል:: "እንደ ላሊበላ እየጮክ የአባትህን ስም ልታስጠፋ ነው ወይ?“ የሚል ግሳፄ ከአያታቸው ባገኛቸው ጊዜ ደግሞ የትውልድ አካባቢያቸውን ለቀው ወደደብረሲና በመሄድ ሲያስተዋውቁ ቆዩ:: ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ልጅ ገብረአምላክ ወርቅለማሁ በተባሉት ወንድማቸው ቤት እየኖሩ በትውልድ ሥፍራቸው በሚገኘው በአብዬ ትምህርት ቤት ጀምረው ያቋረጡትን ዘመናዊ ትምህርት በተስፋ ኮከብ አዳሪ ትምህርት ቤት ቀጠሉ:: እስከ ስምንተኛ ክፍል ከተማሩ በኋላ አቋርጠው በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጦሩ:: 


  በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ቆይታቸውም "ማን ተጋፍቶት፣ ጥጋ በኛ የወገን ደመኛ፣ እኔና ሃያ ሰባቱ ገረዶቼ፣ የጥንቆላ መዘዝ፣ ውለታ በጥፊ፣ ሶስት ለአንድ" የተባሉ ተውኔቶችን በመፃፍ በመድረክና በቴሌቪዥን አቅርበዋል:: በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ቆይታቸው ከደራሲነት በተጨማሪ በአስተዋዋቂነት፣ በተዋናይነትና በፕሮግራም ኦፊሰርነት ሁለገብ አገልግሎት ሰጥተዋል:: በትወና ውያቸውም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን አድናቆትና ሽልማት እስከ ማግኘት ደርሰዋል:: ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እራሳቸው በአብይ ገፀባህሪነት በተሳሉበትና ታሪክ ቀመስ በሆነው የኢዩኤል ዮሐንስ ተውኔት ውስጥ አቶ ውብሸት በተክለ-ሰውነትም ሆነ በቅላት ቀረቤታ ያላቸውን ንጉሠ-ነገሥቱን ወክለው በመጫወታቸው የወርቅ ካባ ለመሸለም በቅተዋል:: በወቅቱ ለከያንያን የሚሰጠው ክብር ዝቅ ያለ ከመሆኑም በላይ ከትልቅ ቤተሰብ መርጦ ለማግባትም ችግር አለበት በሚል የቤተሰቦቻቸውና የዘመዶቻቸው ግፊት ተጨመረበት እና የቲያትር ያን ለመተው ወሰኑ:: ከዚያም የሀገር ፍቅርን ለቀው በብሄራዊ ሎተሪ ውስጥ የማስታወቂያ ሠራተኝነት ተቀጠሩ:: ብዙም ሳይቆዩ  "እማሆይ እንዴት ሰነበቱ? በህልሜ አይቻለሁ እና የሎተሪ ትኬት ይግዙ! ̈ የሚል ማስታወቂያ ይዘው ከህዝብ ፊት ቀረቡ:: እያደርም በሬዲዮና በቴሌቪዥን የሚያቀርቧቸው ማስታወቂያዎች ተወዳጅነትን እያተረፉ መጡ:: አቶ ውብሸት የብሄራዊ ሎተሪን ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቁባት ዥንጉርጉር መልክ ያላት አህያ ነበረቻቸው:: አንድ ሰው ለምሣሌ ሎተሪ በሚደርሰው ጊዜ ብሩን በአህያዋ ላይ ጭነው በፊናንስ ፖሊሶች እንድትታጀብ አድርገው መንገድ ለመንገድ ማስታወቂያ እየሰሩ ከባለዕድለኛው ቤት ድረስ ወስደው ያስረክባሉ:: የአቶ ውብሸት አህያ እንደአንድ የማስታወቂያ ባልደረባ ትታይ ስለነበር ከብሄራዊ ሎተሪ የሚቆረጥላት ወርሃዊ ደመወዝም እንደነበራት ታውቋል:: ከእለታት በአንዱ ቀን ግን ይቺ የማስታወቂያ ክፍል ባልደረባ የሆነችው አህያ በአቶ ውብሸት ላይ ነገር አምጥታባቸው ነበ:: በወቅቱ "የኢትዮጵያ ድምፅ ̈ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበሩት ጳውሎስ ኞኞ  አቶ ብሸት ያገኙትን መረጃ መሠረት በማድረግ ”ብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ያለችው የማስታወቂያ ክፍል አህያ ናት“ በማለት አትመው አወጡ:: ይህ ፅሁፍ በጋዜጣው ታትሞ እንደወጣ በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት 'እኔን ነው በኣሙር አህያ ብሎ የሰደበው ̈ ብለው በንዴት ከንጉሠ-ነገረሥቱ ዘንድ ቀርበው አቤቱታ ያቀርባሉ:: ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይመራና ጉዳዩን የሚያጣራ ኰሚቴ ይቋቋማል:: የኮሚቴው አባላትም ብሄራዊ ሎተሪ ድረስ ሄደው አህያዋ በእርግጥ መኖሯንና የሥራ ድርሻዋንም ከአለቃዋ ከአቶ ውብሸት ጠይቀው ከተረዱ በኋላ ነገሩ ሊቀዘቅዝ መቻሉ ታውቋል:: ሌላም ጊዜ እንደዚሁ በሬዲዮ የሰሩት ማስታወቂያ ጭቅጭቅ አስነስቶባቸው እንደነበር አቶ ውብሸት በሰጡት ቃሉ-መጠይቅ ገልፀዋል:: 


  በመስከረም ወር የተላለፈው የአቶ ውብሸት ማስታወቂያ `ኩኩሉ! ... ተነሱ መስከረም ጠባ፣ ብሄራዊ ተሪ ግዙ፣ 50 ሺህ ብር ማግኘት መተኛት አያስፈልግም፣ የተኛ እንደተራበ ይቀራል፣ ነቅቶ ሎተሪ የገዛ ግን ሀብታም ይሆናል!” የሚል ነበር:: በዚያን ጊዜ የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት ደጃዝማች ግርማቸው ”የንጉሠ-ነገሥቱ ሬዲዮ ጣቢያ እንዲህ መቀለጃ ይሁን?” በሚል ተናደው አቶ ውብሸትን ቢሯቸው ድረስ ያስጠሯቸዋል:: አቶ ውብሸትም ከክቡር ሚኒስትሩ ፊት ቀርበው “የዶሮ ጩኸት የንጋት ምልክት አይደለምን? እኔም ለዚህ ነው ነግቷል ትኬት ግዙ ስል ያስተዋወቅኩት ̈ በማለት ካስረዱ በኋላ በእጆቻቸውን ጭኖቻቸውን መታ መታ አድርገው  ̈ኩኩሉ! ... ተነሱ ደጃዝማች" ብለው ለዛ ያለው ቀልድ በማቅረብ የደጃዝማች ግርማቸው ተክለሃዋርያትን ቁጣ አብርደው ለመመለስ ችለዋል :: 


  የማስታወቂያ ያቸውን በብሄራዊ ሎተሪ ካዳበሩ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሙያ ማሻሻያ ተብሎ የሚሰጠውን የህግ ትምህርት መከታተል ጀመሩ:: በዚህ ወቅት የፊሊፕስ ኩባንያ ባቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት የብሄራዊ ሎተሪን ለቀው በ600 ብር ርሃዊ ክፍያ በሉ ጊዜ ሠራተኝነት ተቀጠሩ:: ለስድስ ዓመታት እንዳገለገሉ ፊሊፕስ የበለጠ የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ በማሰብ ወደሆላንድ ላካቸው:: በሆላንድ በቆዩበት ጊዜ ከየአገሩ የጡ አብረው ይሰለጥኑ የነበሩ የማስታወቂያ ባለሙያዎች የራሳቸው የሆነ ግዙፍ የማስታወቂያ ካምፓኒ መሥራችና ባለ ንብረት መሆናቸውን በመረዳት መንፈሳዊ ቅናት አደረባቸው:: ወደ አገራቸው ተመልሰው በፊሊፕስ ካምፓኒ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ለሶስት ዓመታት እንደሰሩ ለቀው ወጥተው የራሳቸውን የማስታወቂያ ድርጅት አቋቋ:: ፊሊፕስ፣ ኮካኮላ፣ ብሄራዊ ሎተሪንና ማይሌክስ የዱቄት ወተት ድርጅቶችን በደንበኝነት ይዘው መንቀሳቀስ ቀጠሉ:: ይህን የማስታወቂያ ድርጅት ለማቋቋም በተነሱ ጊዜ ብዙ ኩርኮማዎች ደርሰውባቸዋል:: ትልቅ ችግር ያደርሱባቸው ከነበሩት አካላት አንዱ "ስሪ ኤፍ” የሚባል የመንግሥት የማስታወቂያ ድርጅት እንደነበር አቶ ውብሸት ይገልፃሉ:: በግራ ከቀኝ የሚደርስባቸውን ችግር ተቋቁመው በመውያቸው የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በመቻላቸው በአለም ላይ ልዑላን፣ የአገር መሪዎች እና የተለየ የሙያ ችሎታ ያላቸው ምርጥ ሰዎች የሚሸለሙትን "ጐልድ ሜርኩሪ ኢንተርናሽናል አዋርድ“ የተባለውን ሽልማት ለመሸለም በቁ:: "አንበሳ የማስታወቂያና የህዝብ ግንኙነት ድርጅት" በሚል መጠሪያ የሚታወቀው  ድርጅታቸውም በህዝብ ዘንድ ብቃቱን እያስመሰከረ መጣ:: አቶ ውብሸት ባሳለፏቸው የሥራ ዘመናት ሁለት ግዙፍ ችግሮች አጋጥመዋቸዋል:: አንደኛው ባልተመረጡበትና ባልሰለጠኑበት የመርከብ ላይ ንግድ ለመነገድ በተነሱ ጊዜ ያጋጠማቸው የሁለት ሚሊዮን ብር ኪሳራ ሲሆን ሁለተኛው ባልጠበቁት ሁኔታ በአይጥ መርዝ ተመርዘው በሞትና በህይወት መካከል የመገኘት እጣ ፋንታ ነው:: በተለይ ሁለተኛው ችግር ብዙ ቀውስ ፈጥሮባቸው  እንዳለፈ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ:: ከምግብ ጋር በበሉት የአይጥ መርዝ ምክንያት ወደሞት አፋፍ እየተገፉ መምጣታቸውን የተረዱት የኦሪስ ኩባንያ ባለቤት ወደስዊዘርላንድ ሄደው እንዲታከሙ ሁኔታዎችን አመቻቹና በስትሬቸር ላይ ሆነው ወደ ውጭ አገር ተላኩ:: በ17 ዶክተሮች ልዩ ምርመራ ተደርጐላቸው የአይጥ መግደያ መርዝ መብላታቸውን እንዳረጋገጡ በልዩ ህክምና መርዙን ከደማቸው ውስጥ ለማውጣት ቻሉ:: ያም ሆኖ ቀሪውን ህይወታቸውን በዊልቸር ለመገፋት እንደሚገደዱ ተነግሯቸው ወደ አገራቸው ተመለሱ። ወዳገራቸው እንደተመለሱ በጠና መታመማቸውን የተረዱት የሶደሬ መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ምዕመናን ከፍልሰታ ዖም ጋር አያይዘው ሌት ተቀን እንባ እየተራጩ ፀለዩላቸው:: ለአንድ ወር በዚህ ሁኔታ እንደቆዩ ፀሎት ከህክምና ተደምረው በአቶ ውብሸት ጤንነት ላይ ለውጥ መጣ:: ከዊልቸር ወደ ከዘራ ተሸጋገሩ:: ከዚያም እራሳቸውን ችለው መሄድ ጀመሩ:: 


  በመሃሉ ግን የፍች ችግር አጋጠማቸውና ቤታቸውን ሸጠው በጊዮን ሆቴል ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ለመኖር ተገደዱ። ብዙም ሳይቆዩ ግን ሁኔታዎች ሁሉ ተለወጡ:: ጤንነታቸው ሙሉሉ ተመለሰ:: ድርጅታቸው እያንሰራራ መጣ:: በስዊዘርላንድ ለታከሙ በት የኦሪስ ኩባንያ ባለቤት የከፈሉትን 75,000 ብር እዳም ቀስ በቀስ ከፍለው አጠናቀቁ:: ህይወት ወደቀድሞው ሥፍራም ተመለሰች:: አቶ ውብሸት አሁን የታወቁ ሰው ናቸው:: ከተሳማሩበት ያ በተጓዳኝም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ በአዲስ አበባ ወወክማ፣ በባድሜንተን ፌድሬሽን፣ በኢንተርናሽናል አድቨርታይዚንግ አሶሴሽንና በሌሎችም ተቋማት በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት፣ በፕሬዘዳንትነትና በሊቀ-መንበርነት አገልግለዋል:: በማገልገል ላይም ይገኛሉ:: አቶ ውብሸት የማያቋርጥ የዘወትር ፀሎት አላቸው:: ፀሎታቸውም እንዲህ የሚል ነው:: "... ጤንነቴን ስጠኝ፣ የሰው መውደድ ስጠኝ፣ በሰላም አውለኝ፣ ሃጢያቴን ይቅር በለኝ፣ ለዚህ ያበቃኸኝ አምላኬ ሆይ ተመስገን፣ ከክፉ ነገር ሰውረኝ ... የሰጠኸኝን ልጆችና ሃገሬን ባርክ፣ ጠብቅልኝ ”:: አቶ ውብሸት በመጨረሻው ዘመናቸው እንዲሳካላቸው የሚመኙ አንድ ራዕይ አላቸው:: ይህንም ሲያስረዱ “እኔ ራሴን ጠብቄ ሰካራም ሳልሆን፣ ሌባና ወራዳ ሳልሆን ነው የቆየሁት የኢትዮጵያ ህዝብ እኔን በፕሬዘዳንትነት ቢመርጠኝ እሱም አያወላዳ እኔም አላወላዳ:: በልዩ ልዩ ማህበራት ፕሬዘዳንት እየሆንሁ ልምዱን ስላካበትኩ በግማሽ መሳቁንም፣ ማኩረፉንም አቀባበሉንም አውቅበታለሁ:: እንዲያውም የሚሆነኝ ቦታ እሱ ይመስለኛል... ̈ ይላሉ:: ያለባቸውን ደካማ ጐን ሳይቀር ፊት ለፊት ግለ-ሂስ እስከማድረግ የሚደፍሩ ናቸው::


  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ 

   

 • loader Loading content ...
 • @Becky   4 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ጥር 21 ቀን 1939 ዓ.ም. በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሙ ወንፈስ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ:: ነሐሴ 23 ቀን 1995 ዓ.ም. "ከሯጮቻችን በስተጀርባ ያሉት እነማን ናቸው?” በሚል "ምኒልክ ̈ ጋዜጣ ካሰፈረው ታሪካቸው ለመረዳት እንደሚቻለው ዶ/ር ወልደመስቀል እድሜአቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ የቤተ-ክህነት ትምህርት ተምረዋል:: ከዚያም የትውልድ አካባቢያቸውን ለቀው ወደአዲስ አበባ በመምጣት የድሮው አስፋወሰን ይባል በነበረው ት/ቤት በመግባት ተምዋል:: በነበራቸው የእስፖርት ተሳትፎም ት/ቤታቸውን እየወከሉ 400፣ 800 እና 1500 ሜትር ይወዳደሩ ነበር:: ቀጥሎም በመምህራን ማሠልጠኛ ገብተው በእስፖርት ትምህርት በመሰልጠን እንደጨረሱ በዚያው በተማሩበት ት/ቤት በመምህርነት በመሰልጠን እንደጨረሱ በዚያው ሲያገለግሉ ቆዩ:: 

  ዶ/ር ወልደመስቀል 1956 ዓ.ም. የውጭ የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደሀንጋሪ በመሄድ የተማሩ ሲሆን በዚያው አገር ቆይታቸው የሚማሩበትን ኮሌጅ እየወከሉ በ5,000 እና በ 10,000 ሜትሮች መወዳደራቸው ታውቋል:: በ1963 ዓ.ም. በእስፖርት የማስተርስ ዲግሪያቸውን ይዘው ወደ አገራቸው በመምጣት በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እያስተማሩ በተደራቢ በአትሌቲክሱ ዘርፍ የብሄራዊ ቡድኑን ከሚያሠለጥኑ አንዱ በመሆን ሠርተዋል:: በ1966 ዓ.ም. እንደ ገና ወደውጭ አገር በመሄድ ቀደም ሲል በተማሩበት ትምህርት ቤት በመግባት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አገኙ:: በ1973 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በቀድሞው የአካል ማሰልጠኛና ስፖርት ኮሚሽን መ/ቤት ተመድበው ሲሰሩ ቆዩ:: ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአሰልጣኝነት ተመድበው በ800፣ በ1,500፣ በ10,000 እና እንዲሁም በማራቶን እያሰለጠኑ ብዙ አትሌቶችን ለውጤት አብቅተዋል:: ከተጠቀሱት እርቀቶች ሌላ ባለው ውድድር ውጤታማ ለመሆን የሚቻልበትን አቅጣጫ በተመለከተ ዶክተር ወልደመስቀል ሲያስረዱ " ለአጫጭር ሩጫዎች ጅምናዚየም ከተዘጋጀ፣ ክለቦች በአጫጭር ሩጫ ዝግጅት , ማድረጉን ከአሁኑ ከጀመሩ፣ ክልሎች ትኩረት ማድረግ ከቻሉ፣ በተጀመረው የአትሌቲክስ ፕሮጀክት ላይ ሁሉ ትኩረት ካደረገ በአጭር ርቀት ውድ ድሮች መሳተፍ የማይቻልበት ሁኔታ የለም" ብለዋል:: ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ የዓለም ምርጥ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ በመሆን በህዳር ወር 1999 ዓ.ም. በፈረንሣይ አገር በሞናኮ ከተማ ተሸልመዋል:: ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ በአሰል ጣኝነት ከነዶ/ር ይልማ በርታ ጋር በመሆን ዘመናቸው ካፈሯቸው ስመጥር አትሌቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል::

  1. ኃይሌ ገ/ሥላሴ       6. ሚሊዮን ወልዴ

  2. ደራርቱ ቱሉ            7. ፊጣ ባይሳ

  3. ጌጤ ዋሚ             8. ቀነኒሳ በቀለ

  4. አሰፋ መዝገቡ         9. ስለሺ ስህን

  5. ወርቅነሽ ኪዳኔ         10. መሰረት ደፋር እና

            11. ጥሩነሽ ዲባባ ተጠቃሾች ናቸው:: አንድ ወቅት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ስለአስልጣኛቸው ዶ/ር ወልደመስቀል አስተያየት ተጠይቆ ሲመልስ “ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ውጤት ሲገኝም ሲጠፋም አባታዊ አቀራረባቸው አይለወጥም:: እኔ ለርሳቸው ምንጊዜም ልጃቸው ነኝ” ማለቱ ተዘግቧል። 

  / ወልደመስቀል ኮስትሬ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ69 ዓመታቸው ግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡


  ... 2006 አይ...ኤፍ. አሰልጣኝ ሽልማት

  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ

 • loader Loading content ...
 • @Becky   4 months ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ወጋየሁ ንጋቱ በኢትዮጵያ እጅግ አድርጐ ስማቸው ከሚጠራ የመድረክዋንያን አንዱ ነው። ወጋየሁ ከአባቱ ከአቶ ንጋቱ ብዙነህና ከእናቱ ከወ/ አምሳለ በየነ በግንቦት ወር 1936 .. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተወለደ:: ወጋየሁ 1942 .. አካባቢ አቃቂ በሚገኘው የስዊድን ወንጌላዊት ሚሲዮን /ቤት ትምህርቱን ጀመረ:: የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በዳግማዊ ምኒልክ እና በተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤቶች ተከታተለ:: ወጋየሁ በት/ቤት ቆይታው በአንዳንድ የተለዩ አጋጣሚዎች የተሰጥኦ ትርዒት ያቀርብ ነበር:: ከተሰጥኦ ትርዒቶቹ ዋናው የልዩ ልዩ እንስሳትን ድምፅ አስመስሎ ያወጣው የነበረው ይጠቀሳል:: 1955 .. የሁለቱኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አቋቁሞት በነበረው ጥበብ ወትያይባል ወደነበረው የአሁኑ "የባህል ማዕከል” በመግባት ክጓደኞቹ ከአባተ መኩሪያ እና ደበበ እሸቱ ጋር እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ:: በወቅቱ የማዕከሉ ኃላፊ በነበሩት ፍሊፕ ካፕላን አማካኝነትም የትወናን፣ የዝግጅትንና የፅህፈተ-ተውኔትን መሠረታዊ እውቀት ተማረ:: ከዚያም የተማረውን በተግባር በማዋልም በተከታዮቹ ዓመታት ቀጥሎ የተዘረዘሩት ተውኔቶ በዝግጅትና በትወና የላቀ ተሳትፎ አደረገ ::

  - ሮሜውና ጁሌት

  - ጠልፎ በኪሴ

  - የከርሞ ሰው

  - መድሃኒት ቀምሰዋል

  - ዳንዴው ጨቡዴ  

  - የዋርካው ሥር ምኞት

  - ላቀችና ድስቷ በተባሉ ትርጉምና ወጥ ተውኔቶች አብይ ሚናዎችን ይዞ በመጫወቱ ተደናቂ ሆነ:: 

  የቲያትር እውቀቱን ለማጐልበትም ከፍተኛ ጥረት ያደርግ ነበር:: 1959 .. ከደበበ እሸቱ ጋር ወደሀንጋሪ ቡዳፔስት ተልኮ የሥነ-ተውኔት ሙያን ለሁለት ዓመታት አጥንቶ ተመለሰ:: ከሀንጋሪ እንደተመለሰ በሬዲዮና በቴሌቪዥን አጫጭር ተውኔቶችን ማቅረብ ቀጠለ:: በተለይም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለተመልካች እንግዳ የሆኑ "አስማተኛው፣ ቁንጫ፣ ባሉን፣ ቀለም ቀቢው፣ የተዘጋ በርእና የመሳሰሉ ድምፅ አልባ (ማይም) ተውኔቶችን ማቅረብ በመጀመሩ ተደናቂነትን እያተፈ መጣ። 

  1962 .. በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ:: የቲያትር ክፍሉ ኃላፊ፣ አዘጋጅ፣ ተዋናይና እንዲሁም በሙያው ለመስራት የሚፈልጉ ወጣቶችን በማስተማር ሁለጉብ አገልግሎት ሰጠ:: ከዚህ በኋላ ወደኢትዮጵያ ሬዲዮ ተዛወረና በመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢነትና በዜና አንባቢነት ሲሰራ ቆየ:: በዚህ ሥራ ለአራት ዓመታት አገልግሎ በብሄያትር ቤት ተጠረ:: በብሄራዊ ቲያትር ቤት ከተቀጠረበት ጊዜ ኣንስቶም ቀጥሎ በተዘረዘሩት ተውኔቶች አብይ ሚናዎች እየወከለ ተውቷል::

  - የበጋ ሌሊት ራዕይ ፣                - ትግላችን፣

  - ደመ መራራ ፣                       - ደማችን፣

  - ሀሁ በስድስት ወር፣                - ሞረሽ፣

  - አፅም በየገፁ ፣                      - ረ-ኰሎኒያሊስት፣

  - እናት ዓለም ጠኑ ፣                 - የአዛውንቶች ክበብ፣

  - ዋናው ተቆጣጣሪ፣                  - ፍርዱን ለእናንተ ፣

  - ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት፣               - ክራር ሲከር፣

  - ሀምሌት ፣                          - ሊየር ነጋሲ ፣

  - የድል አጥቢያ አርበኛ፣              - ዘርዓይ ደረስ፣

  - ገሞራው ፣                          - አሉላ አባነጋና እና እናት ነሽ ናቸው::

  ከነዚህ ተውኔቶች በአንዳንዶቹ በዋና አዘጋጅነትና በተዋናይነትም ሰርቷል:: ወጋየሁ ንጋቱ ከሚታወቅባቸው ተግባራቱ አንደኛው በሬዲዮ ያቀርብ የነበረው የመፅሃፍት ትረካ ነው:: በመፅሃፍት ዓለም ፕሮግራም በሬዲዮ ከተረካቸውና አድናቆትን ካተረፉለት መፅሃፍት መካከል የሀዲስ አለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር፣ የብርሃኑ ዘሪሁን ሶስት መፅሃት ማዕበል የአብዮት ዋዜማ፣ ማዕበል የአብዮት መባቻ እና ማዕበል የአብዮት ማግስት የተባሉትና የገበየሁ አየለ ጣምራ ጦር ከተደራሲያን አዕምሮ የማይጠፉ ናቸው:: ሀዲስ አለማየሁ መፅሃፋቸው ተተርኮ እንዳለቀ ለወጋየሁ "እኔ ከፃፍኩት ይልቅ አንተ በህዝቡ አዕምሮ የሳልከው ይበልጣል ̈ የሚል የአድናቆት አስተያየት ሰጥተውታል:: በ1966 ዓ.ም. ፀጋዬ ገ/መድህን ከብሄራዊ ቲያትር እንዲነሱ ብዙ የቲያትር ቤቱ ሠራተኞች በተሳተፉበት ሠልፍ ውስጥ ሌላ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው በመደባለቃቸው እንደፀረ-አብዮተኛ ተቆጥሮ ለተወሰኑ ወራት ታስሮ ተፈቷል:: ወጋየሁ በ1977 ዓ.ም. ከባህል ሚኒስቴር ሠራተኞች መካከል ምሥጉን ሠራተኛ ተሰኝቶ ተሸልሟል:: ወጋየሁ ወደመጨረሻው የህይወት ዘመኑ በግልፅ አውጥቶ በማይናገራቸው ጉዳዮች ይበሳጭ እንደነበርና አብዝቶ የመጠጣት ችግርም አጋጥሞት እንደነበር ታውቋል። 

  ህዳር 6 ቀን 1982 ዓ.ም. ባደረበት ህመም ሳቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል::


  ምንጭ:- ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ

   

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ድንቅነሽ (ሉሲ) 3.2 ሚሊዮን ዓመት ያላት የመጀመሪያዋ የሰው ቅሪት አካል ስትሆን በአፋር ውስጥ ሃዳር የተባለ ቦታ ኅዳር 24 ቀን 1974 ዓ.. Donald Johanson, Marice Taieb, Yves Coppens and Tom Gray ተገኘች::


  ሉሲም የተባለችው በዛን ወቅት ተመራማሪዎቹ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ድንቅነሽ ያልናትን የሰው ልጅ ቅሬተ አካል ሲያገኙ በወቅቱ ታወቂ የነበረውን የቢትልስ ሉሲ ኢን ዘ ስካይ ዊዝ ዲያመንድስ የተባለውን ዘፈን እያዳመጡ ነበርና ያገኙትን ቅሬተ አካል ሉሲ ብለው በመሰየም ለዓለም አስተዋወቁ።
  የሉሲ ቅሪተ አካል የሚያሳየው በግዜው ቆማ ትሄድ እንደነበረ ነው።

  ትክክለኛው ቅሪተ አካል በብሔራዊ ሙዚየም ፖሊዎ አንትሮፖሎጂ ላብራቶሪ ይገኛል፡፡

  ምንጭ:- ሪፖርተር ጋዜጣ ህዳር / 2006 እትም 
 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::

  ዕለት፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና  አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ  እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::

  ወር፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::

  ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::

  የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀን 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና  5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::

  የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ  ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::

  ምንጭመስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም

 • loader Loading content ...
 • @Becky   2 years ago
  We all die. The goal isn't to live forever, it's to create something that will.

  የእሬቻ ክብረ በዓል በኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ በዓል ዋነኛው ሲሆን የሚከበረውም በጸደይ በሚጀምርበት ወቅት፤ ከጨለማ ክረምት እና ጎርፍ በሰላም ማለፍ ምክንያት በማድረግ እንደ ምስጋና ነው::  እሬቻ ማለት ለተከበረ ነገር የሚከፈል ዋጋ ማለት ሲሆን ሳር ደግሞ በኦሮሞ ባህል እርጥበቱ ህይወትን የሚያሳይ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው ነገር ነው::

  በዓሉም ወደ መልካ(መልካ ማለት አንድን ወንዝ ጥልቅ ያልሆነ እና አደገኛ እንስሳት የማይገኝበት በቀላሉ ሊሻገሩ የሚችሉት ቦታ) እርጥብ ሳር ይዘው “ማሬ_ሆ” የሚባል ዜማ እያዜሙ ይጓዛሉ፤ እንደደረሱም ያካባቢው የዕድሜ ባለጸጋ ታላቅ የሆነ ሰው ለምርቃት ይጋበዛል:: 

  በድሮ ጊዜ የሚከበርበት ቀን የሚወሰነው አያንቱ በሚባሉ ባህላዊ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ ቀን እና ለሊቱ እኩል የሚሆንበት ቀን ላይ ነበር:: ባሁሉ ወቅት ግን በዘመናዊ ቀን አቆጣጠር በየአመቱ ከመስከረም 19 እስከ 24 ባለው ጊዜ በሚውለው እሁድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ቢሾፍቱ በመሄድ ያከብራሉ::

  ምንጭ:- ከአያንቱ ዜና መስከረም 24/2014

 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (0)


  This user has no comment yet.