loader

Topics (33)


loader Loading content ...

Explanations (31)


 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  This is a very interesting question and I never thought about the difference between these two and the likes of it. My understanding is that the former indicates an action that's still going, while the later indicates an action that has already happened and is complete. For example:

  "ሰዎቹ ለቅሶ ቤት ሄዱ።" ሲባል ሰዎቹ ወደ ለቅሶ ቤት ለመሄድ ጉዞ መጀመራቸውን ይገልፃል እንጂ በእርግጥ ለቅሶ ቤት መድረሳቸውን አያመለክትም። በሌላ በኩል ግን "ሰዎቹ ለቅሶ ቤት ሄደዋል።" ሲባል ለቅሶ ቤት በእርግጥ መድረሳቸውን ያመለክታል።
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  አፄ ምንሊክ በ1882 ዓ.ም. ወደ ትግራይ ደርሰውና ሹም ሽር አድርገው ወደ ሸዋ ከተመለሱ በህዋላ በውጫሌ ውል በ17ኛው ክፍል የተፃፈው ቃል ታርሞ እንዲታደስ ቢሆን ይሻላል እያሉ አሳባቸውን ለኮንት አንቶኔሊ ይነግሩ ነበር:: እርሱ ግን አሳባቸውን የተቀበለ ለመምሰል የኢጣልያም መንግስት ይህ ቃል ታርሞ ቢታደስ ፈቃዱ ነው እያለ የማታለል ቃል ከነገራቸው በህዋላ ምስጢሩ ያልተገለጠ አንዳንድ ምክንያት እየፈለገና እየፈጠረም ስላስቀረባቸው እጅግ ተናደዱ::

  በውጫሌ ላይ በኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስትና በኢጣልያን መንግስት መካከል የተደረገውን ውል ከኢጣልያንኛ ወደ አማርኛ ቇንቇ የተረጎመው በፊት በአስመራ በካቶሊክ ሚስዮን ቤት እየተማረ ያደገ በህዋላ ግን ለአፄ ምኒልክ አገልጋይ የሆነ ግራዝማች ዮሴፍ የሚባለው ነበር::

  በውሉም በ17ኛው ክፍል በኢጣልያንኛ ቇንቇ የተፃፈው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከሌሎች ነገስታት የሚፈልጉትን ጉዳይ ሁሉ በኢጣልያ መንግስት በኩል ለመላላክ ፈቅደዋል ይል ነበር::

  ግራዝማች ዮሴፍ ግን አፄ ምኒልክን በመፍራት ይሁን ወይም የኢጣልያንኛ ቇንቇ አጥርቶ ባለማወቁ ይሁን ምክንያቱ አልታወቀም እንጂ ወደ አማርኛ ቇንቇ ሲተረጉም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከሌሎች ነገስታት የሚፈልጉትን ጉዳይ ሁሉ በኢጣልያ መንግስት አጋዥነት ለመላላክ ይችላሉ ብሎ ተርጉሞት ነበርና አፄ ምኒልክ ለጊዜው ጉዳያቸውን ሁሉ ያውም ግዴታ ሳይኖርባቸው ቢፈቅዱ በኢጣልያ መንግስት አጋዥነት ይልካሉ ማለቱ መስሏቸው ነበር እንጂ የኢጣልያ ጥገኝነት መሆኑን አላወቁም ነበር:: በህዋላ ግን አንዳንድ የውጭ አገር ወዳጆቻቸው የዚህ ትርጉዋሜው ኢትዮጵያ የኢጣልያ ጥገኛ ነች ማለት ነው እያሉ ስለነገሯቸው ይህ 17ኛው ክፍል እንዲሰረዝ መላልሰው ቢጠይቁ የማይሆንላቸው ሆነ::

  ይህም በውሉ በ17ኛው ክፍል የተፃፈው ቃል የኢትዮጵያን ነፃነት የሚነካ ዋና ነገር መሆኑ ከታወቀ በህዋላ በውጭ በያደባባዩ በውስጥም በቤተመንግሥቱ ትልቁም ትንሹም ነገሩን እያነሳ ይነጋገረው ነበርና እቴጌ ጣይቱ በነገሩ ስለተናደዱና ስላዘኑ ከኮንት አንቶሌኒ ጋር ክርክሩ በእልፍኝ በፊታቸው እንዲሆን ከአፄ ምኒልክ አስፈቀዱ::


                 እቴጌ ጣይቱ።

  ኮንት አንቶኔሊም ወደ እልፍኝ ድረስ እየተጠራ እየገባ ብዙ ክርክር ከተደረገ በህዋላ ለ17ኛው የውሉ ክፍል ለውጥ የሚሆን ሌላ የውል አሳብ እንዲያቀርብ ተስማምተው ተለያዩ::

  በማግስቱም ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የውል አሳብ ፅፎ አቀረበ ... የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከመሬቱ አንድ ክፍል ወይም በ17ኛው የውል ክፍል የተባለውን ጥገኝነት ለሌላ ለውጭ አገር መንግስት እንዳይሰጥ ግዴታ የገባ እንደሆነ 17ኛውን ክፍል ለመለወጥ ይቻላል የሚል ነበር::


                 ኮንት አንቶኔሊ።

  በዚያንም ጊዜ አፄ ምኒልክና ልዑል ራስ መኮንን ጥንት አንቶኔሊ ያቀረበው የውል አሳብ መልካም መስሎ ታይቷቸው ነበርና, በዚሁ ለመስማማት ፈለጉ:: እቴጌ ጣይቱ ግን "እኛ ባለፈው ውል ስንፀፀት አሁን እንደገና ከመሬታችን ክፍል ወይም ጥገኝነትን ለሌላ ለውጭ አገር መንግስት ለመስጠት ፍቃድ የለንም:: ነገር ግን ብንሰጥም ባንሰጥም በእኛው ፍቃድ ብቻ ይሆናል እንጂ ኮንት አንቶኔሊ ሊጠይቀን አይገባውም:: እኛም ለዚህ ነገር ግዴታ መግባት አያስፈልገንምና ይህ ቃል በውሉ ውስጥ ሲገባ አይታየኝም::" ብለው አሳባቸውን ገልጠው ተናገሩ::

  ኮንት አንቶኔሊም እቴጌ በተናገሩት ነገር እጅግ ስለተቆጣ "የውሉን አሳብ እቴጌ ፅፈው ያቅርቡና እናየዋለን" ብሎ የድፍረት ቃል ተናገራቸው::

  እቴጌም "እሺ መልካም ነው:: እኛም እንፅፋለን አንተም ሌላ ፃፍና አምጣ" ብለው ተለያሉ::

  በማግስቱም እቴጌ ጣይቱ በውጫሌ ውል በ17ኛው የውሉ ክፍል የተፃፈው ቃል በጭራሽ ተፍቆ ቀርቷል የሚል ቃል ብቻ ፅፈው ቢያቀርቡለት, ለ17ኛው ክፍል ለውጥ ለኢጣልያ መንግስት ጥቅም የሚሆን ሌላ ቃል ካልተጨመረበት የፊተኛው ውል እንደፀና ይቆያል እንጂ አይለወጥም ብሎ ተቆጥቶ ወጣ::

  ወደ ቤቱም ከገባ በህዋላ "አፄ ምኒልክ ስልጣናቸውን ሁሉ ለሴት ለቀው ያላግጣሉ" እያለ ለባልንጀሮቹ ነገራቸው:: ወደ ሮማ ከተመለሰ በህዋላ ግን የእቴጌ ጣይቱን ብርታትና እውቅና እያመሰገነ "እቴጌ ጣይቱ ባይኖሩ አፄ ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ለመሆን ብዙ ችግር ሳያገኛቸው አይቀርም" እያለ ለጉዋደኞቹ ሲናገር ነበር ይባላል::

  በዚያን ጊዜ ለአፄ ምኒልክና ለልዑል ራስ መኮንን የታያቸው በዚህ ምክንያት ጦርነት እንዳይደረግና የሰው ደም እንዳይፈስ ጥገኝነቱ ከቀረልን ለሌላ መንግስት አንሰጥም ብለን ብንዋዋል ጉዳት አይደለም ማለት ነበር::

  ለእቴጌ ጣይቱ የታያቸው ኮንት አንቶኔሊ እንዳቀረበው አሳብ ብንዋዋል ባገራችን የፈቀድነውን ካልሰራን ያው ነፃነትን ማጣት ነው ማለት ነበር:: በዚህም ምክንያት ስምምነት ሳይደረግ ኮንት አንቶኔሊ ወደ ኢጣልያ አገር ተመልሶ ሄደ::

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ ታሪክ (ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል)
  በብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደስላሴ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  የኔፕልስ ልዕልት በመወለዷ ግራዚያኒ የደስታ መግለጫ ገንዘብ እሰጣለሁ ብሎ ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከድሮው ቤተመንግስት ድሆች እንዲሰበሰቡ አዘዘ። ከድሆቹ በስተቀር ታላላቅ የኢጣልያ ሹማምንት፣ የሜትሮፖሊታን ጳጳስ አቡነ ኪርልና ሌሎችም መኩአንንት ነበሩ። ለእያንዳንዱ ድሀም ሁለት ማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር።

  እኩለ ቀን ገደማ ላይ 3000 የሚሆኑ ድሆች ከቤተ መንግስቱ ገቡ። ወዲያው በግቢው በር በኩል አንድ ቦምብ ፈነዳ። ቀጥሎም ሌላ ፈነዳ። ለሶስተኛ ጊዜ የተጣለው ቦምብ የፋሺስት ኢጣልያ መክዋንንት ካሉበት ቦታ ፈነዳ። ግራዚያኒ ጀርባውን ቆስሎ ወደቀ። በቀጠለው ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሌሎች ቦምቦች ተከታትለው ተጣሉ። በጠቅላላው በግቢው ውስጥ ሰባት ቦምቦች ፈነዱ። ጄኔራል ሊታዩ፣ የአዲስ አበባው ከንቲባ ጉይዶ ኮርቴሲ፣ ጋዜጠኛው ማርዮ አፔሎስ እና ሌሎች 30 ያህል ሰዎች ቆሰሉ። የቦምቡ ፍንዳታ ጋብ እንዳለ አድፍጠው ተኝተው የነበሩ ወታደሮች ተነስተው ተኩስ ከፈቱ። በዚያ ግቢ ውስጥ ያለማቁዓረጥ ሶስት ሰዓት ሙሉ ተኩስ ተካሄደ።

  ከጥቂት ጊዜ በህዋላ ባለ ጥቁር ሸሚዞች፣ የኢጣሊያ ሾፌሮች፣ የቅኝ ግዛት ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ እየዞሩ ሕዝቡን ይፈጁት ጀመር።

  አንጄሎ ዴል ቦካ በመፅሐፉ "... በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖር አንድ ኢጣልያዊ ወዳጄ ሲኞር ዲ ስሜን አትግለጥብኝ ብሎ እንዲህ ሲል አጫወተኝ። አየህ፣ የዚያን እለት ብዙ ኢጣልያኖች ብዙ ሥራ ሰርተዋል። ወደማታ ገደማ ካንድ ጉዋደኛዬ ጋር ስንገናኝ ያ ጉዋደኛዬ ቦምብ ስጥል የዋልኩበት እጄ ዝሏል ብሎ ነገረኝ። አንዱ ኢጣልያዊ ሲያጫውተኝ ባንዲት ትንሽ ጣሳ በያዝክዋት ቤንዚን አስር ቤቶች አቃጠልኩባት አለኝ። በዋናው የጦርነት ጊዜ ጥይት ተኩሰው የማያውቁ ኢጣልያውያኖች ሁሉ በዚያን ቀን ሲተኩሱ ዋሉ ስል አጫወተኝ..." በማለት ፅፏል።

  አዲስ አበባ የነበረው የሃንጋሪው ሀኪም ዶክተር ላድስላስ ሳቫ ደግሞ "... ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሰላም እና በፍቅር ከቤተ መንግስቱ ግቢ ተሰበሰቡ። ጥቂት ቆይቶ ግራዚያኒና መክዋንንቱ ከጠቀመጡበት ጠረጴዛ አጠገብ ቦምቦች ተወረወሩ። ቦምቡ እንደተጣለ ግራዚያኒ ጠረጴዛው ስር ተደበቀ። ሌሎች ኢጣልያኖች ግን ከመሬት ተኙ። ቦምቡን የጣለው በኢጣልያኖቹ ዘንድ በአስተርጉዋሚነት የሚሰራ የኤርትራ ክፍለ ሃገር ተወላጅ ነው።"
   
  "ለጥቂት ጊዜ ፀጥ አለ። ኢጣልያኖቹ ሌላ የሚወረወር ቦምብ እንደሌለ ካወቁ በህዋላ ከተኙበት ተነሱ። ወዲያው ካርቴሲ ወደ ኢትዮጵያውያን መክዋንንት ሽጉጡን አነጣጥሮ የመጀመሪያዋን አንድ ጥይት ተኮሰ። ካራቢኔሪዎችም ምሳሌውን ተከተሉ። በጥቂት ጊዜ ውስጥም በዚያ ግቢ 300 ሬሳዎች ተከመሩ።"

  "ኃይለኛና ተገቢ ያልሆነ ጭፍጨፋ ነበር። ሽማግሌዎች፣ እውሮች፣ እግር የሌላቸው ለማኞች፣ ድሆች እናቶች ከነልጆቻቸው ነበሩበት። ባለጥቁር ሸሚዞች በግቢው እየተሯሯጡ በሕይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ይፈልጉ ነበር። ከሬሳዎቹ መሀልም የሚተነፍስ ካለ እያሉ እየመረመሩ ይገድሉ ነበር። ከጥቂት ደቂቃዎች በህዋላ ባለጥቁር ሸሚዞች፣ ካራቤኔሮዎችና የጦር ወታደሮች በከተማው ውስጥ ይሯሯጡ ጀመር። ሱቆች ሁሉ እንዲዘጉ አደረጉ። የውጭ አገር ስዎችም ከቤታቸው እንዳይወጡ አዘዙ። በተለይ ፎቶግራፍ ማንሻ እየተፈተሸ ይወሰድ ጀመር። መንገዱ ሁሉ ጭር አለ። የፖስታና የስልክ አገልግሎት ተቁዋረጠ። በቤተ መንግሥቱና ባካባቢው ያሉት መንገዶች በሙሉ በሬሳ ተሸፈኑ።"

  "በምን አይነት አጨካከን ነው? ደም እንደውሀ ሲፈስ በየመንገዱ ላይ ያየሁት የዚያን ጊዜ ነው። የወንዶች፣ የሴቶች፣ የልጆች እሬሳ በያለበት ተኝቷል። ወዲያውም ከባድ የቃጠሎ ጭስ ተነስቶ ከተማዋን አጨለማት። የህዝቡ ቤት ከተፈተሸ በህዋላ ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ ቤቱ በእሳት ይቃጠላል። ቃጠሎው ቶሎ እንዲያያዝም በቤንዚንና በዘይት ይጠቀሙ ነበር። ሰው እሳቱን እየሸሸ ከቤቱ ሲወጣ በመትረየስ ይገድሉታል። ሌሊቱንም ሲገድሉና ሲያቃጥሉ አደሩ። የማልረሳው ነገር፣ በዚያ ሌሊት የኢጣልያ መኮንኖች በሚያማምር አውቶሞቢላቸው ከሚስቶቻቸው ጋር ሆነው ብዙ ሬሳ ከተከመረበትና ብዙ ቃጠሎ ከሚታይበት ቦታ በሰው ደም ላይ እየቆሙ ያን እልቂት እየተመለከቱ ይስቁ የነበረበት ሁኔታ ነው።"

  "ግራዚያኒን ሆስፒታል አስገብተውታል። ግራዚያኒ ሆስፒታል ሆኖ በመስኮት የከተማዋን መቃጠል እያየ ይስቅ ነበር። ዳግማዊ ኔሮ። በዓለም ጦርነት ጊዜ ቁስለኛ ለማንሳት ከግንባር ቀደሙ ጦር ጋር በአምቡላንስ ውስጥ እሰራ ነበር። በሌላም ጦርነቶች ተካፋይ ሆኛለሁ። እንደ አዲስ አበባው ያለ እልቂት ግን አላየሁም።"

  "በመክናዎቹ እየዞሩ ሬሳ ያነሳሉ። ባለጥቁር ሸሚዞች ወደ ኢጣልያ ባንክ እየገቡ ሌሊት የሰርቁትን ብርና ወርቅ ያስቀምጣሉ። ዘረፋው በቤት ውስጥ ብቻ አልነበረም። ከሚገድሏቸው ሴቶች አንገትና ጆሮ ላይ የሚገኘውን ወርቅ ሁሉ ይወስዱ ነበር።"

  "ሕክምና በምሰራበት ቦታ ብዙ ኢጣልያኖች የመጡ ነበር። እያንዳንዱ ኢጣልያም ምን ያህል ሰው እንደገደለ በኩራት ይናገራል። አንዳንዶቹ 80 ገደልኩ ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ መቶ እንደገደሉ ይናገራሉ። አንድ ኢጣልያዊ ብቻ እያዘነ እኔስ የገደልኩት ሁለት ብቻ ነው ብሎ ሲናገር ሰምቻለሁ። ... የማልረሳው ነገር፣ ግድያው እንዲቆም በተደረገበት ጊዜ ታላቁ ግራዚያኒ ለሕዝብ በማዘን ግድያው ይቁም ብለዋል ተብሎ የተነገረው ነው። ግሩም አዘኔታ ..." በማለት በሰፊው ፅፏል።

  በቁጥር 14154 ግራዚያኒ ሮማ ላለው ለቅኝ ግዛት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ቴሌግራም "እነኚህ ጥቁሮች የኛን ወታደር ሲያዩ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ይላሉ። ይህን የሚሉትንም ለመቀጣጫ ሁሉንም አስጨረስክዋቸው። እደግመዋለሁ፣ አስጨረስክዋቸው" ብሏል። በዚያው ዘመን እ.ኤ.ዓ. የካቲት 22 ቀን (በኛ የካቲት 14 ቀን) የወጣው ጋዜጣ ዴል ፖፖሎ ሲፅፍ "... የአዲስ አበባ አጋማሽ በአሰሳው ፀድቷል። 2000 ኢትዮጵያውያን ተይዘው ወደ ደናኔና ወደሌሎችም ማሰሪያ ቦታዎች ተልከዋል..." ይላል።

  የካቲት 12 ቀን በተጀመረው እልቂት በሶስት ቀን ውስጥ 30000 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተገደሉ በህዋላ ሌላው እየታፈሰ ወደ በረሃ እስር ቤቶች ተላከ። እስር ቤቶቹ እንዴት ነበሩ? ለጦር ወንጀለኞች አጣሪ ኮሚቴ፣ ብላታ በቀለ ሃብተ ሚካኤል ከተናገሩት ውስጥ በመጠኑ እንጥቀስ። "... መቃዲሾ እንደደረስን በቀጥታ ከዋናው ወህኒ ቤት አገቡን። በማግስቱም ወደ ደናኔ ወሰዱን። 200 ሰዎች ባንድ ቦታ አጎሩን። ይሰጡን የነበረው ምግብ ለጤናችን ፈፅሞ የማይስማማ ነበር።"

  "የሚሰጡንም በላዩ ላይ ብዙ ትላትሎች የሚታዩበት የደረቀ ቂጣና ሻይ ነበር። በዚህም ምክንያት ብዙዎቻችን ታመምን። የዚያን ጊዜ የእስር ቤቱ ኃላፊ ብርጋዴር ባሮኒ ነበር። ስለምግባችን ብዙ ጊዜ እየቀረብን ብናመለክትም ትዕዛዙ የበላይ ስለሆነ ምንም ማድረግ እንደማይቻል ይነግረን ነበር። በግራዚያኒ ሕይወት ላይ አደጋ ከተጣለ በህዋላ ብዙ እስረኞች ወደኛ መጡ። ቦታ ስለጠበበ ሜዳው በሽቦ ታጥሮ ከዚያ ሰፈሩ። እኛንም ወስደው ከነሱ ጋር ደባለቁን። ከተደባለቅን በህዋላ የምግብ ጉዳይ የባሰ ሆነ። በምግቡ ምክንያት በየቀኑ አራትና አምስት ሰዎች እየሞቱ ይጣሉ ጀመር..." ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ከተመሰረተ በህዋላ በዚሁ ስር ለተቁዋቁዋመው አጣሪ ኮሚሽን ቃላቸውን ከሰጡት እስረኞች መሃል ሌላው አቶ ሚካኤል ተሰማ ናቸው። እሳቸው እንዲህ ብለው ነበር "... በደናኔ እስር ቤት ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ታስሬ ቆይቻለሁ። የወህኒ ቤቱም ሁኔታ እንዲህ ነበር። ላንድ ወታደር ማደሪያ የተሰራች አንዲት ድንክዋን ለሶስት ኢትዮጵያውያን ተሰጠችን። ምግባችን የደረቀ ጋሌታ ነው። የውቅያኖሱን ውሃ መጠጣት እንደጀመርንም ብዙዎቻችን ታመምን። በየቀኑ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች በተቅማጥ በሽታ ይሞቱ ነበር። በጠቅላላውም 3175 ሰዎች ሞቱ። ይህንንም ቁጥር ለማወቅ የቻልኩት በክሊኒኩ ውስጥ ረዳት ሀኪምና የበሽተኞች ሁኔታ መዝጋቢ ስለነበርኩ ነው። በደናኔ እስር ቤት የነበርነው 6500 ሰዎች ነን። ከነዚሁ ውስጥ 3175 ሰዎች ሞቱ። ዓመት ከታሰርን በህዋላ ስጋ፣ ማካሮኒ እና ሩዝ በሳምንት አንድ ጊዜ ይሰጠን ጀመር። እስረኞቹን ይጠብቁ ከነበሩት ኢጣልያኖች መሃል ብርጋዴር ባሮኒ፣ 50 አለቃ ቶሳቶ እና አሁን ስሙን የረሳሁት የካራሚኔሪዎች ማርሻል እስረኞቹን በመግረፍ የታወቁ ነበሩ።"

  "ስራችን አትክልት መኮትኮት፣ የሚነድ እንጨት መስበርና መንገድ መስራት ነበር። በሥራ ቦታ ድካም የሚያሳዩ ሴቶች ሆኑ ወንዶች እጆቻቸውን የሁዋሊት እየታሰሩ ለሰባት ቀናት ጣሪያ ላይ ይንጠለጠላሉ። በእንዲህ ያለው ቅጣጥም ሁለት ሰዎች እጆቻቸው እየተገነጠሉ ሞተዋል። እስረኛ ታሞ ወደ ክሊኒክ በሚመጣበት ጊዜ ካፒቴን አንቶኒዮ እነዚህ ሰዎች ከሚኖሩ ቢሞቱ ይሻላቸዋል በማለት አርሴኒክ እና እስትሪቺኒን የተባሉ መርዞችን በመርፌ በመውጋት ይገድላቸው ነበር። አንዳንዶቹንም ለህክምና የሚመጡትን እጅና እግራቸውን እያሰሩ ገላቸውን በምላጭ በመተልተል ይጫወቱባቸው ነበር። ..." ሲሉ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

  የኤርትራ ክፍለ ሃገር ተወላጅ ደጃዝማች ሪሳርዮ ጊላ እግዚዕ በግራዚያኒ ላይ ቦምብ በተጣለ ጊዜ ከዚያው ስለነበሩ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ደጃዝማች በእውነት እመሰክራለሁ ብለው ከማሉ በህዋላ "... የተኩስ ድምፅ ሰማሁ። መኪናዎች እዚህም እዚያም ይሯሯጣሉ። ሰውም ይሯሯጣል። መትረየስ ይተኮሳል። ሁሉም ነገር ተመሰቃቅሏል። ኢትዮጵያውያኖች ከኢጣልያኖች ይሸሻሉ። ኢጣልያኞቹ ደግሞ ከኢትዮጵያውያኖቹ ይሸሻሉ። ኢጣልያኖቹ እንደገመቱት በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ከብቦ የነበረው ሽፍታ ከተማዋን የወረራት መስሏቸዋል። ከዚያ በፊት ራስ ደስታ ከአዲስ አበባ ገብተው የኢትዮጵያ አርበኞች ከከተማዋ ያለውን ኢጣልያዊ በሙሉ ይገድላሉ እየተባለ ይወራ ስለነበር ነው..." ብለዋል።

  ደጃዝማች ሪሳሪዮ ከሁለት ኢጣልያኖች ጋር ወደፋሺስት ጠቅላይ ፅህፈት ቤት ሄደው በዚያ ስላዩት ሲናገሩ "... ከፋሺስት ዋና ፀሀፊ ከጉይዶ ኮርቴሲ ጋር ተገናኘን። ዙሪያውንም ብዙ የፋሺስት ሹማምንት አሉ። ኮርቴሲም ለነኛ የፋሺስት መኮንኖች ... ወንድሞቼ ሆይ፣ ዛሬ ድል የማድረጋችንና የበላይነታችንን የማሳወቂያ ቀናችን ነው። በዚች በሶስት ቀን ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አጥፉ። ለዚህ ለሶስት ቀን የሚሆንም የነጭ ሽብር (ካርታ ቢያንካ) ፍቃድ እሰጣችዋለሁ። ይህም ፍቃድ ለማጥፋት፣ ለመግደልና በኢትዮጵያውያኖች ላይ የፈለጋችሁትን ለማድረግ የሚያስችላችሁ ነው አላቸው።"

  "ከዚህ በህዋላ እነኚያ የፋሺስት መኮንኖች ወጥተው ሄዱ። ሁሉም የጦር መሳሪያቸውን በክንዳቸው እንደያዙ ነበር። ልክ እንደወጡም ስራቸውን ጀመሩ። በካራሚኔሪዎች ያልታሰረ፣ በመንገድ ላይ ሲሄድ ወይም እቤቱ ውስጥ አርፎ የተቀመጠው ሁሉ ተገደለ። ... ቤቶች ሲቃጠሉ አይቻለሁ። ... ከሚቃጠለው ቤት ልጆች ሲወጡ በኢጣልያኖች እየተገፉ ከእሳቱ ውስጥ ሲጨመሩ አይቻለሁ።"

  "በማግስቱ ቅዳሜ ቀን ነበር። በዚያም ቀን ኢጣልያኖች ትንንሽ ቤቶችን ሲያቃጥሉ ዋሉ። በትልልቆቹ ቤቶች ላይ ግን ስማቸውን እየፃፉባቸው ያልፋሉ። ይህም ቤቱ የተያዘ መሆኑን ለመግለፅ ያህል ነው። ..." በማለት መስክረዋል።

  ፎር ጎድ ኤንድ ኤምፔረር በተባለው ድርሰታቸው ሚሲዮናውያኖቹ ሄር በርት እና ዴላ ሃንሰን እንደፃፉት "...  አዲስ አበባ የደረስነው እልቂቱ ከቆመ በህዋላ ነው። ከዚህ በፊት የህዝቡ መኖሪያ የነበሩ ቤቶች በሙሉ ተቃጥለዋል። ሌላው ቀርቶ የሆስፒታል ግድግዳዎች ሳይቀር በእሳት ተለብልበው ይታያሉ። በከተማዋ በሙሉ የሚታየው የከሰለ ቤት ፍራሽና በእሳት ተለብልቦ የጠቆረ ግንብ ነው። ይህንንም በማየታችን ልባችን ተነካ። በተለይም በጣም ያሳዘነን ነገር፣ ቤቶች ሁሉ የተቃጠሉት፣ ነዋሪዎች ውስጣቸው እንዳሉ ነው ቃሉን በህዋላ ነው።..." ብለዋል። በዚያን ቀን ስለተካሄደው እልቂት ብዙ የአይን ምስክሮች ብዙ አሰቃቂ ድርጊቶችን መስክረዋል። የሁሉንም ለማጠቃለል ራሱን የቻለ መፅሐፍ የሚወጣው ስለሆነ ትቼዋለሁ።

  ጋዜጠኛው ቺሮ ፖጃሊ የካቲት 13 ቀን ስላየው ሁኔታ "... ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎች መደበቃቸው ስለተሰማ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ቤንዚን ተረጭቶ እሳት ተለቀቀበት። ይህንንም ያዘዘው ኮርቴሲ ነው። ... የቤተክርስቲያኑ መፅሃፍትና ስዕሎች ተቃጠሉ። ... ከቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከእሳቱ ለመሸሽ 50 ያህል ሰዎች ሲወጡ ተያዙና ከቤተክርስቲያኑ ጉዋሮ ተወስደው በእሳት ይቃጠሉ ሲባል አንድ ኮሎኔል አዝኖላቸው መቃጠሉ ቀርቶ በቦምብ ይገደሉ ብሎ አዘዘና በሙሉ ተገደሉ።... በዚህ ቀን ኮሎኔል ማዚ የጠቅላላው የመገናኛ ራዲዮ ኃላፊ እንዳጫወተኝ ሶስት ጄኔራሎች መሞታቸው ተላልፏል አለኝ..." በማለት በመፅሐፉ ፅፎታል።

  የካቲት 12 ቀን ስለደረሰበት አደጋ ግራዚያኒ ለኢጣልያ ቅኝ ግዛቶች ሚኒስቴር ቴሌግራም ልኮ ነበር። የዚያም ቴሌግራም ግልባጭ በኢትዮጵያ ላሉ የኢጣልያ ሹማምንት ተላልፎ ነበር። ግራዝያኒ ባስተላለፈው ቴሌግራም "... ዛሬ ጧት በ11 ሰዓት (በኛ 5 ሰዓት) ግቢ ተገኝቼ ነበር። ታላላቅ መኩዋንንት፣ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች ሁሉ ተሰብስበው ነበር። የስብሰባው ዋና ምክንያት የኔፕልስ መስፍን ስለተወለደ ሶስት ሺህ ለሚሆኑ ድሆች ምፅዋዕት ለመስጠት ነበር። 12 ሰዓት ሲሆን (በኛ 6 ሰዓት) በተሰበሰበው መኩዋንንት አስር የብሬዳ ሥራ የእጅ ቦምቦች ካልታወቁ ሰዎች ተጣሉብን። በዚህም ምክንያት ሰላሳ ሰዎች ቆሰሉ። ... በእኔ መቁሰል ምክንያት አገሪቱን የተከበሩ ፔትሬቴ እና ጄኔራል ጋርቦልዲ በህብረት እንዲጠብቁ አድርጌያለሁ። ለአዲስ አበባ ከተማ ፀጥታም አላፊ አድርጌያቸዋለሁ።" ብሏል።

  በሌላ ቀን ባስተላለፈው ቴሌግራሙ ደግሞ "... የተጣለብኝ ቦምብ ቢያንስ 18 ይህናል። አሳባቸው ባንድ ፈንጂ እኔን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የመንግሥቱን ባለስልጣኖች ጠራርጎ ለማጥፋት ነበር።... ሊሆን ግን አልቻለም። ... የአዲስ አበባ ሰዎችም ጉዳይ ታውቁዋል። የአዲስ አበባን ከተማ ዙሪያ ከከበበው ሽፍታ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው የመከላከያ ኃይላችንን ከጀርባው ይወጉታል። ... በተጣለብኝም ቦምብ 250 ፍንጥርጣሪ ብረቶች ከገላዬ ወጥተዋል። እነኚህንም ፍንጥርጣሪዎች ለታላቅ መታሰቢያነት አስቀምጫቸዋለሁ።..." ብሏል።

  ግራዚያኒ የየካቲት 12 ቀንን እልቂት ባዘዘ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የነበረው የኢጣልያ ወታደር 35000 ሜትሮፖሊታን ወታደሮች፣ 40000 ባለጥቁር ሸሚዝ ሚሊሺያ፣ 5000 የኤርትራ፣ 3000 የሊቢያ ተወላጅ ወታደሮች ነበሩ። የኤርትራ ተወላጅ ወታደሮች "እኛ ወታደሮች ነን። ከተማ ውስጥ ከሴትና መሳሪያ ከሌለው ጋር በጥይት ተኩስ አንተኩስም" በማለታቸው ብዙዎቹ ጦር ሰፈራቸው ውስጥ ተገደሉ። ሌሎችም ታሰሩ።

  የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ዛሬ ዩኒቨርሲቲ በሆነው ግቢ ውስጥ ቦምቦች ሲፈነዱ ቦምቦቹ የተጣሉት ከሁለት ይሁን ከብዙ ሰዎች እስካሁን የታወቀ መረጃ የለም። ግራዚያኒ አጠገብ የፈነዳውን ግን አብርሃ ደቦጭ ከጉዋደኛው ከሞገስ አስገዶም ጋር እንደጣለው ይነገራል።

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት
  በጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  ይድረስ ከሙሴ አልቤርቶ ፕሪስ፣

  ሰላም ላንተ ይሁን። በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ ወርቅ እና ሁሉ አይነት ሜኔራል እንድፈልግ እወዳለሁ ብለህ ስለጠየከኝ ከዚህ ቀጥሎ በተፃፈው አገር ውስጥ ለሶስት ዓመት ወርቅና ሁሉን አይነት ሜኔራል፣ ክቡር ድንጋይም እንድታስፈልግ በዚህ ወረቀት ላንተ ብቻ ፍቃድ ሰጥቼሃለሁ። ይህም የምትፈልግበት ሃገር ወሰን ይህ ነው። ከገንጂ ወንዝ ምንጭ አንስቶ እስከ ጁባ ወንዝ ምንጭ ድረስ። ከጁባ ወንዝ በወረደ ጉሙዝ ድረስ። ደግሞ ከገንጂ ወንዝ ግራ ግራውን ወርዶ ያምቦ ከሚባለው ጉሙዝ ድረስ።

  ይህም ሶስት ዓመት ፈልግ ያልኩህ በ1897 ዓ.ም. በጥር 5 ቀን ይጀምራል። አሁን ካልነው አገር ውስጥ ወርቅ እና ሜኔራል፣ ክቡር ድንጋይም ተገኝቶ አወጣለሁ ስትል፣ ያንጊዜ ውል እናደርጋለን። ይህንንም ስትፈልግ ከባላገር እንዳትጣላ ከአገር ሹም ዳኛ እየተቀበልክ ይሁን። ይህንንም ውል በምናደርግበት ጊዜ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚገባውን ግብር ከዚህ ቀደም ለሌላ ከተነጋገርኩት በላይ አላስበልጥብህም።

  ጥር 5 ቀን 1897 ዓ.ም. አዲስ አበባ

  ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

  ይድረስ ከሙሴ አርኖልድ ሆልድ፣

  ሰላም ላንተ ይሁን። በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ ወርቅ እና ሁሉ አይነት ሜኔራል እንድፈልግ እወዳለሁ ብለህ ስለጠየከኝ ከዚህ ቀጥሎ በተፃፈው አገር ውስጥ ሶስት ዓመት ወርቅና ሁሉ አይነት ሜኔራል፣ ክቡር ድንጋይም እንድታስፈልግ በዚህ ወረቀት ላንተ ብቻ ፍቃዴን ሰጥቻለሁ። ይህንንም የምትፈልግበት አገር ወሰን ይህ ነው። በሴሜን በኩል የገባ ወንዝ፣ በደቡብና በምዕራብ በኩል የገንጂ ወንዝ፣ በምስራቅ በኩል ከገባ ምንጭ አንስቶ እስከ ገንጂ ምንጭ ድረስ ነው።

  ይህም ሶስት ዓመት ፈልግ ያልኩህ በ1897 ዓ.ም. በጥር 5 ቀን ይጀምራል። አሁን ካልነው አገር ውስጥ ወርቅ እና ሜኔራል፣ ክቡር ድንጋይም ተገኝቶ አወጣለሁ ስትል፣ ያንጊዜ ውል እናደርጋለን። ይህንንም ስትፈልግ ከባላገር እንዳትጣላ ከአገር ሹም ዳኛ እየተቀበልክ ይሁን። ይህንንም ውል በምናደርግበት ጊዜ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚገባውን ግብር ከዚህ ቀደም ለሌላ ከተነጋገርኩት በላይ አላስበልጥብህም።

  ጥር 5 ቀን 1897 ዓ.ም. አዲስ አበባ

  ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

  ይድረስ ከሙሴ ዳሱ ዶግስ፣

  ሰላም ላንተ ይሁን። ከአሁን ቀደም ወርቅና ሁሉ አይነት ሜኔራል በኢትዮጵያ መሬት ለመፈለግ ፍቃዴን ለማግኘት ሙሴ ዲዴን ልከህ ስለጠየከኝ፣ ከዚህ ቀጥሎ በተፃፈው አገር ውስጥ በሁለት ዓመት ውስጥ ወርቅና ሜኔራል፣ ክቡር ድንጋይም እንድታስፈልግ በዚህ ወረቀት ላንተ ብቻ ፈቃድ ሰጥቻለሁ። ይህንንም የምትፈልግበት አገር ወሰን ይህ ነው። በምስራቅ በኩል የሙገር ወንዝ፣ በምዕራብ በኩል የደዴስ ወንዝ፣ በሰሜን በኩል የአባይ ወንዝ፣ በደቡብ በኩል ከአዲስ አበባ አንስቶ ለቀምቴ ከተማ ድረስ ያለው የነጋዴ መንገድ ነው።

  ይህም ሁለት ዓመት ያልኩህ በሐምሌ 1 ቀን 1897 ዓ.ም. ይጀምራል። አሁን ካልነው አገር ውስጥ ወርቅና ሜኔራል፣ ክቡር ድንጋይም ተገኝቶ አስወጣለሁ ስትል፣ ያን ጊዜ ውል እናደርጋለን?? ይህንንም ስትፈልግ ከባላገር እንዳትጣላ ከአገር ሹም ዳኛ እየተቀበልክ ይሁን። ይህንንም ውል በምናደርግበት ጊዜ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚገባውን ግብር በመጀመሪያ በሰጠሁህ ፍቃድ በቤንሻንጉል ወርቅና ሌላ አይነት ሜኔራል ለማውጣት እቀባላለሁ ካልሁህ በላይ አላስበልጥም።

  የካቲት 14 ቀን 1897 ዓ.ም. አዲስ አበባ

  ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

  ይድረስ ለጄኔራል ልሸን፣

  ሰላም ላንተ ይሁን። እኛ የተነጋገርንው እኔ ለራሴ ብዬ ካቆየሁት የወርቅ ቦታ ሚጤ ከሚባለው ወንዝ ላይ የመስኮብ መሀንዲሶች የወርቅ ማውጫ መዘውር ያቆሙልኛል። እስከ ሁለት ዓመት እነሱ ይሰሩልኛል። የኔንም ሰዎች ያስተምሩልኛል። የመኪናውንም ዋጋ ደሞዛቸውንም ከዚያው ከሚያወጡት ወርቅ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ በየዓመቱ ሁለት ሺህ ከአምስት መቶ ወቄት፣ ቢበዛም እስከ ሶስት ሺህ ወቄት ድረስ ይቀበላሉ።

  እነዚያም አይተው የተመለሱት የመስኮብ መሀንዲሶች ከዚያው ከወርቁ ቦታ በአንድ ዓመት ከአራት ሺህ እስከ አምስት ሺህ ወቄት ይገኝበታል እንዳሉኝ አንተም ታውቃለህ። ከዚያው ከሚያወጡት ወርቅ ለኔ የሚተርፈኝ በየዓመቱ ከአንድ ሺህ ወቄት ወርቅ ይበልጣል። እንግዲህ በዚሁ ቃል እነሱ የወርቁን ማውጫ መኪና አምጥተው እንዲሰሩልኝ ይሁን።

  እኔም ለስራው ለመርዳት ሰው አዝላቸዋለሁ። የወርቁን ማውጫ መኪና መሳሪያ ሁሉ የመስኮብ መሃድሶች ባልጪ ድረስ ተጠንቅቀው ያወጣሉ። ግን ከባልጪ አንስቶ ሚጤ ድረስ እኔ እሰድላቸዋለሁ። እነሱ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ከሰሩልኝ በህዋላ፣ የወርቁ ማውጫ መኪና ከነመሳሪያው፣ አንድ ነገር ሳይጎድል ሁሉም ነገር ለኔ ይቀራል። እነሱ ያስተማሩልኝ የኔ ሰዎች ይሰሩልኛል።

  መጋቢት 12 ቀን 1897 ዓ.ም. አዲስ አበባ


  ምንጭ:
  አጤ ምኒልክ በውጭ አገራት የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች
  በጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  ወደፊት የሚገሰግሰው የኢጣልያን ጦር መስከረም 25 ቀን 1928 ዓ.ም. አዲግራትን ያዘ። አዲግራት ከተያዘ በሕዋላ ከአዲግራት እንትጮ፤ ከእንትጮ አድዋ የሚያደርስ የመኪና መንገድ መስራት ተጀመረ። የመንገዱ ሥራ የሚከናወነው ሌት ከቀን ነበር። ወታደሩ እና መንገድ ሰሪው ክፍል በመደዳ በሰልፍ ቆሞ "ከሮም እስከ አዲስ አበባ" የሚለውን መዝሙር እየዘመረ እጅ በጅ ድንጋይ ይቀባበላል። ከኢጣልያ ወታደር ፊት ለፊት አምሳ ማይል ያክል ራቅ ብለው 20,000 ወታደሮች ይዘው የተቀመጡትን ራስ ስዩምን የሚያስባቸውም ሆነ የሚጨነቅላቸው ኢጣልያዊ የለም። በስተሰሜን 40,000 ወታደር ይዘው የተሰለፉትን ራስ ካሳንም የሚያስታውስ ኢጣልያዊ ጠፋ። ኢጣልያኖች ሁለቱንም የጦር መሪዎች ንቀው የመንገድ ስራቸውን ቀጠሉ።

  የምድር ጦሩ መንገዱን በሚሰራበት ጊዜ የኢጣልያን አየር ኃይል አድዋ ከተማ ድረስ በመብረር ሕዝቡን ያስፈራራ ነበር። ጋዜጠኛው ቼስኮ ቶማሴሊ "... ዴስፔራታ የሚባሉት አውሮፕላኖቻችን ከእግረኞቻችን ጦር ቀድመው እየሄዱ የጠላትን ሰፈር ይመታሉ። በ0820 ሰዓት አድዋ ከተማ ላይ ስያንዣብቡ ከአድዋ ግቢ ፀረ አውሮፕላን ተተኮሰ። ከየቤቱ ሁሉ መትረየስ ወደ አውሮፕላኖቻችን ይተኮሳል። ነገር ግን አውሮፕላኖቻችን በአድዋ ከተማ ላይ ሶስት ጊዜ ሲያንዣብቡ ሊያግዳቸው የቻለ ኃይል የለም። ከአይሮፕላኖቻችን የሚጣሉት ቦምቦችና የሚተኮሱት መትረየሶቻችን በመሬት ላይ ከከተማዋ ይተኮስ የነበረውን ተኩስ እያበረደው ከተማዋን ጭስ ብቻ አደረጋት..." በማለት ፅፏል።

  እንደ ቶማሴሊ አፃፃፍ ከተማዋ ቃጠሎ ይነሳባት እንጂ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። አምስት ሺህ ያህል የሚሆነው የአድዋ ከተማ ሕዝብ ከተማዋን ለቅቆ ሸሽቶ ስለነበር የኢጣልያ ቦምብና መትረየስ የገደለው አንዲት ሴት፤ አንድ ሕፃንና ጥቂት ከብቶችን ነበር። ከቦምቡ ውርወራ በህዋላ የታተሙ የስብከት ወረቀቶች ከአይሮፕላን ተበተኑ። የተበተኑትም ወረቀቶች "... በሰላም አርፋችሁ ስራችሁን ስሩ። ለዚህ ፍትህ፤ ነፃነት እና ሰላም ለሚያስገኝላችሁ ለኢጣልያ ድል አድራጊነት ድሉ ቶሎ እንዲያልቅ ፀልዩ። የኢጣልያ ወታደር የመጣው ለእናንተ ሰላም ሊያስገኝ ነው... የመጣነው እነዚህን ወንጀለኞች ጌቶቻቹን ለመቅጣት ነው..." የሚል ቃል የያዘ ሲሆን ህዝቡ በአሰተኛ ወሬ እንዳይሸበርና ችግር እንዳይፈጥርም ያስጠነቅቃል።

  የኢጣልያ ጦር አድዋን በቀላሉ አልያዘም። በደጃዝማች ገብሬ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር የኢጣልያን ጦር አግዶ ተዋግቶ ነበር። ይህን የኢትዮጵያን ጦር የፈታው ከአይሮፕላን የሚጣለው ቦምብና አይሮፕላኖቹ የሚተኩሱት መትረየስ ነው። ይህም ቢሆን የሙሶሎኒ ጦር መረብን ካቁዋረጠ ጀምሮ ለመጀመርያ ጊዜ ኢጣልያዊ ወታደር በኢትዮጵያውያን የተገደለው በአድዋ ጀግኖች ነው። በመደበኛው ጦር የብርጌድ አዛዥ የነበረው ሌተና ሞርጋንቲኒ ከአድዋ ጀግኖች በተተኮሰ ጥይት ተገደለ። ሞርጋንቲኒ እንደተገደለ ወታደሮቹ በመሪያቸው ሞት ተደናግጠው ቦታቸውን ለቀው ሲሸሹ በነሱ ቦታ 3ኛው ባታሊዮን ተተካ።

  የኢጣልያ ሰላይ ቡድን ወደ አድዋ ሄዶ ሰልሎ ሲመለስ የአድዋ ከተማ ባዶ መሆኑንና ራስ ስዩምም ያለመኖራቸውን ተናገረ። ከዚህ በህዋላ ከዳር ተቀምጦ የነበረው 84ኛው ሬጂሜንት 2ኛ ብርጌድ መስከረም 26 ቀን 1928 ዓ.ም. ከጧቱ አራት ሰዓት ላይ አድዋ ከተማ ገባ። ይህ ብርጌድ አድዋ ከተማ ሲገባ ሙዚቀኞች በሰልፍ ሆነው ሙዚቃ እያሰሙ የኢጣልያን ባንዲራ አስይዞ ገባ። የብርጌዱ አዛዥ ቪላ ሳንታ ፈረስ ላይ ሆኖ በመኮንኖች ታጅቦ ከወታደሩ ጀርባ እየተግዋዘ ወደ ራስ ስዩም ግቢ ሄደ።

  ቪላ ሳንታ በአስተርግዋሚው ንግግር አደረገ። "... ከዚህ በህዋላ ቦምብ የለም። የሸሹት ዘመዶቻቹም ይመለሱ። ኢጣልያ መብታችሁን በሙሉ ትጠብቃለች..." አለ። ቪላ ሳንታ ንግግሩን ሳይጨርስ አምስት ኢትዮጵያውያን ተኩስ ከፈቱበት። ከእነዚህም ከአምስቱ አንደኛው እዛው ሲገደል አራት አመለጡ።

  የሶስተኛው አየር ኃይል ብርጌድ አዛዥ ጄነራል ራንዛ የአድዋን መያዝ በቴሌግራም ለደቦኖ አሳወቀ። ጄኔራል ደቦኖ በአራት ሰዓት ተኩል የአድዋን መያዝ እንደሰማ በአምስት ተኩል ገደማ "ኩሩዎቹ ኢጣልያኖች በኩራት አድዋ ገቡ" የሚል ቴሌግራም ወደ ሮም አስተላለፈ። ሙሶሎኒ የአድዋን መያዝ ሲሰማ ተደሰተ። "ለአንተ እና ለወታደሩ ሁሉ የከበረ ምስጋና በኔና በሕዝቡ ስም አቀርባለሁ" የሚል መልስም ለደቦኖ ላከለት።

  ቀደም ስል እንደተጠቀሰው የኢጣልያ ጦር አድዋን በቀላሉ አልያዘም። የኢትዮጵያ ወታደር ባለው ውልክስክስ ጠመንጃና ጥይት 30 የኢጣልያ ወታደሮችን ገድሎ 70 አቁስሏል። 33 የኢጣልያ ወታደሮች ጠፍተዋል። ይህ ቁጥር ራሳቸው ኢጣልያኖች ያመኑት ነው። አድዋ ከተያዘ ከጥቂት ቀናት በህዋላ፤ ማለትም ጥቅምት 3 ቀን አክሱም ተያዘ። ከጥቂት ቀናት በህዋላም የአክሱም ሃውልት "የድል አድራጊው የፋሺስት መንግስት መታሰቢያ" ተብሎ ተወሰደ።

  ኢጣልያኖች ኢትዮጵያን ለመውጋት ጦር ሲያግዙ ከጦሩ ጋር አንድ ከእብነ በረድ የተሰራ ሐውልትም ከሮማ መጥቶ ነበር። ሀውልቱ በጋቪናና ዲቪዥን ሲግዋዝ ከርሞ አድዋ እንደተያዘ በዱቼ ሙሶሎኒ ትዕዛዝ በምኒልክ ጊዜ አድዋ ላይ ለተገደሉ ኢጣልያኖች መታሰቢያነት ተተከለ። ይህንንም የመታሰቢያ ሃውልት ጄነራል ደቦኖ መርቆ ከፈተው።

  ኢጣልያ አድዋና አክሱምን ከያዘ በህዋላ አልደላውም። ለስብከት ብሎ የሚነዛውን ገንዘብ ህዝቡ በደስታ አልቀበል አለ። በተለይ ከኤርትራ ተቀጥረው የዘመቱለት ወታደሮች፤ ማለትም የኤርትራ ተወላጆች በብዛት ከድተው ከነመሳሪያቸው ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ስለተደባለቁ ከባድ ስጋት አደረበት። ደቦኖም ከዚያን ጊዜ ወዲህ የነጭና የጥቁር ወታደሩን ማለያየቱ ቀርቶ ባንድነት ተደባልቀው እንዲዘምቱ አደረገ። የዚህም ምክንያት ነጮቹ ወታደሮች ጥቁሮቹን ወታደሮች በአይነ ቁራኛ እንዲጠብቁ ነው።

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት
  ከጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  • "እስከዛሬ ድረስ በተደረገው የታሪክ ምርምር የደጃዝማች ኃይለስላሴ የክዳት አይነትና አፈፃፀም፤ ከሌሎች ሁሉ የተለየ የሚያደርገው በቂ ምክንያት መኖሩ መታወቅ አለበት። ደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ፤ ለፋሺስት መንግስት ተባባሪነታቸውን በመግለፅ የመጀመሪያው መስፍን ብቻ ሳይሆኑ፤ ከጠላት ጋር ተሰልፈው አገራቸውን ለመውጋት የፋሺስት ዩኒፎርም ለመልበስም የመጀመሪያው ናቸው።" አምባሳደር ዘውዴ ረታ።

  • "ከእኚህ ሰው ጋር በ1967 ዓ.ም. ተገናኝተን ስንጫወት "... በሰላም በግብርና እያረስኩ ለመኖር እንጂ ኢትዮጵያን ለመጉዳት አልከዳሁም..." ብለውኛል። ውሸታቸውን ነው እንጂ በአምስቱ የፋሺስት ዘመናት የሰሯቸውና በየጊዜው የሚሸለሟቸውን ሜዳሊያዎች የሚያወሱ የኢጣልያ ጊዜ ጋዜጦች ከእኔ ዘንድ በብዛት አሉ።" ጋዜጠኛ እና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ።

  ኃይለስላሴ ጉግሳ የአፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ነው። ኃይለስላሴ ጉግሳ እጅግ ተሞላቆ ያደገ መስፍን ነው ይለዋል ሞስሌ በመፅሐፉ።  ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ስልጣን እንደያዙ ትግራይን ለሁለት ከፍለው ለራስ ስዩም እና ለሀይለስላሴ ጉግሳ በገዢነት ሰጧቸው። በዚያም ላይ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ገና ለጋብቻ ያልደረሰች ልጃቸውን ዘነበወቅን ገና በ13 ዓመት እድሜዋ ለኃይለስላሴ ጉግሳ ዳሩለት። ልጅቱም በወልድ ምክንያት ሞተች።


                                                   ልዕልት ዘነበወርቅ ኃይለስላሴ።

  ኃይለስላሴ ጉግሳ "ግዛት አንሶኛልና ትግራይ በሙሉ ተጠቃሎ ይሰጠኝ" በማለት አመለከተ። ንጉሱም "ሁሉን ለማስተዳደር አትችልምና ከስዩም ጋር እየተረዳዳችሁ ግዙ" አሉት። ኃይለስላሴ ጉግሳ በአማችነቱ ሁልጊዜ ወደ አዲስ አበባ ይመላለሳል። ወደ አዲስ አበባ የሚመላለሰውም በአስመራ ዞሮ በመርከብ ወደ ጅቡቲ ሄዶ፤ ከጅቡቲ በባቡር ተሳፍሮ አዲስ አበባ ይገባል። ኤርትራ ወሰን በሚደርስበት ጊዜ የኢጣልያ መኪና ተቀብሎ አስመራ ያገባዋል። ሲመለስም ከባህር ጠረፍ እስከ ትግራይ ወሰን በኢታጣልያ መኪና ይጉዋዛል።


                                                       ደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ።

  ደቦኖ በመፅሐፉ "... ጉግሳ የንጉሰ ነገስቱ ሴት ልጅ ባል ነው። ያመፀ አመፀኛ ነው። ... በትግሬ በተሾሙት ራስ ስዩምና በሱ መሃል ቅራኔ አለ። የስለላ ጉዋዶቻችንና አድዋ ያለው ቆንስላችንም ኃይለስላሴ ጉግሳ ከኛ ወገን እንዲሆን አድርገውታል። ... አስመራ መጥቶ የኛ መሆኑን ካረጋገጠ በህዋላ ሹመት እንድሰጠው ጠየቀኝ።... ከኢትዮጵያ ጋር ግጭቱን እስክንጀምር ድረስ እሺ እያልኩ አቆየሁት።... እንቁላል ለመጥበስ መጥበሻውን ከማዘጋጀታችን በፊት እንቁላሉን እንዳልሰብር ብዬ ነው። ስለዚህ ኃይለስላሴ ጉግሳን ግድየለም ታገስ ብቻ... ቀኑ በደረሰ ጊዜ ያልከውን ሁሉ አደርግልሃለሁ እያልኩ አቆየሁት።... " ይላል።

  በአስመራ የኢትዮጵያ ቆንስላ የነበሩት ወዳጆ አሊ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ኃይለስላሴ ጉግሳ ከኢጣልያኖች ጋር መወዳጀቱንና ከኢታልያኖችም ደሞዝ እንደሚከፈለው በበቂ ማስረጃ አስረድተው ለንጉሡ አመለከቱ። ንጉሰ ነገስቱም "... አሁን ያለው የኢትዮጵያ መክዋንንት አብዛኛው ከኢጣልያ ገንዘብ ይቀበላል። ይህም የኢጣልያን ኢኮኖሚ ለመጉዳት እንጂ እኛን ለመክዳት አይደለም። ሁሉም ከኛው ጋር ናቸውና የኃይለስላሴ ጉግሳም እንደዚሁ ነው..." ብለው የወዳጆ አሊን ሪፖርት ሳይቀበሉ ቀሩ።

  ኃይለስላሴ ጉግሳ ጦርነቱ ሊነሳ አቅራቢያ መስከረም 28 ቀን ከአዲስ አበባ ጋር የሚገናኘውን የስልክ መስመር በሙሉ በጣጥሶ በወታደሮቹ ታጅቦ የአስመራ ጉዞውን ጀመረ። ኃይለስላሴ ጉግሳ ወደ ኢጣልያኖች ከመግባቱ በፊት 12,000 ወታደሮች ነበሩት። ኢትዮጵያን ከድቶ ወደ ኢጣልያ ሲገባ ግን እሱንም ሰራዊቱ ከድቶት ታጅቦ የገባው በ1000 ወታደሮች ብቻ ነው። ኃይለስላሴ ጉግሳ ዕዳጋ ሐሙስ ላለው የኢጣልያ ጦር እጁን ሲሰጥ ለኢጣልያ መንግስት ከልብ ለማገልገል መምጣቱን ነገረ።

  ደቦኖ በመፅሐፉ ስለ ኃይለስላሴ ጉግሳ አመጣጥ ሲገልፅ "ኦቶብሬ 8 ቀን ጄኔራል ሳንቲኒ በላከብኝ መልዕክት ኃይለስላሴ ጉግሳ ከኛ እርዳታ መፈለጉንና መቀሌ ውስጥ 7000 ሰዎች ይዞ የተቀመጠውን ደጃዝማች ኃይሉ ከበደን ለመውጋት መጠየቁን ላከብኝ። ኦቶብሬ 10 ቀን ጧት ጄኔራል ሳንቲኒ ደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ ሰዎቹን ይዞ በኛ መስመር ለማለፍ ጠይቁዋልና ምን ላድርግ? ብሎ ለከብኝ። እኔም መምጣቱን ይምጣ ግን አንድ አይንህን ጣልበት አልኩት። ... ቀትር ሲሆን የአየር ክፍላችን እንዳስረዳኝ በረጅም ሰልፍ በሰላም እንደምጉዋዝ እና በጉዋዙም ውስጥ ከብቶች መኖራቸውንና ጉዞውም ከመቀሌ ተነስቶ በአዲግራት በኩል ለማለፍ ከመሃል መድረሱን ነገሩኝ። በአራት (በኛ አስር) ሰዓት ከአንደኛ ክፍለ ጦር በራዲዮ ኃይለስላሴ ጉግሳ 1200 ሰዎች፤ 8 ጥሩ መትረየሶች ይዞ አዲግራት መግባቱን ነገሩኝ። ይህንንም ወደ ሮም ሳስታውቅ 10,000 ወታደሮች አሉት የተባለው እያባዙት ነው ብዬ መምጣቱን ነገርኩ። ለጄኔራል ሳንቲኒም በሚቀጥለው ቀን ኃይለስላሴ ጉግሳ ከኔ ዘንድ መጥቶ እንድንገናኝ እንዲያደርግ በቴሌግራም አሳወቅኩት።"

  "ኦቶብሬ 12 ቀን በ11 (በኛ 5) ሰዓት ኮአቲት ደረሰ። እኔም በጎጆዬ ውስጥ ተቀበልኩት። እሱም መከፋቱን ነገረኝ። ስለጉዳዩም አንዳንድ ፍንጭ አጫወተኝ። በአበሻ ውስጥ ጦርነት የሚፈልግ ሰው እንደሌለና ጦርነቱን የሚፈልግ ንጉሡ ብቻ መሆኑን ነገረኝ... አሁን ፈጥናችሁ መቀሌን ብትይዙ በሰላም ገብታችሁ መቀመጥ ትችላላችሁ አለኝ። እኔም ይሄን መወሰን የምችለው አቆርዳትን ጎብኝቼ ስመለስ ነው አልኩት። ከዛ በሁዋላ ስለኛ ወታደሮች ያለውን አስተያየት ጠየኩት።"

  "እጅግ በጣም ታላቅ ዝግጅት ነው አለኝ። በተለይ የሰራነው መንገድ እንዳስደሰተው ነገረኝ። ... ሰዎችህ አሁን ባንተ ላይ ሙሉ እምነት አላቸውን? አልኩት። እሱም በአዎንታ ራሱን ነቅንቆ እንደነገርኩዋችሁ በጣም ጥሩ የሚሆነው በተቻለ ፍጥነት መቀሌ ብትገቡ ነው አለኝ። ..." ይለዋል።

  የዚህ ሰው መክዳት የኢትዮጵያን ጦር በብዙ መንገድ ጎድቷል። አዲስ አበባ በሚመጣበት ጊዜና መቀሌም ሆኖ ንጉሰ ነገስቱ የጦሩን ምስጢር ያጫውቱትና ያማክሩት ስለነበር የኢትዮጵያን ጦር ሁኔታ በዝርዝር ያውቀዋል። ይህንንም የሚያውቀውን የኢትዮጵያን ጦር ሁኔታ በዝርዝር ነደቦኖ ነግሯል። ኢንጂነር ፌርናርድ ቤትሪ የተባለ የስዊድን ሰው ከደሴ አዲስ አበባ ድረስ የሚሰራው መንገድ ፕላን ለበረውና አብሮ ከድቶ ፕላኑን መሰናክሎቹን ሁሉ የሚገልፀውን መመሪያ ኃይለስላሴ ጉግሳ ለደቦኖ ሰጠ። መቀሌ ድረስም ያለምንም ችግር በሱ መሪነት ኢጣልያኖች መጉዋዝ እንደሚችሉ አስረዳ። ራስ ስዩምም ምንም መከታና ረዳት ስለሌላቸው ከዋና ከተማቸው ከአድዋ በቀላሉ መግባት እንደሚቻል ከደቦኖ አጫወተው።

  ኃይለስላሴ ጉግሳ እሱን ባልከዱት ጥቂት ወታደሮች ታጅቦ፤ ካኪ ልብሱን ለብሶ፤ በሠራዊቱም መሃል ሃያ መትረየስ፤ አራት የተራራ መድፍ እና ሁለት መለስተኛ ፀረ አውሮፕላን መትረየስ ይዞ ከደቦኖ ጋር ሲገናኝ ጄኔራል ደቦኖ ሚስጥሩን ሁሉ ከሰማ በሁዋላ በኢጣልያ ንጉስ በቪክቶር አማኑኤል ስም የትግራይ ጠቅላይ ገዥ ብሎ ሾመው።


                                  ደጃዝማች ኃይለስላሴ የልዑል ራስነት ማዕረግ ከኢጣልያን ሲቀበል።

  ስለሹመቱ ጉዳይ ደቦኖ ሲገልፅ "... ሙሶሊኒ በቴሌግራም ደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳን የትግሬ ጠቅላይ ገዥ ብዬ እንድሾመው አሳወቀኝ። አሳቡ ጥሩ አሳብ ነው። ነገር ግን እኔ እንዳጣራሁት ኃይለስላሴ ጉግሳ ሕዝብ የሚያቅፈው ትልቅ ሰው አይደለም። ተዋጊም አይደለም። ... እንደ አባቱ እንኩዋን የማስተዳደር ችሎታ የለውም። ቢሆንም ብዙ ወታደሮች በተሰበሰቡበት በንጉሳችን ስም ሹመቱን አወጅኩለት..." ብሏል።

  ከዚህም በሁዋላ በኃይለስላሴ ጉግሳ ሰባኪነት አንዳንድ የትግራይ ሹማምንት ለኢጣልያ ገቡ። ኃይለስላሴ ጉግሳም ካኪውን ለብሶ፤ በቀይ ሐር ጥብጣብ በግራና በቀኝ ቁልቁል የተሰመረበትን ጠባብ ሱሪውን ታጥቆ፤ ረጅም ቧት ጫማ አድርጎ፤ የኢጣልያኖችን ጠርቡሽ (ባርኔጣ) ራሱ ላይ ደፍቶ በአስመራ ከተማ እየተዘዋወረ ለሕዝብ ይታይ ጀመር። ከዚህም በተጨማሪ ጦርነቱ በተነሳ ጊዜ ኃይለስላሴ ጉግሳ ለኢጣልያኖች እጅግ ጠቃሚ ሥራ የሰራና ቀንደኛ ተዋጊ ነበር። በተለይ በመንገድ መምራት በኩል ብዙ አገልግሏል።

  ምንጭ:
  1. የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት -- በጳውሎስ ኞኞ
  2. የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት --በዘውዴ ረታ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን 1935 ዓ.ም.፤ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የክተት አዋጅ ካስነገሩ በሇዋላ፤ በሰሜን በኤርትራና፤ በደቡብ በሱማሌ በኩል፤ በሚገባ ተዘጋጅቶ የመጣውን የፋሺስት ጦር ለመከላከል፤ ዋና ዋናዎቹን አዝማቾች መርጠው እንደሚከተለው ደለደሉ።

  ዋና ጠቅላይ አዝማች:- ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ -- የቤጌምድር እና የሰላሌ ገዥ።


                                                     ልዑል ራስ ካሳ ሃይሉ።

  ሀ/ ለሰሜን ጦር፤
             1. በተንቤን ግንባር
             ዋና አዝማች፤ ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ -- የትግራይ ገዥ፤
             በውስጣቸው:          ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ፤ የከምባታ ገዥ።
                                        ደጃዝማች በየነ አባ ሰብስብ፤ የኮንታ ገዥ።
                                        ደጃዝማች ወንድወሰን ካሳ፤ የቤጌምድር እንደራሴ።
                                        ደጃዝማች አበራ ካሳ፤ የሰላሌ እንደራሴ።
                                        ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ፤ የዋና ሰቆጣ ገዥ።
                                        ፀሀፊ ትአዛዝ አፈወርቅ ወልደማርያም፤ የቀድሞ የፅህፈት ሚኒስትር።
                                         ደጃዝማች መንገሻ ይልማ፤ የጦር ሚኒስቴር ዲሬክተር።
                                        ቀኛዝማች ደህኔ ወልደማርያም፤ የቀድሞው የፅህፈት ሚኒስቴር ዋና ዲሬክተር።
                                        በጅሮንድ ለጥይበሉ ገብሬ፤ የቤተመንግሥቱ ዕቃ ቤት በጅሮንድ።


                                                              ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ።
             2. በአላጌ ግንባር
            ዋና አዝማች፤ ራስ ሙሉጌታ ይገዙ -- የጦር ሚኒስትር።
             በውስጣቸው:        ቢትወደድ መኮንን ደምሰው፤ የወለጋ ገዥ።
                                    ራስ ከበደ መንገሻ፤ የግድም ኤፍራታ ገዥ። 
                                    ራስ ጌታቸው አባተ፤ የከፋ ገዥ።
                                    ደጃዝማች ወዳጄ ውቤ፤ የወሎ እንደራሴ።
                                    ደጃዝማች ወልደማርያም በዳዳ፤ የገሙ ገዥ።
                                    ደጃዝማች አውራሪስ ዱሉ፤ የመንዝ ገዥ።
                                    ፊታውራሪ በየነ ሰራዊቱ፤ የወለኔን ጦር ይዘው።
                                    ቀኛዝማች አበበ ረዴ፤ የማለፍያ ጠመንጃ ያዥን ጦር ይዘው።


                                                      ክቡር ራስ ሙሉጌታ ይገዙ።
             3. በሽሬ ግንባር
            ዋና አዝማች: ራስ እምሩ ኃይለስላሴ -- የጎጃም ገዥ።
            በውስጣቸው:       ደጃዝማች አያሌው ብሩ፤ የሰሜን ገዥ።
                                   ደጃዝማች መስፍን ገመቹ፤ የአገው ምድር አስተዳዳሪ።
                                   ደጃዝማች አምባቸው ገሠሠ፤ የቀድሞው ሊቀመኩአስ።
                                   ደጃዝማች አበራ ተድላ፤ የማይጨው ገዥ።
                                   ደጃዝማች አድማሱ ብሩ፤ የየጁ ገዥ።


                                                  ክቡር ራስ እምሩ ሃይለስላሴ።

  ለ/ለደቡብ ጦር፤
            1/ ለቀኝ ደቡብ
            ዋና አዝማች፤ ደጃዝማች ነሲቡ ዘአማኑኤል፤ የሐረር እንደራሴ።
            በውስጣቸው:       ደጃዝማች ሃብተሚካኤል ይናዱ፤ የኩሎ ገዥ።
                                   ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው፤ የኢሊባቡር ገዥ።
                                   ደጃዝማች አበበ ዳምጠው፤ የጎፋ ገዥ። 
                                   ደጃዝማች አምደሚካኤል ሃብተስላሴ፤ የአሩሲን ጦር ይዘው።


                                                ክቡር  ደጃዝማች ነ ቡ ዘአማኑኤል።
             2/ ለግራ ደቡብ
            ዋና አዝማች፤ ራስ ደስታ ዳምጠው -- የሲዳሞ ገዥ።
            በውስጣቸው፤      ደጃዝማች ገብረማርያም ጋሪ፤ የአገር ግዛት ሚኒስትር።  
                                  ደጃዝማች መኮንን ወሰኔ፤ የወላይታ ገዥ።
                                  ደጃዝማች ደባይ ወልደ አማኑኤል፤ በወለጋ ውስጥ የአውራጃ ገዥ።
                                  ፊታውራሪ ታደሰ ገነሜ፤ የአውራጃ ገዥ።


                                                     ክቡር  ራስ ደስታ ዳምጠው።
             3/ ለማህል ደቡብ
             ዋና አዝማች፤ ደጃዝማች በየነ መርዕድ -- የባሌ ገዥ።
            በውስጣቸው:       በጅሮንድ ፍቅረስላሴ ከተማ፤ የገንዘብ ሚኒስትር።
                                   ፊታውራሪ አጥናፍሰገድ ወልደጊዮርጊስ፤ የጉማይን ጦር ይዘው።
                                   ቀኛዝማች አስፋው ወልደጊዮርጊስ።
                                   ቀኛዝማች ሰለባና ቀኛዝማች አንዶም፤ ከኤርትራ ከኢጣልያን ከድተው የመጡ።


                                              ክቡር  ደጃዝማች በየነ መርዕድ።
  ምንጭ:
  የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት
  በዘውዴ ረታ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  ደራሲ እና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያን ጦር ዝግጅት እና አጠቃላይ ሁኔታ እንደሚከተለው ይተርክልናል 

  --------- 

                                የክተት አዋጅ ነጋሪት ሲመታ።

  የኢትዮጵያ ወታደር ብዛት ዊልያም ማኪን ሲገልፅ ከነጀሌው 700,000 ያደርሰውና ".. ካኪ ለብሶ የሚታየው የሰለጠነው ወታደር ግን 25,000 ይሆናል" ይላል። ይህ እንግዲህ በጠቅላላው ኢጣልያንን ሊመክት የተሰለፈው ጦር ነው። 


                         መረብ ላይ የኢጣልያን ዘመናዊ ጦር ለመግጠም የተሰለፈው የኢትዮጵያ ጦር።

  ኢጣልያኖች በሰጡት ግምት የኢትዮጵያ ወታደር 350,000 ነው ይሉና 400,000 ጠመንጃ በያይነቱ፤ 200 መድፍ፤ አምሳ ቀላልና ከባድ ኦርሊኮን (ፀረ አውሮፕላን) አላቸው ብለዋል። ልዎናርድ ሞስሌ እንደፃፈው ደግሞ የኢትዮጵያ ጦር 200 ትናንሽ የተለያዩ መድፎች፤ ለእያንዳንዱ መድፍም 500 ጥይት፤ 3500 መትረየስ፤ 15 አይሮፕላን፤ ለስምንት ወር ከሚበቃ ቤንዚን ጋር ኢትዮጵያውያን ነበራቸው ብሏል።


                       ወደምስራቅ ግንባር የዘመተው የኢትዮጵያ ጦር።

  የኢትዮጵያ ሕዝብ ድል ለመሆን የበቃው በጦር መሪዎቹ የአመራር ችሎታ ማነስና ጠላትን በመናቃቸው ነው። እያንዳንዱ መኩዋንንትም የርስ በርስ ቁርሾ ስላለበት አንዱ አንዱን በመጋፈጥ፤ በጦር ሜዳ ላይ ሹም ሽር በማድረግ፤ ለዘውዱና ለስልጣን የነበራቸው ሽሚያ ሁሉ ተጨምሮ ህዝቡን በአንድነት ሊያስተባብረው ባለመቻሉ ኢጣልያ ድል ለማድረግ ቻለች። ይህን የኢጣልያ ጦር መሪዎች ሁሉ አምነውበታል።


                በዘመናዊ ሁኔታ የሠለጠነው የኢትዮጵያ ጦር በሰልፍ።

  የዚያን ጊዜውን የሁሉንም አሳብ አሁን መናገር አይቻልም እንጂ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ጦር መሪ ምን አይነት ስህተት እንዳደረገ አለፍ አለፍ እያልን በመጠኑ እናየዋለን። የኢትዮጵያ ጦር አማካሪ የነበረው ሩስያዊው ኮሎኔል ኮኖቫሎፍ (T.E. Konovaloff) በመፅሐፉ "... ራስ ስዩም የተከበሩ እና ክብራቸውን የሚጠብቁ ሰው ናቸው... የቶፖግራፊ ካርታ ሳሳያቸው በዚህ ጉዳይ አትጨነቅ። አልፈልገውም። የካርታ ጉዳይ ስሜት ያለው ራስ ካሳ ነው። በእነሱም ላይ ካርታ ብቻ ሲመለከት ብዙ ሰዓት ያጠፋል። ለኔ ግን ምንም ስሜት አይሰጡኝም። በዚህ ምክንያትም እባክህ አታስቸግረኝ ይሉኛል..." ሲል ፅፏል። ኮኖቫሎፍ የሚያቀርበው ካርታ የኢጣልያ ጦር በየት ቢመጣ በየት በኩል መግጠም እንደሚቻል የሚያስረዳ ነበር። ግን ተቀባይነት አጥቶ ጦሩ እንደዝንጀሮ ገደል እየቧጠጠ እንዲዋጋ እና እንዲያልቅ ሆነ።

  በደቦኖ ቦታ የተተካው ዋናው የኢጣልያ ጦር አዛዥ ማርሻል ባዶልዮም ቢሆን በሁዋላ ጊዜ ባሳተመው መፅሐፉ የኢትዮጵያውያንን የጦር መሪዎች ሁኔታ ገልፆታል "... የኢትዮጵያ ጦር አዛዦች በሙሉ የጦር አዛዥነት ችሎታ ፈፅሞ የላቸውም ... ጉዳዩን ሁሉ በቀላሉ የሚገምቱና የምመፃደቁ ናቸው... " ብሏል።

  የባዶሊዮ የቅርብ ረዳት የነበረው ጄኔራል ኯሪኖ አርሜሊኒ (Quivrino Armellini) ስለኢትዮጵያውያን የጦር መሪዎች ሲገልፅ "... ራስ ካሳ፤ ራስ ሙሉጌታ፤ ራስ ስዩምና ራስ እምሩ ስለጦርነት የተማሩት ትምህርት የለም። ... ታላቅ ሰውነታቸ ብቻ ለጦር አዝማችነት አበቃቸው። ... ምንም አይነት የጦር ትምህርት ሳይኖራቸው, በዘመናዊ የጦር ትምህርት የሰለጠነውን ወታደር፤ ዘመናዊውን መሳሪያና ዘመናዊ ጦር አዛዥችን እንዲገጥሙ ታዘዙ። ይህ ነው ድል ለመሆን ያበቃቸው ምክንያት ..." ብሏል።

  ባዶልዮ ስለራስ ካሳ ሲፅፍ "... የማዘዝ ልምድ የለውም። በደህና ጦርነት ቦታ ውሎ ደህና ውጊያ እንክዋን አላየም። ሌላው ቀርቶ የራሱን ወታደሮች እንክዋን ሥራ ማሰራት አይችልም። ወታደሮቹ ግን ምርጥ ምርጦች ናቸው። ባለፈውም ሆነ አሁን የአበሻ ጦር መሪዎች ከፊታቸው ካለው ጠላት ይልቅ ከሁዋላ የቀረውን ወዳጃቸውን ይፈራሉ። በዚህም ፍራቻ ምክንያት ያላቸውን ኃይል ሁሉ ባንድነት ሰብስበው ከጠላት ጋር አይታገሉበትም። ከሀይላቸው ግማሹ ተከፍሎ በመንደር ይቀርና የጌታውን ክብር እንዲጠብቅ ይደረጋል..." ብሏል። በሌላው የመፅሐፉ ገፅ ላይ ደግሞ ይህንኑ ጉዳይ አንስቶ "... በኢትዮጵያውያን ጦር መሪዎች መሃል መለያየት እና የውስጥ መጠራጠር እንደተፈጠረው ሁሉ ወታደሩም ጌታውን እየተከተለ ተሸካክሯል። ለዚህ ሁሉ መለያየት ያበቁት ንጉሡ ናቸው። ... ራስ ስዩም፤ የግል ጉዳይ የሆነ የማዕረግ ነገር ቂም አለባቸው። ራስ ካሳ ጥሩ የቤተክርስቲያን ሰው ናቸው። ሙሉጌታ ጦረኛና በጦር ያደገ ሰው ነው። በዚህም በጦረኛነቱ ምክንያት ጠቅላይ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ ሆኖ ተሾሞ ነበር..." ብሏል።

  ባዶሊዮ ራስ ሙሉጌታን "... ተሾሞ ነበር..." ያለው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ሙሉጌታ ተሽረው ራስ ካሳ ከተሾሙ በሁዋላ ያተተው ነው። ስለራስ ሙሉጌታ መሻርና ስለራስ ካሳ መሾም ባርከር ሲፅፍ "... ንጉሡ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከታላላቅ ሰዎች የተወለዱ ናቸው እንጂ የጦር አመራር ችሎታ ያላቸው አይደሉም። ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነቱ ውስጥ ለመግባት ደሴ ሲደርሱ የስራ መጀመሪያ ያደረጉት ራስ ሙሉጌታን ሽረው የቅርብ ወዳጃቸውን ራስ ካሳን መሾም ነበር። የጦር ሚኒስትሩ ራስ ሙሉጌታ የታወቀ ጎበዝ ሰው ነበር። የሚጠበቀውና የሚፈራውም የሱ ጦር አመራር ነበር። የወታደሮች ወታደር ነበር። ራስ ካሳ ግን ምንም የጦር ጥበብ የማያውቅ ሰው ነው። ከነገሥታት ትውልድ እና በፖለቲካም ተሰሚነት ስላለው ብቻ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ሆነ። ለዚህ ነው ባዶሊዮ የሙሉጌታን መሻርና የካሳን መሾም ሲሰማ የተደሰተው። ..." ካለ በሁላ በሌላ የመፅሐፉ ገፅ ደግሞ "... ሙሉጌታ ተሽሮ ካሳ ሲሾም አምባራዶም ያለው ሙሉጌታና ጎንደር ያለው እምሩ የካሳን ትዕዛዝ ላለመስማት ጆሯቸውን ደፈኑ። ሙሉጌታ የሚደርሰውን ትዕዛዝ እንዳልሰማ እየሆነ ምንም የሰማሁት የለም ይላል። እምሩም የተነሳብኝን ያገር ውስጥ ሽፍታ በመከላከል ላይ ነኝ እያለ አይታዘዝም። የካሳ ትዕዛዝ ተቀባይ አጣ። እነዚህ ሁለት ታላላቅ ጦረኞች የሚያስቡት ሃሳብ ካሳ የሚገጥመውን ገጥሞ እንዲዋረድና ከፍ ያደረገው የንጉሥ አይን ዝቅ እንዲያደርገው ነው ..." በማለት ይተነትናል።

  በርከር "... የተፈራው ጦር የሙሉጌታ ነበር ..." ያለው እውነቱን ነው። ይህን ነገር የኢጣልያ ጦር ጠቅላይ አዛዥ የነበረው ባዶሊዮም በመፅሐፉ እንዲህ ስል ይገልፀዋል "... የጦር ሚኒስትሩ ሽማግሌው ራስ ሙሉጌታ በአድዋ ዘመቻ ክንዱን ያሳየ በመሆኑ የኢትዮጵያን ጦር ፈርተን ብዙ መሳሪያ አከማችተን ነበር። ጦርነቱ እንደተጀመረ ንጉሡ፤ ራስ ሙሉጌታን ሽረው ቄሱን ራስ ካሳን የጦር ሚኒስትር አድርገው በመሾማቸው የኢጣልያ ጦር በቀላሉ ድል እንደሚያደርግ ገብቶን ተደሰትን። በመክዋንንቱ መሃከል ባለው የርስ በርስ ያለመግባባትም ተጠቀምን። ንጉሱም የራስ ሙሉጌታን ሰራዊት እንዲከዳ ስላደረጉ ራስ ሙሉጌታን ከጥቂት ከተረፉ ወታደሮቹ ጋር አዳል በረሃ ውስጥ አግኝተን በአይሮፕላን መትረየስ ገደልነው። በዚህም በሙሉጌታ ሞት የኢትዮጵያውያንን ሞራል ሰበርንው..."

  በኢትዮጵያውያን መሃል ባለው ያለመግባባት እና መለያየት ምክንያት ከውጭ አገር ኢትዮጵያን ለመርዳት የተነሱና በኢጣልያ ግፈኝነት የተበሳጩ የውጭ አገር ሰዎች ሁሉ ተቀባይ አጡ። ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ባወጀች ጊዜ ከእንግሊዝ አገር ብቻ ሶስት ሺህ ሰዎች ኢትዮጵያን ለመርዳት በወዶ ዘማችነት ተመዝግበው ነበር። እ.ኤ.ዓ. ሴፕቴምበር 4 ቀን 1935 ዓ.ም. የወጣው ዴይል ኤክስፕረስ ጋዜጣ "... ንጉሡ ይህን እርዳታ አልተቀበሉትም። ያልተቀበሉበትም ዋና ምክንያት ለነዚህ ሰዎች የሚከፈል ምንም ነገር የለም ብለው ነው። ከኢትዮጵያውያን ጎን ተሰልፈን እንዋጋለን ያሉት እንግሊዞች ብቻ ሳይሆኑ በራንግል አርሚ ውስጥ የነበሩና ካገራቸው የከዱ ሩስያውያን፤ ቱርኮች፤ ሃንጋርያውያኖችና ቼኮዝሎቫክያን ሁሉ ናቸው። ..." ብሏል። ይህ ብቻ ሳይሆን በኒውዮርክ ከተማ ያሉ አሜሪካውያን በሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት የኢጣልያን አድራጎት ተቃወሙ። በማዲሰን አደባባይ የተሰበሰቡ ዘጠኝ ሺህ አሜሪካውያን የሙሶሎኒን ፎቶግራፍ በማቃጠል ተቃውሟቸውን ገለፁ። በኢጣልያ ውስጥም ቢሆን ሳይፈሩ አድራጎቱን የተቃወሙ ሰዎች ነበሩ። በጀርመን ሲኒማ ቤቶችም የሙሶሎኒን ጦር ማጋዝና ማከማቸት የሚያሳየውን "ኢትዮፒያ 1935" የተባለው ፊልም ለሕዝብ እየታየ ህዝቡ ተቃውሞውን ይገልፅ ነበር። በካይሮም የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች በየመስጊዱ ሕዝቡን እየሰበሰቡ ኢትዮጵያን በግፍ ከመጣባት መከራ እንዲያድናት እንዲፀለይ አዘዙ።

  ይህ ሁሉ ቢሆንም ጀናው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሪዎች ስህተትና በመሳሪያ እጥረት ድል እየሆነ ይሄድ ጀመር። ባዶሊዮ ራሱ ሲመሰክር "... የኢጣልያ አይሮፕላኖች ዘመናዊና ባለሙሉ ትጥቅ ባይሆኑ ኖሮ ኢትዮጵያውያን የአድዋውን ድል እንደገና ይደግሙ ነበር። በፓይለቶቻችን ታላቅ ተግባር ኢጣልያኖች ድል ለማድረግ በቃን።..." ብሏል።


  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት
  በጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  ደራሲ እና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ የኢጣልያንን ጦር ዝግጅት እንደሚከተለው ይተርክልናል

  ---------------------------

  ሙሶሎኒ በ1926 ዓ.ም. የቅኝ ግዛቱን ሊብያን ጎብኝቶ ነበር። ሊብያን እየተዘዋወረ ከጎበኘ በሁላ ወደ ሮማ ለመሄድ ከዋናዋ ከተማ ከትሊፖሊ ሲነሳ ለተሰበሰበው የኢጣልያ ሰራዊት ንግግር ሲያደርግ "... ሶማሊያን ጎብኝቻለሁ። ይሄው አሁን ደግሞ ሊብያን ጎበኘሁ። ሁለቱም አሸዋ የተሞሉ ሳጥኖች ናቸው። ወደ ኢትዮጵያ ግፉ። ..." ማለቱን ቤትሪስ የተባለ ደራሲ ዋት ኔክስት፤ ኦ ዱቼ በተባለው መፅሐፉ ገልፆታል። ከዚህ ንግግሩ ቀደም ብሎ በመስከረም ወር ዲስኩር ሲያደርግ "... የኢጣልያ መመርያ መቶ ዓመት በግ ሆኖ ከመኖር አንድ ቀን አንበሣ መሆን ይመረጣል የሚባለውን ፍልስፍና መከተል ነው..." ብሎ ነበር።

  ዱቼ ሙሶሎኒ ከሁለቱም ዲስኩሮቹ በፊት በነሐሴ ወር ብቻ አምሳ ታላላቅ የኢጣልያ የወታደር መርከቦች በስዊዝ ካናል በኩል ወደ ምስራቅ አፍሪካ አልፈዋል። የኢጣልያ መንግስት ወታደሮቹንና የጦር መሣርያውን በስዊዝ ካናል በኩል ሲያሳልፍ 250,000 የእንግሊዝ ፓውንድ ለካናሉ ኪራይ ከፍሏል። የኢጣልያ ጦር ወደ ምስራቅ አፍሪካ ማለት ያን ጊዜ የኢጣልያ ቅኝ ግዛቶች ወደነበሩት ወደ ኤርትራ እና ወደ ሶማሊያ የተጉዓዘው ሰባት ወር ሙሉ ነው።


                             ወደ ኢትዮጵያ የሚጏዘው የኢጣልያ ጦር ስዊዝ ካናልን በመርከብ ሲያቇርጥ።

  ጠቅላላ የጦሩ ዝግጅትና ክምችት ተጠናቆ ያለቀው በነሐሴ ወር ነው። በኤርትራ እና በሶማሊያ የሚከማቸው ጦር ተዘጋጅቶ ካለቀ በሁላ 250,000 የሚሆኑ የኢጣልያ ወታደሮች "ሂዱ" የሚለውን ትዕዛዝ ብቻ ይጠባበቃሉ። ዝግጅቱ በጦር መሳሪያና በወታደር በኩል ብቻ ሳይሆን የወታደሩ ስንቅና ቁስለኛው የሚታከምበት የመርከብ ላይ ሆስፒታሎች ሁሉ ተዘጋጅተዋል። ሙሉ የሆስፒታል ድርጅት ያላቸው መርከቦች ስምንት ሲሆኑ በእነኚህም መርከቦች ውስጥ 6000 ያህል አልጋዎች ተዘርግተውባቸዋል። የእነኚህም መርከቦች ስም ኡራያን፤ ቴቬራ፤ ካሊፎርኒያ፤ ቪዮና፤ ሄለን፤ ቼሳሬ፤ አኩሊያ፤ ግራዲቫ ይባላሉ።

  ዱቼ ሙሶሎኒ ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ. መጋቢት 8 ቀን 1935 ዓ.ም. ለምሥራቅ አፍሪካው የኢጣልያ ጦር አዛዥ ለጄኔራል ደቦኖ በፃፈላቸው ደብዳቤ ላይ "... ጦርነቱ በጥቅምት መጨረሻ ወይም በህዳር ወር እንዲጀመር ይሁን። ... ከሁለቱ ቅኝ ግዛቶቻችን ከጨቸመሩት አንድ መቶ ሺህ ጥቁር ወታደሮች ጋር አሁን ሶስት መቶ ሺህ ወታደር አለህ። በተጨማሪ አምስት መቶ ያህል አውሮፕላኖች ሶስት መቶ መኪናዎችም እልክልሃለሁ። እደግመዋለሁ፤ አስር እልክልሃለሁ። አምስት ዲቪዚዮን ከመደበኛው ወታደር፤ አምስት ዲቪዚዮን ደግሞ በፈቃደኝነት ከምዘምቱ ባለጥቁር ሸሚዞች እልክልሃለሁ። እነኚህም የምልክልህ በጥንቃቄ የተመረጡና የሰለጠኑ ናቸው። ... በጥቂት ሺህ ሰዎች እጥረት ምክንያት የአድዋን ድል አጣነው። ያን ስህተት ዛሬ አንደግመውም። ..." የሚል ቃል ላከለት።


                                     ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የኢጣልያ ጦር ምፅዋ ወደብ ላይ ሲራገፍ።

  ሙሶሎኒ እና ደቦኖ ይህን ደብዳቤ በተፃፃፉበት ጊዜ ኢጣልያ በሁለቱ ቅኝ ግዛቶቿ ያሰፈረችው ጦር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሀገሮችም ማስገበሪያ ጭምር በቂ ነው ተብሎ ተገምቷል። በዚያን ጊዜም 298, 821 ወታደር 19,233 የጭነት እንስሳት፤ 5000 መኪናና ሞተር ብስክሌት፤ 207, 219 ቶን የሚመዝን የጦር መሳሪያ፤ 26,000  መንገድ የሚሰሩ ተራ ኢጣልያኖች በሁለቱ ቅኝ ግዛቶቿ ውስጥ ነበሯት። ሙሶሎኒ በደብዳቤው ለጄኔራል ደቦኖ ቃል በገባለት መሰረት ጦርነቱ ሊጀመር ሲል የጦሩ ዝግጅት ብዛት 360,000 ወታደር፤ 30,000 እንስሳት (በቅሎና ፈረስ)፤ 6500 መኪናና ሞተር ሳይክል፤ ሶስት ሚሊዮን ቶን የሚመዝን የጦር መሳሪያና 50,000 መንገድ ሰሪ ተከማቼ።


                                   ለውጊያ የመጡ አውሮፕላኖች ወደብ ላይ ከመርከብ ሲራገፉ።


                                  ለውጊያ የመጡ ፈረሶች ምፅዋ ወደብ ላይ ከመርከብ ሲራገፉ።

  ኢጣልያ የተዘጋጀችው በጦር መሳሪያ ብቻ አልነበረም። ሰላዮቿ ባቀርቡላት የኢትዮጵያ ሁኔታም ጭምር ነበር። በተለይ ደጃች ኃይለስላሴ ጉግሳ አስጠንተው ለደቦኖ የሰጡት የኢትዮጵያ ካርታ ጥሩ መመሪያ እና ጠቃሚ ሆኗል። ሌሎቹም ሰላዮች ቀደም ብለው በመግባት የመሄጃ መንገዱንና የማጥቂያ ቦታውን ሁሉ አጥንተው አቅርበዋል። ጠቃሚ ጥናት ካቀረቡት ሰላዮችም መሃል ቱሊዮ ፓስቶሪ ይገኝበታል። ቱሊዮ ፓስቶሪ በስለላ ተግባሩ ምን እንደሰራ ለአንጄሎ ዴል ቦካ አጫውቶት አንጀሎ በመፃፉ ፅፎታል። እንዲህ ይላል "... ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ አመታት የቆየሁ ነኝ። 64 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውሬአለሁ። ከንጉሥ ምኒልክ ጋርም ወዳጅ ነበርን። ... በ1924 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) በሁዋላ ጄኔራል የሆነው ካፒቴን ማላድራ (Malladra) ጠራኝ እና አንድ ሚሽን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ስላሰብን አብረህ ለመሄድ ፍቃደኛ ነህን? አለኝ። ... ጅኦሎጂስት ነኝና በኢትዮጵያ ውስጥ በማዕድን ፍለጋ ስም ገብተን የኢጣልያን ጦር በጉዞው ላይ ሊያጋጥመው የሚችሉትን የመንገድ መሰናክሎች ማለት ወንዞች እና ተራራዎችን እንድናጠና ነበር። ... ወንዞች በበጋ እና በክረምት ያላቸውን የውሃ ብዛት ሁሉ በሚገባ እየለካሁ እንዳጠናና ውሃ የምበዛባቸውንም ወንዞች በየት በኩል ማቁዓረጥ እንደሚቻል የመሸጋገሪያውን መልካ ሁሉ እንዳጠና ነበር። ... ዝግጅታችን ካለቀ በሁዋላ በ1928 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) ከእንግሊዛዊው ጂኦሎጅስት ኔስቢት (L.M. Nesbitt) ጋር ሆነን ከአዲስ አበባ እስከ ደንከል በረሃ እስከ ዳሎል ድረስ አጠናን። ... በተለይ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው የባቡር ሐዲድ የሚያልፍበትን የአዋሽን ድልድይ ደህና አድረጌ አጠናሁት። የድልድዩን ደካማ ጎኑንም አጠናሁ። ይህን በምሰራበት ጊዜ በጉዟችን ላይ ለሚያጋጥሙን መኩዋንንቶች ሁሉ በንጉሡ ላይ አድማ አድርገው እንዲነሱም እንሰብክ ነበር። ... አሁን አንዳንድ ሰዎች ደጃች ኃይለስላሴ ጉግሳን ያስከዳው ባሮን ፍራንኬቴ ነው ይላሉ። እሱ አይደለም። ኃይለስላሴ ጉግሳን ያስከዱት የሚስጥር ሰራተኞቻችን ሰርጀንት ኢሬ እና ሲኞር ሜኦ ናቸው። ... በዚህ ስብከታችን ምክንያት ጦርነቱ በተጀመረ ጊዜ ከኢትዮጵያ ጦር ሶስት እጁ ያህል ሳይዋጋ ቀረ። ለምሳሌ እንደ ደጃች አያሌው ብሩ ያሉት ጦራችንን በደስታ ተቀብለው የሸኙ ሰው ናቸው። በዚህ በኩል የፖለቲካ ሰዎቻችን መልካም ውጤት አስገኝተዋል..."

  የኤርትራ ገዢ የነበረው ኮራዶ ዞሊ "... በኢትዮጵያውያን መካከል ከባድ ብጥብጥ እንዲነሳ የመከፋፈሉን ተግባር ያካሄድ የነበረው የኤርትራው ግዛት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አስጨናቂና አስቸኩአይ የመንግስት ግልበጣዎች እንዲጠነሰሱ አድርገናል። ... አብዛኛውም ቅስቀሳችን በትግሬዎችና በአማራዎች መሃል ጥላቻ እንዲፈጠር ነበር። በተለይ በሸዋ ...." በማለት እትዮፒያ ዲ ኦጂ በሚባለው መፅሐፉ ውስጥ ፅፎታል።

  በዝግጅቱ አለመሟላት አዝኖ የነበረው ደቦኖ በዝግጅቱ መሟላት ተደሰተ። በህዋላ ጊዜ በፃፈው መፅሃፉም ይህን ሁኔታ ያብራራና "... አሁን ሁሉም ተልኮልናል። በመጀመሪያ ድቪዝዮናችን ውስጥ የነበሩት ወታደሮች በሚገባ የተመረጡ አልነበሩም። በክፍለ ጦሩ ውስጥ 12,000 መምህራን፤ አራት መድሃኒት ቀማሚዎች ሶስት ጠበቆች፤ ዘጠኝ ሰዓት ሰራተኞችና ብዙ ጠጉር ቆራጮች ሁሉ ወታደር ተብለው ተልከው ነበር። ያኔ የተገኘውን ሁሉ እያጋበሱ መላክ ነበር። ..." ብሏል።

  ሙሶሎኒ ለደቦኖ አንድ ቴሌግራም አሳለፈ። ቴሌግራሙም "... በሶስተኛው ቀን የወደፊት ጉዞህን እንድትጀምር አዝዤሃለሁ። ጥቅምት 3 ቀን እልሃለሁ። ..." የሚል ነበር። እ.ኤ.አ. ጥቅምት ሁለት ቀን ማታ ደቦኖ የሚከተለውን አዋጅ አወጀ። "የበላይ መኮንኖች፤ የበታች መኮንኖች፤ የምድር፤ የባህር እና የአየር ኃይል ወታደሮች፤ ባለጥቁር ሸሚዞች፤ ጥቁር ወታደሮች (አክሰሰሪ) -- በፀጥታ እና በሚደነቅ ዲስፕሊን እስከዚህች ቀን ድረስ ቆይታችዋል። ዛሬ ቀኑ ደረሰ። ግርማዊ ንጉሳችንና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ቤኒቶ ሙሶሎኒ ወሰን አልፋችሁ እንድትጉዋዙ አዟል። ኩራት እና ክብር ወደፊት ይመራችሁዓል። ባለኝ የአዛዥነት ልምድ በመላው ወታደር ዘንድ የጠበቀ ስነ ስርዓት እንዲኖር እፈልጋለሁ። ከባድ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ጉዞ ነው። ጦረኛ የሆነ ጠላት ይጠብቃችሁዓል። የነፃና የጠራ ድል ግን የኢጣልያ ፋሺስት ይሆናል። -- ጄኔራል አሚሊዮ ደቦኖ"

  እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቀን 1935 ዓ.ም. በኛ አቆጣጠር መስከረም 23 ቀን 1928 ዓ.ም. ጦርነቱ እንዲጀመር ትዕዛዝ በተሰጠበት እና የኢጣልያ ጦር በተንቀሳቀሰበት እለት በኢጣልያ ከተሞች በሙሉ የቤተ ክርስቲያን ደውሎች ተደወሉ። ህዝቡ በሙሉ በየከተማዎቹ እየተዘዋወረ ታላቅ በዓል እና ሰልፍ አደረገ። ከሰዓት በሁዋላ ዱቼ ሙሶሎኒ በፓላዞ ቬኔዚያ ሆነው ለመላው የኢጣልያ ሕዝብ ንግግር አደረጉ "... እናንተ ባለጥቁር ሸሚዞች፤ የኢጣልያ ወንዶች እና ሴቶች፤ በመላው ዓለም የተበተናቹ፤ በተራራ ላይ፤ በባህር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ስሙኝ። ለሀገራችን ታላቅ ታሪክ የሚሰራበት ሰዓት ተደወለ። በዚህች በአሁኗ ሃያ ሚሊዮን ኢጣልያውያን በኢጣልያ አደባባዮች ተሰብስበዋል። ... እንዲህ አይነት የህዝብ መሰብሰብ በታሪክ ውስጥ ያቶም ተሰምቶም አይታወቅም። ሃያው ሚሊዮን ሕዝብ የተሰበሰበው ባንድ ልብ፤ ባንድ ፍቃድ፤ ባንድ ውሳኔ ሆኖ ነው። ከብዙ ወራት ጀምሮ የክብራችን መንኮራኩር ሲሽከረከር ቆይቶ አሁን ወደ ግቡ በማምራት ላይ ነው። ጉዞው ፈጣን ነው። ረጅም ጉዞ ሳይግዋዝም አይቆምም። ጉዞው የወታደር ጉዞ ብቻ ሳይሆን የመላው የኢጣልያ ሕዝብ የተባበረ ጉዞ ነው። ጉዞው የአርባ አራት ሚሊዮን ነፍሳት ጉዞ ነው። ... አርባ ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያን በትግስት ጠበቅናት። አሁን ግን በቃ ..." ሙሶሎኒ በዚህ ንግግሩ መላውን የኢጣልያ ሕዝብ ከመቀስቀሱ በፊት የመንኮራኩሯ ጉዞ ተጀምሮ ነበር። ይህ ዲስኩር ከመደረጉ በፊት በዋዜማው ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት የኢጣልያ ወታደር መረብን ተሻግሮ ነበር።


                            ሙሶሎኒ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጁን ለጣልያን ህዝብ ባደባባይ ሲገልፅ።

  "ወደፊት ሂዱ" የሚለው ትዕዛዝ እስኪደርስ ድረስ አንድ መቶ ሺህ የኢጣልያ ወታደር ከወሰኑ ከመረብ አካባቢ ሰፍሮ ነበር። ጄኔራል ቪላሳንታ በመረብ አካባቢ ለተሰበሰበው ወታደር "... መረብ ለአርባ አመታት ያህል የማይጠቅም የሰላም ውል ምልክት ሆኖ ቆየ ... አሁን ግን ያ ወረቀት መቀደዱ ነው..." በማለት ንግግር አደረገ።

  ይህ ወሰን አልፎ የገባው የኢጣልያን ጦር ወሰኑን ያቁዓረጠው በዕለቱ ስልሳ ኪሎ ሜትር ተጉዞ ነው። ወሰኑን አልፎ በዓል ከተደረገ በሁዋላ በጄኔራል ማራቬኛ የሚመራው ሁለተኛው ዲቪዥን ጦር በስተቀኝ በኩል ጉዞውን ወደ አድዋ ቀጠለ። በመሃል ደግሞ በጄኔራል ፒርዚዮ ቢሮሊ የሚመራው ጦር ወደ እንትጮ አቅጣጫ አመራ። በስተግራ በጄኔራል ሳንትኒ የሚመራው ጦር ወደ አዲግራት ተጉዋዘ። በዚህ ጉዞ ላይ ለእያንዳንዱ ወታደር አምሳ ኪሎ ግራም የሚመዝን ጥይት ተደልድሏል። እያንዳንዱ ወታደርም የአራት ቀን ምግቡንና ሁለት ሊትር በሚይዝ ኮዳ ውሃ ይዟል። ፀሐይዋ ሞቅ ባለች ጊዜ ወታደሩ ሁሉ እየዘመረ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይጉዓዝ ጀመር።

  በጦሩ መሃል የጦሩን ሁኔታ የሚከታተሉና ታሪክ የሚፅፉ 300 ጋዜጠኞችና ደራስያን ነበሩ። ጋዜጠኛው ቼስኮ ቶማሲሊ ስለዚያች ጉዞ በመፅሐፉ ሲገልፅ እንዲህ ይላል። "... መንገደኛው ወታደር ሁሉ እያንዳንዱ በሚያልፍበት ቦታ አፈር በጣቱ እያነሳ በምላሱ የአፈሩን ጣዕም ይቀምስ ነበር። ይህም የአፈሩን አይነት ለማወቅና ለመለየት እያሉ ነው። ይህን ምርምር የሚያደርጉበት ምክንያት ከጦርነቱ በሁዋላ የምያለሙትን መሬት ለመምረጥ ብለው ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ ያገኙትንና የቀመሱትን ሁሉ ጥሩ አፈር ነው እያሉ ይነጋገራሉ። እልፍ ባሉ ቁጥር ደግሞ የተሻለ አፈር ያገኙና ይሄ የበለጠ ነው ይላሉ። ይሄ ባመት ሁለቴ ሰብል ይሰጣል። ይሄ ደግሞ በዓመት ሶስቴ ሰብል ይሰጣል እያሉ እየተነጋገሩ ይጉዋዛሉ..." ብሏል።


                                                       የኢጣልያን ጦር መረብን ሲያቇርጥ።

  የኢጣልያ ጦር ያለምንም ተከላካይ ተጉዋዘ። የኢትዮጵያ መንግስት የኢጣልያ መንግስት ወሰን አልፎ መጉዋዙን ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ አመለከተ። ኢጣልያ መረብን እንዳትሻገር እንዲከላከሉ ራስ ስዩም ታዘው ነበር። ራስ ስዩም ግን በስፍራው አልተገኙም።

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት
  በጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
 • @መርሻ   2 years ago
  Interested in just about everything!
  ጳውሎስ ኞኞ፣  በኢትዮጵያ  እና  በኢጣልያ  መካከል  በሊግ  ኦፍ  ኔሽንስ  የተደረገውን  ክርክር  ምን  ይመስል እንደነበር በሚከተለው መልኩ አቅርቦልናል ...

  ------------------

  የኢጣልያ ሰራዊት ወሰን አልፎ አፍዱብ ድረስ መያዙንና ወደ አዶና ወደ ገርለጎቢ መንገድ መስራት መጀመሩን ጭምር ኢትዮጵያ ታህሳስ 15 ቀን 1927 ዓ.ም. ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ አመለከተች። ኢጣልያንም ከቅኝ ግዛቱ ወሰን ያለማለፉንና ከግዛቱም ያለመውጣቱን ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ በሰጠው መስል አረጋገጠ። ኢጣልያ እንደ እውነተኛ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሐሰተኛ ተቆጥረው ኢጣልያን በመፍራት ብቻ ክርክሩ ቆመ። በዚያን ጊዜ የፈረንሳይ ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት ሙሴ ረኔ ለእንግሊዙ ለሚስተር ኤደን ይህንን ጉዳይ አንስተው ሲያጫውቱ "... ይሄ የሀበሾች ጥያቄ እኝደማቹሪ ጉዳይ መጥፎ ጠረን ይሸተኛል ..." አሉ ሲል አቭዎን ፅፎታል።

  ኢጣልያ ወሰን እየገፋ ሄደ። ገርጉቢ ደረሰ። ይህንኑ ገርጉቢ መድረሱን የኢትዮጵያ መንግስት ታህሳስ 25 ቀን 1927 ዓ.ም. ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ አመልክቶ ከወሰን መግፋቱ እንዲታገድ ሲል ፍርድ ጠየቀ። በዚህ ጊዜ በሊጉ ስብሰባ የእንግሊዝ መንግስት ተወካዮች የሆኑት ሰር አንቶኒ ኤደን፤ የፈረንሳይ መንግስት ተወካይ የሆኑት ላቫል ባንድነት ሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ የሆኑትን በጅሮንድ ተክለሃዋርያትን በአሳብም ሆነ በሞራል ድጋፍ ተጫኗቸው። ጉዳዩም ለጥር 9 ቀን ተቀጠረ።

  ጥር 9 ቀን የተሰበሰበው ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ኢጣልያን በመፍራት ብቻ እውነተኛ ፍርድ መፍረድ አቅቶት ጉዳዩን ለመጎተት ሲል በኢትዮጵያ እና በኢጣልያ መሃል ያለውን ጉዳይ አጀንዳ እንዲይዝ በማለት ወሰነ። የኢጣልያ መንግስት ተወካይም "ይህ ነገር በሁለቱ መንግሥታት ስምምነት በሰላም የሚያልቅ እንጂ ይህን ማህበር ሊግ ኦፍ ኔሽንስን አያገባውም። ምክንያቱም ጉዳዩን የሁለቱ አገራት ተካላዮች በስምምነት የሚወስኑት ስለሆነ በአጀንዳ መያዝ የለበትም" ሲል አመለከተ። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይም "ጉዳዩ በሰላም የሚያልቅ ከሆነ ሃሳቡን እንቀበላለን" አሉ።

  ኢጣልያ በሰበብ አስባብ ጉዳዩን ከሊግ ኦፍ ኔሽንስ አጀንዳ ካወጣ በሁላ ሰላማዊ ንግግር መጀመሩ ቀርቶ ጦሩን በቅኝ ግዛቶቹ ማከማቸት ጀመረ። የኢትዮጵያ መንግስትም እንደገና "... የኢጣልያ መንግስት በሶማልያና በኤርትራ ጦር ማከማቸት ላይ ነው። ... ከዚህ በፊት ጉዳዩን በሰላም እንጨርሳለን በማለት ለዚህ ጉዳይ ቃል በገባው መሰረት ለመፈፀም አሻፈረኝ ብሏል..." በማለት ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ መጋቢት 8 ቀን አመለከተ።

  መጋቢት 13 ቀን የተሰበሰበው ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጉባኤም "... ሁለቱ መንግሥታት ማለት ኢጣልያ እና ኢትዮጵያ ወሰን የምያካልላቸው ሌላ 3ኛ ዳኛ በ30 ቀናት ውስጥ በስምምነት መርጠው ለጉባኤው እንዲያቀርቡ፤ ባያቀርቡ ጉባኤው ተጨማሪውን 3ኛ ዳኛ ይመርጣል ..." ሲል ወስኖ ተበተነ።

  ጉባኤው ስለሶስተኛው ዳኛ ወስኖ ከተበተነ ከ15 ቀን በሁላ የኢጣልያ መንግስት ሚያዚያ 2 ቀን ለሊጉ ዋና ፀሀፊ ባቀረበው ማመልከቻ "... እኛ በሰላም መንገድ በዲፕሎማቲክ በኩል ጉዳዩን ለመጨረስ ስንችል፣ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ዳኛ መርጣችሁ አቅርቡ ያለን ያለአግባብ ስለሆነ ውሳኔው ይነሳልን ..." ሲል አመለከተ። ሚያዚያ 7 ቀን የተሰበሰበው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጉባኤ በፈረንሳይ እና በጀርመን መሃል ስላለው ነግር ተነጋግሮ ሲጨርስ የሊጉ ፀሀፊ የኢትዮጵያንና የኢጣልያን ጭቅጭቅ አቀረቡ። የሁለቱም መንግሥታት ማለት የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ መልዕክተኞች በጉባኤው ላይ የየበኩላቸውን አቤቱታ አቀረቡ። በመጨረሻ የጉባኤው ፕሬዚዳንት "... ሁለቱ መንግሥታት ዳኛ መርጠው ነገሩን በሰላም እንዲጨርሱ ወስነናል። በመሃላቸው ያለው ጉዳይም ይሄን ያህል አስጨናቂ አይደለም። እንነጋገርበትም ከተባለ ለግንቦት ወር አጀንዳ ይያዝላቸው..." በማለታቸው ለግንቦት 17 ቀን አጀንዳ ተያዘለት።

  የቀጠሮው ቀን እስኪደርስ ድረስ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ፔር ላቫል ከኢጣልያ ጋር ሮም ውስጥ የተለያየ የወዳጅነት ውል ተፈራረሙ። በቀጠሮው መሰረት ግንቦት 17 ቀን የተሰበሰበው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጉባኤም " ... በኢጣልያ እና በኢትዮጵያ መሃል ያለው ክርክር በወሰን አካላይ ዳኛ የሚያልቅ ስለሆነ ወሰናቸውን በዳኛ ይካለሉ። ኢጣልያ የጦር ያይሏን በግዛቶቿ ታከማቻለች የተባለው ግን በማስረጃ ተደግፎ ያልቀረበ ስለሆነና ቢቀርብም ደግሞ አንድ መንግስት በግዛቱ ጦር እንዳያስቀምጥ የሚከለክል ሕግ ስለሌለ የኢትዮጵያን መንግስት አቤቱታ አልተቀበልንውም። ... በዚህ መሰረት ለወሰን አካላይነት የሚመረጡት ዳኞች ስራቸውን ይቀጥላሉ። ሪፖርታቸውንም ለመስማት ጉዳዩ ለጁላይ 25 ተቀጥሯል። ..." በማለት ወሰነ።

  የኢጣልያ መንግስት ለወሰን ተካላይነት በበርሊን የኢጣልያ አምባሳደር የሆነውን ኮንት ሉዊጂ አልድሮቫንዲ (Aldrovandi) እና ራፋኤል ሞንታኛ እንዲሆኑ መረጠ። ኢትዮጵያም በኢንተርናሽናል ሕግ አዋቂነት የታወቁትና በፓሪስ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ጂኦፍሬ እና በኢንተርናሽናል ሕግ በኒውጀርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑትን ፒትማን ፖተር ዳኛ እንዲሆኑላት መረጠች። ሙሶሎኒ ይህን የኢትዮጵያን ምርጫ በመቃወም ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ በፃፈው ደብዳቤ "... የኢጣልያ መንግስት እንዳደርገው ሁሉ የኢትዮጵያም መንግስት ዳኞቹን መርጦ ማቅረብ ያለበት ከኢትዮጵያውያን እንጂ ከውጭ ሃገር ሰው መሆን የለበትም ..." አለ። ተቀባይ ግን አላገኘም።

  የእነዚህ የተመረጡት ዳኞች ጉባኤ ግንቦት 29 ቀን ሚላን ውስጥ ተሰበሰበ። ጉባኤው ለጉባኤው ፀሐፊነት አራት ሰዎች እንዲመርጡ ወስኖ ሶስቱ ኢጣልያውያን ማለት በኢጣልያ ቅኝ ግዛት ሚኒስቴር ዋና ዲሬክተር የሆኑት ኢንሪኮ ቼሩሊ፤ በኢጣልያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲሬክተር የሆኑት ጉአርናስኬሊ (Guarnaschelli) እና ካፒቴን ዛንኪ (Zanchi) ሲመረጡ ሌላው አራተኛ ፀሀፊ ኢትዮጵያ ለዳኝነት የመረጠቻቸው የጆፍሪ ልጅ ሬይሞንድ ነበር። ጉባኤውም ሌላ ሥራ ሳይሰራ ይቺው ሥራ ሆና በዚህችው ምርጫ ብቻ የሚቀጥለው ስብሰባ ጁን 25 ቀን ሆላንድ ውስጥ እንዲሆን ወስኖ ተበተነ።

  ጁን 25 (ማለትም ሰኔ 18) ቀን ሆላንድ ውስጥ በተደረገው ስብሰባ ከኢጣልያ በኩል ፕሮፌሰር ሊሶ እና ሌሎችም የኢጣልያ መኩዓንንት የኢጣልያን መንግስት ወክለው፤ በኢትዮጵያም በኩል የፓሪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ጋስቶን ዤዜ (Jeze) እና በፓሪስ የኢትዮጵያ መንግስት ሚኒስቴር የነበሩት በጅሮንድ ተክለሐዋርያት የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው ተሰበሰቡ። ስብሰባው ከየመንግሥታቱ ተወካዮች ጋር ከተዋወቀ በሁላ ሌላ ፋይዳ ያለው ሥራ ሳይሰራ ለሰኔ 27 ቀን ተቀጣጥሮ ተነሳ።

  ሰኔ 27 ቀን በተደረገው የወሰን አካላይ ዳኞች ጉባኤ ፕሮፌሰር ሌሶና የኢጣልያ መንግስትን አሳብ አመለከቱ። ንግግራቸውም ያው የተለመደው ወሰን አላለፍንም፤ በሰላም እንካለል የሚለው ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ የሆኑት ፕሮፌሰር ዤዜ ደግሞ ጠቅላላውን ሁኔታ አመልክተው የወልወልን ግጭት በማስረጃ እየደገፉ አስረዱ። ዳኞቹም በፕሮፌሰር ዤዜ ንግግር ተመስጠው እውነተኛውን ፍርድ ለመፍረድና የኢጣልያን ወሰን ገፊነት አውቀው ውሳኔ ሊያሳልፉ ሲሉ ፕሮፌሰር ሊሶና ተነስተው "... በዚህ ጉዳይ መነጋገር የለብንም..." በማለት አመለከቱ። ከኢጣልያ በኩል የተመረጡት ሁለቱ ዳኞች "የሊሶና ሃሳብ ትክክል ነው። መነጋገር የለብንም" ሲሉ በኢትዮጵያ በኩል የተመረጡት ዳኞች ደግሞ "የኢትዮጵያ መንግስት በማስረጃ የተደገፈ አቤቱታ ስላቀረበልን በማስረጃው መሰረት መነጋገር አለብን" ሲሉ ተከራከሩ። በዚህ ጭቅጭቅ ብቻ ጊዜው አልፎ ጉባኤው ተዘጋ።

  የሁለቱ መንግሥታት ክርክር የሚወስነው ወሳኝ አጥቶ ጉዳዩ ወደተጀመረበት ወደ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ተመለሰ። ሐምሌ 24 ቀን የተሰበሰበው ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጉባኤ "አንድ ሌላ አምስተኛ ዳኛ ይጨመርና የሱ ቃል ወሳኝ (ቬቶ) ይሁን" አለ። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ፕሮፌሰር ዤዜ ጉዳዩ ምንም ያማያከራክር ወልወል የኢትዮጵያ ግዛት መሆኑን በበቂ ማስረጃ አስደግፈው አመለከቱ። የኢጣልያ ማንዣበብ ወጥሮ የያዛቸው የጉባኤው ዳኞችም የኢትዮጵያን መንግስት አቤቱታ ሳይቀበሉ "የሁለቱ አገሮች ችግር ተጠንቶ ለሴፕቴምበር 4 ይቅረብልን" በማለት በድፍን ጉባኤውን ዘግተው ተነሱ።

  ሴፕቴምበር 4 ወይም ነሐሴ 29 ቀን የተሰበሰበው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጉባኤውም "... በወልወል የተነሳው ግጭት አጋጣሚና ያልታሰበበት ድንገተኛ ነው። ይህም መሆኑን ሁለቱም መንግሥታት አምነዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ወልወል ግዛቴ ነው ስል የኢጣልያ መንግስትም ወልወል የኔ ግዛት ነው ብሏል። በቦታው ላይ የተጣለው ቦምብ እና የደረሰው እልቂት ቢሆን በኢንተርናሽናል ደረጃ ሲታይ ይህን ያህልም አስደናቂ አይደለም። ... " ብለው መላ የሌለው የፍራቻ ውሳኔ ወሰኑ። የኢትዮጵያን የክስ አቤቱታ ማየት የጀመረው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጉባኤ አለቀ። የኢጣልያም ጦር ክምችት ተጠናቀቀ። በጥቅምት ወር 1928 ዓ.ም. ኢጣልያ በየአቅጣጫው ጦር ከፍታ ወሰን እያለፈች አገር መያዝ ጀመረች።

  ምንጭ:
  የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት
  በጳውሎስ ኞኞ
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (30)


 • @መርሻ   6 months ago
  Interested in just about everything!
  ይህንን ጥያቄ የስድስተኛ ክፍል ልጄ ጠይቆኝ በቅጡ ማብራራት አልቻልኩም። ሰዋስው ላይ ተገቢውን ማብራሪያ አገኛለሁ ብዬ አስባለሁ። አመሰግናለሁ!
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  ባለፈው ስለእኚህ ወይዘሮ የተፃፈውን መፅሃፍ ሳነብ በልጅነት የተዳሩበትን እድሜ ሳይ ደንቆኝ ነበር! ባጠቃላይ ሸዋረገድ ገድሌ ከልጅነት እድሜቸው ጀምሮ ያከናወኗቸው ተግባራት በሙሉ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው። እናመሰኛለን ተፈሪ!
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን Kebe_T.D! ለጥያቄውም ሆነ ለመልሱ።
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን አማን!
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  haha ... I second that @Gosa
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን ደሞዜ! አባ ጉራች እና አባ ሻንቆ ተቀራራቢ ትርጉም ያላቸው የፈረስ ስሞች ይመስሉኛል። ሁለቱም ጥቁር ፈረስን ይገልፃሉ :)
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  I like this man! Thank you!
  ጎራዴ መዞ ሲሄድ ከቤቱ፣ 
  ወየው ሰው ፈጀ አለች እናቱ። 

  እንኳን እናቱ የወለደችው፤ 
  ኮራች አማቱ የተጋባችው።
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እናመሰግናለን ጎሳ! እውነት ነው፤ ተመሳሳይ ቃል በዓነጋገር ስልት ወይም በሰውነት ሁኔታ ብቻ በሰዎች ዘንድ የተለየ አስተያየት ሊያስከትል ይችላል።
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  Thanks, Tariku! Most of his songs are nostalgic ... I have no idea what they are about but I enjoy listening to them!
 • @መርሻ   1 year ago
  Interested in just about everything!
  እኚህ ጉደኛ ሰውዬ እንደዚህም ብለው ነበር:
  አለቃ ገብረ ሃና በተሾሙበት ደብር የሚያገለግል አንድ መልከ ጥፉ ፉንጋ ደብተራ ይኖር ኖሮ አንድ ቀን ይህ ሰዋ አለቃን ያለ ጫማ ሲሄዱ አያቸውና መምህር ምነው በባዶ እግርዎ ጫማ አይገዙም? ቢላቸው፣ እስቲ አንተ ፊት ግዛ እኛ ደግሞ ኋላ እንገዛለን አሉት ይባላል።
 • Load more...
loader Loading content ...