
Topics (15)
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
-
-
-
-
-
-
-
-
-












Explanations (12)
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
የሲዳማ ብሄር የራሱ የሆነ አዲስ አመት አለው፡፡ ፍቼ ወይም ጨምበላላ የአዲስ ዓመት በዓል አከባበር ሲሆን በሲዳማ ብሄር ጉዱማሌ ተብሎ ይጠራል:: የአዲስ አመት ክብረ በዓሉ በየአመቱ ለሁለት ሳምንታት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ ይህ የአዲስ ዓመት በዓል በሲዳመኛ ቋንቋ ፍቼ ተብሎ ይጠራል፡፡ የአዲስ አመቱ መግቢያ ትክክለኛ ቀን የሚወሰነው በብሄረሰቡ አያንቶዎች በሚባሉ ባህላዊ ኮከብ ቆጣሪዎች ነው፡፡ አያንቶዎች ቀኑን ወስነው ለማህበረሰቡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ የበዓሉ አከባበር ባሀላዊ ስርዓቱ ጠብቆ ይከበራል፡፡
የዚህ ዓመትም የፍቼ ጨምበላላ ሐምሌ 8/2007 በሐዋሳ ከተማ ተከብሯል::
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
ዋልያ በኢትዮጵያ፣ በሰሜን ተራራዎች እና ራስ ደጀን ተራራ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ የዱር አጥቢ እንስሳ ነው:: ዝርያውም ከፍየል እና የበግ (Caprini) ይመደባል:: ዋልያ በሌላ አፍሪካ አገሮች ከሚገኙት የሰሃራው ባርባሪ በግ እና የኑቢያ አይቤክስ ብቸኛ ዝርያ ካስባሉት ምክንያቶች፦ በማንኛውም ወቅት መራባቱ፣ የቀንዱ ወፈር ማለት እና ማጠር፣ ጢሙ አጠር ማለቱ እና የቆዳው ቀለም ጠቆር ያለ ቡኒ መሆኑ ነው::
ባብዛኛው ጊዜ የወንዱ ዋልያ ወደ 125 ኪሎ ሴቷዋ ደሞ 80 ኪሎ ግራም ክብደት አላቸው:: ወንዶቹ ጠቆር ያለ ቡኒ ቀለም ሲኖራቸው፣ የሴቶቹ ፈካ ያለ ቡኒ ነው፡፡
ዋልያዎች በቡድን ከመሰባሰብ ይልቅ ብቸኝነት ያዘወትራሉ:: በይበልጥ በስሪያ ወቅት ተነጥለው ለብቻቸው ይሆናሉ:: ከ150 እስከ 165 ቀኖች የተጀ እርግዝና በኋላ 1 ወይም 2 ግልገል በመውለድ ይታወቃሉ::
በዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ማኅበር እንደሚገለጸው ይህ ብርቅዬ እንስሳ በመጥፋት ላይ ነው:: ለዚህም ተጠያቂው ዋነኛ ጠላቶቻቸው፤ ለትልልቆቹ ጅብ፣ ለግልገሎቹ ቀበሮና የሎስ ሲሆኑ የሰዎችም የመኖሪያ ሥፍራቸውን በመንጠቅ ዋነኛው ነው::
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሪፖርተር፣ ውክፔዲያ
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
ጢያ ትክል ድንጋይ በዩኔስኮ 1980 ተመዝግቦ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሲሆን በደቡብ ክልል ወደ ቡታጂራ መሄጃ መንገድ ላይ ሶዶ ጥያ ከተማ ውስጥ ይገኛል:: ይህ ትክል ድንጋይ ብዛቱ ወደ 36 የሚጠጋ ሲሆን የተለያየ ስፋት፣ ርዝመት(1 እስከ 5 ሜትር) እና ውፍረት አለው:: 32ቱ ትክል ድንጋይ ላይ የተለያየ ምስል (የጎራዴ፣ የጦር፣ የጨረቃ፣ ጸሐይ መሰል፣ የእጅ እና ምንነቱ መለየት ያልተቻለ ቅርጽ) ተቀርጾባቸዋል::
ጢያ ትክል ድንጋይ ተመራማሪዎች በአሁኑ ጊዜ በሶዶ፣ በስልጤና ጌድዮ አካባቢ ካሉት መቃብር ጋር በማነጻጸር ታላላቅ ሰዎች የተቀበሩበትን ለማመላከት የተተከለ እንደሆለ ይገምታሉ::
ምንጭ:- ኢትዮጵያን ሪጶርተር፣ እና የዩኔስኮ (unesco) ድረ ገጽ
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
አባባ ተስፋዬ በባሌ ክፍለ ሃገር 1924 ዓ.ም. ተወለዱ:: በልጅነታቸው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት ተምረዋል:: የመጀመሪያ ስራቸው ተዋናይነት እንደሆነ የሚነገርላቸው አባባ ተስፋዬ በወቅቱ የሴት ተዋንያን ባለመኖሩ ወክለው ይተውኑ ነበር:: “ኤዲፐስ ንጉስ”፣ “አሉላ አባነጋ”፣ “አቴሎ”፣ “ስነ ስቅለት” እና “ሀ ሁ በስድስት ወር” የተወኑባቸው የመድረክ ስራዎች ሲሆኑ የድርሰት ስራዎችም አበርክተዋል::
አባባ ተስፋዬ ከተውኔቱ በበለጠ ከህዝ ዘንድ ያገነናቸው ስራ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የህጻናት እና የልጆች ተረት በሚያቀርቡበት ጊዜ ነው:: አባባ ተስፋዬ ተረቶቻቸው ምክር አዘል ከመሆናቸውም በላይ በድርጊት የታገዙ በመሆናቸው በብዙ ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ዘንድ ልዩ ትዝታ አላቸው:: እንዲሁም 4 የተረት ድርሰት መጻህፍት ጽፈዋል::
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
አቤ ጉበኛ በባህርዳር አቸፈር ወረዳ ውስጥ ሰኔ 25 ቀን 1933 ዓ.ም. ተወለድ:: አቤ በልጅነታቸው የቄስ ትምህርት ንባብ፣ ዜማ፣አቋቋምና ቅኔን ከተማሩ በኋላ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባህርዳር ሁለተኛ ደረጃ ደሞ በአዲስ አበባ ተምተዋል:: ለተወሰነ ጊዜ በማስታወቂያ ሚኒስቴር እና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጋዜጠኝነት ካገለገሉ በኋላ ስራቸውን አቋርጠው ወደድርሰት ሙያ ተዘዋወሩ::
ሁለገብ ደራሲ አቤ አጫጭር እና እረጃጅም ልቦለዶችን፣ ተውኔቶችን፣ ግጥሞችን እና ወጎችን ይጽፉ የነበረ ሲሆን ጭብጦች እንደ ጭቆና፣ ሙስና፣መሀይምነት እና ማህበራዊ ኑሮ ላይ ያተኮሩ ነበር:: በመሆኑም በግዜው ከነበሩት ባለስልጣናት ጋር ተቃውሞም ፈጥሮባቸው እስከ እስር ደርሰው ነበር::
ደራሲ አቤ ወደ 20 መጸሃፎችን ያሳተሙ ሲሆን የ1966 “አልወለድም” በቀዳሚነት የሚጠቀስ ስራቸው ነበር:: “አንድ ለናቱ” የሚባለው ታሪካዊ ልቦለድ ስራቸው ደሞ በቴዎድሮስ ዙሪያ ሆኖ የዘመነ መሣፍንትንም የእርስ በእርስ ውጊያ የሚያሳይ በጥናት ላይ የተደገፈ ታላቅ ጽሁፍ ነው::
ደራሲ አቤ በወቅቱ የሰዓት እላፊ በነበረበት ወቅት በለሊት ሲንቀሳቀሱ በጥይት ተመተው ጥር 30 ቀን 1972 ዓ.ም. ህይወታቸው እንዳለፈ ይነገራል::
ምንጭ:- ታሪካዊ እዝገበ ሰብ፣ ውክፔዲያ
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
ተወዳጁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም. ከአባቱ አቶ ገሠሠ ንጉሴ እና ከእናቱ ወ/ሮ ጌጤ ጉሩሙ አዲስ አበባ ጠመንጃ ያዥ ሰፈር ተወለደ:: ጥላሁን የ14 ዓመት ልጅ ሳለ አያቱ ጋር ወደ ወሊሶ በመሄድ ትምህርት መማር ጀመረ:: የጥላሁን አያት ምንም እንኳን ትምህርቱ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ቢመክሩትም ጥላሁን ግን የሀገር ፍቅር ቲያትር አርቲስቶች ትርኢት ለማሳየት ወደ ትምህርት ቤታቸው በመጡ ጊዜ ከአቶ ኢዮኤል ዮሃንስ ጋር ከተወያየ በኋላ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ:: ለጥቂት ጊዜ ካገለገለ በኋላ ወደ ክቡር ዘበኛ ባንድ ተቀላቅሎ ታዋቂነት ተቀዳጀ::
ጥላሁን በብዛት የአማርኛ አልፎ አልፎ የኦሮምኛና ሱዳንኛ በመዝፈን እንዲሁም ያልዳሰሰው ሃሳብ(ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለቤተሰብ፣ ስለፖለቲካ፣ ስለተፈጥሮ፣ ስለማህበራዊ ጉዳዮች ወዘተ) ባለመኖሩ የመዚቃ ንጉስ እስከመባል ደረሷል:: በመሆኑም በሱ የሂወት ዘመን የነበሩ ህጻናት ሳይቀር አውሮፕላን በሰማይ ሲያዩ “አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሠሠ” በማለት ይዘምሩ ነበር:: ጥላሁን ለረጅም ዘመናት ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው አስተዋጽዎ የክብር ዶክትሬት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስከማግኘት የደረሰ ታላቅ ድምፃዊ ነው::
በግል ህይወቱም ጥላሁን በተለያየ ጊዜ ወ/ሮ አሥራት አለሙ፣ ወ/ሮ ሂሩት መስፍን፣ ወ/ሮ ፊሪያል አህመድ፣ ወ/ሮ ማርታ ሲማቶስ እና ወ/ሮ ሮማን በዙ ጋር በትዳር 14 ልጆችን አፍርቷል:: ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ በ68 ዓመቱ ሚያዚያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ከዚህ አለም በሞት አተነዋል::
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
ሰዓሊ ለማ ጉያ የትውልድ ቦታቸው ደብረዘይት ከተማ ድሎ በምትባል መንደር ሲሆን ጊዜውም ነሃሴ 12 ቀን 1921 ዓ.ም. ነው:: የብዙ ሙያ ባለቤት ሰዓሊ ለማ፤ በግብርና፣ ማስተማር፣ ውትድርና በአየር ኃይል ውስጥ አገልግለዋል:: ውትድርናውን በሻምበል ማዕረግ እያሉ በ1968 ዓ.ም. ጡረታ ወተዋል:: በመቀጠልም ቀደም ሲል ይመኙት ወደነበረው የሥዕል ሙያ ተሰማሩ:: ሻምበል ለማ ተመሳሳይ ሙያ ካላቸው ልጆቻቸው እና ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ አለማቀፍት እና በሃገር ውስጥ መድረክ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል:: ደብረ ዘይት ላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር “የአፍሪካ ሙዚዬም” በሚል ባሰሩት ኤግዚብሽን ሰራዎቻቸው ለጎብኚ ክፍት ነው::
ተፈጥሯዊ አሳሳልን የሚያዘወትሩት ሻምበል ለማ “የሸክላ ገብያ” እና “የደንከል ልጃገረድ” ድንቅ ከሚባሉት ስራዎቻቸው ቀዳሚ ናቸው::
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ከአባታቸው ከታዋቂው የሙዚቃ ሰው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መካኒክ፣ ሾፌር እና የስነ ጽሁፍ ሰው ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙላቷ ገብረስላሴ በጅማ ከተማ መስከረም 1 ቀን 1914 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
አባታቸው ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በልጅ እያሱ ጊዜ የቴሌግራም እና የፖስታ ሚኒስቴር ሆነው በማገልገላቸው አፄ ሀይለስላሴ ስልጣን ሲይዙ በግዞት ወደ ጅማ በላኳቸው ጊዜ ነበር ይድነቃቸው እዛው የተወለዱት፡፡
ይድነቃቸው ተሰማ እንደጊዜው ልጆች ሁሉ በቤት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እና የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን የተከታተሉ ሲሆን የፈረንሳይኛን ቋንቋንም በአሊያንስ፣ በምኒሊክ እና በተፈሪ መኮንን ት/ቤቶች ተምረዋል፡፡ በ1928 ዓ.ም ወደ ፈረንሳይ አገር ለመሄድ ከተመረጡት ሁለት ጎበዝ ተማሪዎች መሀከል አንዱ በመሆን ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ቢሆንም አገራችን በጣሊያን በመወረሯ ምክንያት ጉዞአቸው አልተሳካም፡፡ በጠላት ወረራ ዘመንም በጊዜው ለኢትዮጵያውያን የሚፈቀደውን ትምህርት በጣሊያን ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ በ8 ዓመት እድሜቸው የስፖርት ዓለም ተሳትፎን የጀመሩት ይድነቃቸው ተሰማ በ14 ዓመታቸው ደግሞ የአራዳ ልጆች በመባል የሚታውቁ አቶ አየለ አትናሽ እና ጆርጅ ዱካስ የመሰረቱትን የዛሬውን ዝነኛ እና ባለታሪክ የዛኔውን የሰፈር ቡድን ተቀላቀሉ፡፡
ይድነቃቸው ተሰማ በ1936 ዓ.ም ከወ/ሮ በዛብሽ ተክለማርያም ጋር ትዳር መስርተው እስከ እለተ ሞታቸው ለ43 ዓመት ያህል አብረው ኖረው 11 ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በዚያው አመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንንም እንደመሠረቱ እና በሀገሪቱ የክለቦች ውድድር እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን በመመስረት ካፕቴን በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ለ15 ጊዜ ያህል ተሰልፈው ተጫውተዋል፡፡
ሁለገብ ስፖርተኞች የነበሩት ይድነቃቸው ተሰማ በአጭር ርቀት ሩጫ በቦክስ እና በብስክሌት ስፖርተኝነትም የታወቁ ነበሩ ከሁሉም በላይ ግን ታላቅ እግር ኳስ ተጫዋች የነበሩ ሲሆኑ ለክለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ የወድድር ዘመን በ47 ጨዋታዎች 43 ጐሎችን በማስቆጠር እስከአሁንም ድረስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለሪከርድ ናቸው፡፡
በ1940 ዓ.ም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፀሐፊ በመሆነ የተመረጡ ሲሆን በ1953 የኢትዮጵያ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በ1953 የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴን መስፈርቶች በሙሉ እንዲሟላ አድርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የመሠረቱ ሲሆን የኮሚቴው ፕሬዝዳንት በመሆን ከመስረታው እስከ 1973 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም የ1952 የሮም፣ 1956 የቶኪዮ፣ እና የ1960 የሞስኮ ኦሎምፒኮች የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን መሪ ነበሩ፡፡
በአለም አቀፍ የስፖርት ደረጃ ደግሞ ይድነቃቸው ተሰማ በተጨዋችነት፣ በቡድን መሪነት፣ የአሰልጣኝነት የኢትየጵያ ቡድን ይዘው ከ1940 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የአፍሪካ፣ አውሮፓ ሀገሮች የተዘዋወሩ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ወክለው በአለም አቀፍ የስፖርት ጉባዔ ላይ የተካፈሉት ግን በ1949 ዓ.ም በሱዳን ካርቱም ከተማ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መስራች ጉባዔ ላይ ነበር፡፡
ከዚህ ጉባዔ በኋላ በአደራጅ ኮሚቴነት፣ በምክትል ፕሬዝዳንትነት፣ እና በፕሬዝዳንትነት የአህጉሩን ኮንፌዴሬሽን ለ30 ዓመታታት በታላቅ ትጋት፣ ብልህነት እና ቆራጥነት አገልግለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ይድነቃቸው ተሰማ በሚከተሉት አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ በማገልገል ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው እና ለወገኖቻቸው አኩሪ ታሪክ ጽፈዋል፡፡
- በአፍሪካ ብሔራዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በመስራችነት እና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት፣
- በአፍሪካ የሰፖርት ኮንፌዴሬሽኖች ህብረት ውስጥ በመስራችነት እና በፕሬዝዳንትነት፣
- በአፍሪካ የብሔራዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ውስጥ በመስራችና በክብር ፕሬዝዳንትነት
- በአፍሪካ የስፖርት ሚኒስትሮች ካውንስል ውስጥ በቋሚ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት
- በአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት
- የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባልነት እና
- የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ምሳሌነቱ አቻ የማይገኝለት አገልግሎት ስጥተዋል፡፡
-----ምንጭ - ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፌዴሬሽን ድረ፣ ታሪካዊ መዝገበ_ሰብ 2006 ዕትም -
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
አቶ ገርማሜ ንዋይ በ1953 ዓ ም በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ንቁ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱና የጀኔራል መንግሥቱም ንዋይ ታናሽ ወንድም ናቸው፡፡ ገርማሜ ንዋይ በ1916 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አራዳ ጊዮርጊስ በተባለው አካባቢ ተወለዱ፡፡ ገርማሜ መጠሪያ ስማቸውን የወሰዱት በአጼ ምኒልክ ዘመን ንጉሠ-ነገሥቱን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገላቸው የላቀ ክብርና ሞገስ ከነበራቸው ከእናታቸው አባት ከደጃዝማች ገርማሜ ወልደሃዋርያት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ገርማሜ ንዋይ ዕድሜአቸው ለትምህርት እንደደረሰ ተወልደው ባደጉበትና አባታቸው አለቃ ንዋይ በአለቅነት በሚያስተዳድሩት በአራጻ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ነባሩን ትምህርት ተምረዋል፡፡ በጣሊያን ወረራ ዘመንም ያለችግር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡ ነጻነት አንደተመለሰ ደግሞ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተመዘገቡ፡፡ ቀጥሎም ወደቀዳማዊ ኃይለሥላሌ አዳሪ ት/ቤት ተዛወሩ፡፡ በዚህ ት/ቤት በቆዩባቸጡ ዓመታት የተማሪዎች መሪ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመመረጥ ቻሉ፡፡ ይህ እጋጣሚም ገርማሜ ወደፓለቲካዊ እንቅስቃሌ ለመሳብ ምክንያት እንደሆናቸጡ የሚናገሩ አሉ፡፡ በ1940ዎቹ ወደመጀመሪያ ለከፍተኛ ትምህርት በተላኩበት ሰሜን አሜሪካ ውስጥ የተማሪዎች ማህበር መሪ በመሆን ተመረጡ፡፡ በተማሪዎች ማህበር ሊቀ-መንበርነታቸው በዋሽንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከነበሩት ከቅርብ ዘመዳቸው ከራስ እምሩ ኃይለሥላሌ ጋር በየጊዜው አየተገናኙ በአገራዊ ጉዳይ ላይ ከመመካከራቸውም በተጨማሪ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ተጠሪዎች ከነበሩት ከነልጅ ሚካኤል አምሩ፣ ደጃዝማች ዘውዴ ገ/ሥላሴና ከሌሎች አባላት ጋር በደብዳቤ ግንኙነት በመመሥረት የፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸው ታውቋል፡፡ ገርማሜ ገና ከተማሪነት ዘመናቸው አንስቶ ኮምኒስታዊ አስተሳሰቦችን ያቀነቅኑ አንደ ነበር የውጭ ደራሲዎች ፅፈዋል፡፡ ገርማሜ በ1946 ዓ.ም. ከአሜሪካን ወደኢትዮጵያ እንደተመለሱ መደበኛ ሥራቸውን በአገር ግዛት ሚንስቴር እየስሩ በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ በልዑል ራስ እምሩ እገዛ “የቀጨኔ ክለብ” በሚል የሚጠራውን የፓለቲካ ማህበር በጓደኛሞች የመገናኛ ማህበር ሽፋን መሠረቱ። “የቀጨኔ ክለብ” በህቡዕ የተቋቋመ የፓለቲካ ማህበር መሆኑ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እንደተደረሰበት በይፋ ተዘጋ፡፡ የቀጨኔ ክለብ ቢዘጋም ገርማሜ በወንድማቸው በጀኔራል መንግሥቱ መኖሪያ ቤትና በሌሎችም አመቺ በሆኑ ሥፍራዎች ሁሉ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ቀጠሉ፡፡ የገርማሜ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ የቀዳማዊ ኃይስሥላሴን ሥርዓት በሚቀናቀኑ ወገኖች ሁሉ ይደገፍ እንደነበር ከጊዜ በኋላ ታትመው የወጡ የፅሁፍ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡
ገርሚሚ የንጉሠ-ነገሥቱን ሥርዓት ለመጣል የሚያደርጉትን ትግል ጉልበት ይሰጠዋል ተብሎ ስለተገመተ የጋብቻ ዝምድና አንዲመሠርቱ የተደረገው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን በጠላትነት ከሚፈርጁ ወገኖች እንደነበር የሚጠቁሙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ የገርማሜ ባለቤት ወ/ሮ አያልነሽ ዘውዴ አባታቸው ግራዝማች ዘውዴ ተክለ ማርያም አናታቸው ደግሞ ወ/ሮ እስከዳር ገብረህይወት ይባላሉ፡፡ አባታቸው ግራዝማች ዘውዴ የልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን አሽከር አንደመሆናቸው አባትና ልጅ በነበራቸው የሥልጣን ሸኩቻ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ይቃወማሉ፡፡ የገርማሜ ባለቤት ወላጅ እናት ወ/ሮ እስከዳር ገብረህይወት ደግሞ የንጉሥ ሚካኤል ልጅ፣ የልጅ ኢያሱ ደግሞ የወንድም ልጅ እንደመሆናቸው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አስተዳደር ደስተኞች አንዳልሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሰው ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ታዲያ የገርማሜ ዎለቲካዊ ትግል በባለቤታቸው በወ/ሮ አያልነኸ የግራና የቀኝ ዘመዶች ሁሉ ድጋፍ ያገኝ ነበር፡፡ገርማሜ ይህን መሰሉን ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ እስከ 1947 ዓ.ም. በአገር ግዛት ሚኒስቴር ቆዩ፡፡ በዚሁ ዓመት የቅርብ አለቃቸው የነበሩት ራስ አበበ አረጋይ ተነስተው በምትካቸው ራስ መስፍን ስለሺ የአገር ግዛት ሚኒስትር ሆኑና መጡ፡፡ ራስ መስፍን የአገር ግዛት ሚኒስትር ሆነው ሥፍራውን ከያዙበት ጊዜ አንስቶ አስቀድሞ መረጃው ስለነበራቸው በገርማሜ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር አየጠበቀ መጣ፡፡ በመሃሉም ከግብፅ የአገር አስተዳደር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጋር ገርማሜ የደብዳቤ ልውውጥ መጀመራቸው ይደረስባቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን ጀኔራል ናጊብ የተባለ ወታደራዊ መኮንን የግብፅን ንጉሥ ፋሩክን ከዙፋናቸው አውርዶ ሥልጣን የያዘበት ወቅት ነበር፡፡ ገርማሜ የሚላላኩት ደብዳቤ ይዘት የሚያተኩረው ታዲያ አዲሱ የግብፅ መንግሥት ሹሞ ሽር ለማድረግ ይቻላቸው ዘንድ ተሞክሯቸውን እንዲያጋሯቸው የሚጠይቅ ነበር፡፡ ገርማሜ እያደረጉ ያሉት የደብዳቤ ልውውጥ እንደተደረሰባቸው ወዲያውኑ ከአገር አስተዳደር ሚኒስቴር ከሥራቸው ተነስተው ወደጡረታ ሚኒስቴር እንዲዛወሩ ተደረገ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ የወላይታ አስተዳዳሪ ሆነው በንጉሠ-ነገሥቱ ተሾሙ፡፡ በወላይታ ቆይታቸውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለው እንዳለ ወጋኦጋዴን አስተዳደር ተዛወሩ፡፡ በዚያን ጊዜ በሱማሊያ በኩል ስለኢትዮጵያ መልካም አስተሳሰብ የሌላቸው ቡድኖች በየቦታው ተሰባስበው መዶለት የጀመሩበት አጋጣሚ ስለነበር ገርማሜ ወዴኦጋዴን የተቀየሩበት ዋናው ምክንያት የነዚሀን ወገኖች ምክርና ድጋፍ እንዳያገኙ ታስቦ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ እንደተባለውም ገርማሜ በ1953 ዓ.ም. የተደረገውን መፈንቅለ_መንግሥት የተቀላቀሉት ከኦጋዴን መጥተው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ታህሳስ 5 ቀን በ1953 ዓ.ም. የተደረገው መፈንቅለ-መንግሥት እንደከሽፈ ገርማሜ ከወንድማቸውና ከሌሎች ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን በናዝሬት በኩል ወዴኦጋዴን የማምለጥ እቅድ ይዘው ጉዞ መጀመራቸውን በስም መጠቀስ የማይፈለጉ አንዳንድ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ግን ይህን ስለማቀዳቸው የሚያስረዳ የጠራ ማስረጃ የለም፡፡ ታህሳስ 7 ቀን 1953 ዓ.ም. ይከተሏቸው ነበሩ ኃይሎች ተኩስ ተከፍቶባቸው ወንድማቸው ጀኔራል መንግሥቱ ቆስለው ሲያዙ ገርማሜ ወዲያውኑ ተገደሉ፡፡
-
@ምስጋና 2 years agoYou have two ears and one mouth. Follow that ratio, Listen more, talk less.
ጓድ ውባንቺ ቢሻው የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ፕሬዘዳንት የኮ/ሌ መንግስቱ ባለቤት ሲሆኑ ትውልድ አገራቸው ጉጃም ውስጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሥነ_መንግሥት ታሪክ የብዙዎቹ ርዕሠ_ብሄሮች ባለቤቶች በፓለቲካውም ሆነ በአስተዳደሩ ንቁ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ከአጼ ምኒልክ ዘመን አንስቶ ያሉ ርዕሠ_ብሄሮች ባለቤቶች ለምሣሌ የአቴጌ ጣይቱን፣ የእቴጌ መነንንና የቀዳማዊ አመቤት አዜብ መስፍንን ተሳትፎ ብንመረምር በጉልሀ የሚታዩ ተግባራትን አናገኛለን፡፡ የጓድ ውባንቺ ቢሻው ፓለቲካዊ ሚና ግን ምን እንደነበር በውል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች በተባለው መፅሃፍ ኮሎኔል መንግሥቱ ከሰጡት የምስክርነት ቃል ለመረዳት አንደሚቻለው ጓድ ውባንቺ ቢሻው በቤተሰባዊ አስተዳደር ጠንካራ ነበሩ፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ “አሥራ ሰባት ዓመት ሙሉ በሥልጣን ላይ ስቀይ ከውባንቺና ከልጆቼ ጋር የማሳልፈው ጊዜ በጣም ውሱን በመሆኑ አንድም ቀን ሰለቸን ደከመኝ ሳትል፡ ሳትማረር የልጆቿን ትምህርትና የቤተሰቡን ጣጣ ሁሉ ብቻዋን የተወጣች ነች” ብለዋል፡፡ በ17 ዓመት የአስተዳደር ዘመናቸው ኮሎኔል መንግሥቱ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ከኢትዮጵያ ሲወጡ ጓድ ውባንቺ ቢሻውም አብረው ስለመጓዛቸው በመገናኛ ብዙሃን ከመነገሩ ባሻገር አብረው በይፋ ስለምንም ነገር ያላቸውን አስተሳሰብ የገለጽበት አጋጣሚ የለም፡፡












Comments (0)
Popular topics
ሽፈራው ወይም ሽፈሬ ተክል (Moringa Oleifera)
የኢትዮጵያው ንጉስ አፄ ካሌብ (st. Elesbaan)
ደርግ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ላይ ያቀረበባቸውና ለስቅላታቸው እንደምክንያት የተሰነ...
የ፲፱፻፶፫ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ በፍጥነት ታቅዶ በፍጥነት የተከወነ ነው ይባላል። ለዚህ አባባል እ...
Meskea-hazunan Medhane Alem(Sidetegnaw) Church in Addis Ababa
ዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ ከእንግሊዝ መንግስት ጋር የኢትዮ-ሶማሊያን ድንበር በተመለከተ የተፃፃፏቸው ደብዳቤዎች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የፓትርያርክ ስልጣኗን ለማግኘት ከግብፅ ቤተክርስትያን ጋር ያረ...
ጄነራል ተፈሪ በንቲ ከደርግ የተሰናበቱበት እና ኮሎኔል መንግስቱ ስልጣን ያጠናከሩበት ሂደት ምን ይመስል ነ...