loader

Topics (25)


loader Loading content ...

Explanations (25)


 • @Kemal   8 months ago
  Sewasewer


  ጎሬ በደቡብ ምዕራባዊ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ናት። ከመቱ ከተማ በስተ ደቡብ የምትገኝ ሲሆን፣  የ 8 ° 9'N 35 ° 31'E ኬክሮስ (latitude) እና ኬንትሮስ (longitude) እንዲሁም  2085 ሜትር ከፍታ አለው። ጎሬ በማርም የሚታወቅ ከተማ ነው። በ1960 ወቅት የሙከራ ሻይ ተክል ተጀምሮ ብዙዎቹ አሁንም ተጠናክረው ቀጥለዋል። ከእነርሱም መካከል በ 800 ሺህ ሄክታር ላይ ያለው በኢትዮጵያ ትልቁ የጉመሮ የሻይ ተክል ነው። ከተማው የአውሮፕላን ማረፊያ አለው።

  ጎሬ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ተቆርቁሮ በራስ ተሰማ ናደው ቤተ መንግስት ዙሪያ ያደገ ከተማ ነው። እ.ኤ.አ. በ 2005 ከግዛታዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሢ በተገኘው መረጃ  መሰረት ጎሬ በአጠቃላይ 12,708 የተመዘገበ የህዝብ ብዛት ያለው ሲሆን ፣ ከእነዚህ ውስጥ 6,125 ወንዶች እና 6,583 ሴቶች ናቸው። በ 1994 በተደረገ ቆጠራ መሠረት ደግሞ ይህ ከተማ 7,114 ነዋሪ የነበረው ሲሆን ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 3,322 ወንዶች እና 3,792 ሴት ነበሩ።

  ሐምሌ 9 ቀን 1927 ዓ.ም የግሪክ ዜጎች የሆኑት ቲ ዜዎስ  እና ዶ. ዶናሊስ (T. Zewos and A. Donalis) ከተማውን ከጋምቤላ ጋር ማገናኘት የሚያስችል የ 180 ኪ.ሜ ርቀት ያለው መንገድ ለመስራት ውል ወስደው ነበር ። ይሁን እንጂ ከጅማ እስከ ጎሬ የሚወስደው መንገድ እስከ 1935 አልተገነባም ነበር። ስለሆነም ከጎሬ ወደ አዲስ አበባ ለመድረስ  በጭነት በቅሎ ከ 20-22 ቀናት እንዲሁም  በቅሎችን እየጋለቡ  ከ 14-15 ቀናት ይወስድ ነበር። 

  ከጊዜ በኋላ ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ የጣልያን ወራሪ ኃይሎችን ለመቋቋም ጎሬን መሠረት አድርጎ ለመጠቀም ሞክሯል። ነገር ግን የሱ ተቃዋሚ የነበሩት የወለጋ ኦሮሞዎች በ 1936, በጥቅምት ወር መገባደጃ ከተማዋን ለቆ እንዲሄድ አስደርገውታል። በመሆኑም ህዳር 26 1936 ላይ የጣሊያን 1ኛ የኤርትራ ብርጌድ ወታደሮች ከተማውን ተቆጣጥረውታል።

  ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ፣ ጎሬ  የኢሊባቦር አውራጃ ዋና ከተማ ሆኖ አገልግሏል። በኋላ ግን በ 1978 መቱ ዋና ከተማ ሆኖ ተተክቷል።

  ማጣቀሻ

  • Pankhurst, Richard KP (1968). የኢትዮጲያ ኢኮኖሚክ ታሪክ . አዲስ አበባ: ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ. ገጽ 449.
  • From Entotto to the River Baro (1897), translated by Richard Selzer


 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  ሰው አይነ ምድሩ ሲቀጥን ተቅማጥ ያዘው ይባላል። አይነ ምድሩ ንፍጥና ነጭ መሰል ነገር ካለበት ችግሩ የተቅማጥ በሽታ ይሆናል። ተቅማጥ አደገኛ በሽታ ነው። በታዳጊ አገሮች ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሕጻናት የሞት መንስኤ ሆኗል። በተለይ የአመጋገብ እጥረት ባለባቸው ልጆች በጣም አደገኛ ነው።  ተቅማጥ የሌሎች በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል።

  መከላከል በጣም ጠቃሚ ሲሆን፣ ንፅህናም እጅግ አስፈላጊ ነው። በተለይም መፀዳጃ ቤትን ለሸንትና አይነ ምድርን ለመፀዳዳት፣ እጅንም ከምግብ በፊት መታጠብ እና የህፃናትንና የሌሎች ልጆችን አይነ ምድር መፀዳጃ ቤት ውስጥ መድፋት ይገባል። ልጆች ተቅማጥ ሲይዛቸው ሁልጊዜ ኦ አር ኤስ (ሕይወት አድን ንጥረ ነገር) ይስጧቸው። አዋቂዎች ለመጀመሪያ መድሃኒት ያልበሰለ የዘይቱን ፍሬ፣ ወዘተ ቢሞክሩ፤ አደገኛ ሁኔታ ላይ ካሉ ግን ኦ አር ኤስን መውሰድ ግዴታ ይሆናል። በሽተኛው ቫይታሚንና ማእድናት ያላቸውን ምግቦች መመገብ መቀጠል ይኖርበታል።

  በተቅማጥ ላለመያዝ የመከላከያ ዘዴዎች 
  • መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላና ከምግብ በፊት እጅዎን በሳሙና (ወይም በፓፓያ ቅጠል) መታጠብ።
  • በየምሽቱ መታጠብና በንፁህ ቦታ መተኛት
  • አዋቂዎችና ልጆች ሁለቱም ለሽንትም ይሁን ለአይነ ምድር መፀዳጃ ቤት መጠቀም ይገባቸዋል። ይህ ሳይሆን ሲቀር በሽታዎች በቀላሉ ከአንዱ ወደ ሌላው ይሰራጫሉ። እነዚህን መሰል መልካም ልምምዶች የሚቃወም ባህልና ወግ ካለ ተቃወሙት።
  • ካርቦሀይድሬት ያለባቸውን ጥሩ ምግቦች (ለምሳሌ፣ በቆሎ ወይም ማሽላ) ፣ ፕሮቲን (ሥጋ ወይም እንቁላል) እና አትክልትና ፍራፍሬ ይመገቡ።
  • በየእለቱ ነጭ ሽንኩርትና ካሮት አልፎ አልፎ የፓፓያ ቅጠል 5 ሳንቲ ሜትር ስፋት ያለው ቢመገቡ ትላትሎችንና አሜባን ያስወግዳል።

  በተቅማጥ ከተያዙ መወሰድ የሚገባቸው የቤት ውስጥ መፍትሄዎች
  • በአይነ ምድሩ ውስጥ ምንም ደም እና ትኩሳት የሌለው
   • የምግብ መመረዝ እና የቫይረስ ተቅማጥ- ለልጆች ኦ አር ኤስ፣ ለአዋቂዎች ኦ አር ኤስ እና ቻርኮል (ስለ ኦ አር ኤስ እና ቻርኮል አዘገጃጀት ከታች ይመልከቱ)
   • ኮሌራ (ከባድ ተቅማጥ ሆኖ ተቅማጡ የሩዝ ውሃ የሚመስል) - ኦ አር ኤስ፣ ከዚያም ሆስፒታል። ሆስፒታል ከሌለ ፀረ ተዋሲያን መድሃኒት መውሰድ። ፀረ ተዋሲያን መድሃኒት ከሌለ ደግሞ የዘይቱን ወይም  የማንጎ ሻይ ይሞክሩ (ስለ ዘይቱን ወይም የማንጎ ሻይ አዘገጃጀት ከታች ይመልከቱ)
  • በአይነ ምድሩ ውስጥ ደም ሳይኖር ትኩሳት ያለው
   • ወባ - ሁልጊዜ ኦ አር ኤስ። ሁልጊዜ የሎሚሣር ሻይ፣ የፀረ ወባ መድሃኒት መውሰድ።
  • በአይነ ምድሩ ውስጥ ደም ኖሮት ትኩሳት የሌለው
   • የአሜባ ተቅማጥ - ኦ አር ኤስ፣ የዘይቱንና የማንጎ ሻይ መውሰድ።
  • በአይነ ምድርም ይሁን በሽንት ውስት ደም ያለው እና ትኩሳት አልባ የሆና
   • ቢልሃርዝያ - ኦ አር ኤስ፣ የቻይና ጭቁኝ ሻይ ይሞክሩ፣ ካልሆነ ወደ ክሊኒክ ወይም ሆስጲታል ይሂዱ
  • ደምና ትኩሳት ያለው
   • የባሲለሪ (ባክቴሪያ) ተቅማጥ በሽታ - ኦ አር ኤስ፣ የዘይቱን ማንጎ ሻይ ይሞክሩ። ከአንድ ቀን ሀሗላ መሻሻል ካላሳየ ወደ ሆስፒታል ይሂዱ። ሆስፒታል ከሌለ ፀረ ተዋስያን መድሃኒት ይጠቀሙ። ፀረ ተዋስያን መድሃኒት ከሌለ ተቅማጡ እስኪቆም የቪንሴሮሲያ (vincerosea) አበባና ቅጠሉን ሻይ ይጠቀሙ።
  ... ይቀጥላል


  ምንጭ       
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  የፈንገስ በሽታ በማንኛውም የሰውነታችን ክፍል ሊከሰት ይችላል። ነገር ግን አብዣኛውን ጊዜ የሚገኘው በአውራ ጣቶች ወይም በተቀሩት ጣቶቻችን (የእግር ጮቅ) እና በእግር መካከል ነው። ጭርት እና (ቆርቆሮ መሰል ነጭ መልክ ያለው በአናት ላይ የሚታይ) በፈንገስ የመመረዝ ውጤት ነው። የተመረዘው ስፍራ በየቀኑ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ሲገባው ደረቅ መሆንና በዘይት (ከታች እንደተመለከተው) መታከም አለበት። ከተቻለ ለንፁህ አየርና ለፀሃይ ብርሃን ማጋለጥ ያስፈልጋል። ከተፈጥሮ የተሰሩ ልምሶችን ማለትም የጥጥ ልብሶችን መልበስ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። ሁልጊዜ የበሽታው ምልክት ከጠፋ በኋላ እንኳን ለሁለት ሳምንታት ያህል ህክምናው መቀጠል ይኖርበታል።

  • ነጭ ሽንኩርት   • የነጭ ሽንኩርቱን ዘይት በሽታው ባለበት ቦታ ላይ ማሸት።
   • ይህንን ዘይት ለእግር ጮቅም ይጠቀሙ።
   • በአማራጩ በአውራ ጣት መካከል አዲስ የተሠነጠቀ ነጭ ሽንኩርት ሊደረግ ይችላል።

  • የጉሎ ዘይት ወይም የዘምባባ ዘይት እና ካሲያ አላታ


                 የካሲያ አላታ (የጭርት ቅጠል) ተክል

   • የካሲያ አላታን (የጭርት ቅጠል) አዲስ ቅጠል መውቀጥና ከተመጣጣኝ የጉሎ ዘይት ጋር መደባለቅ። የጉሎ ዘይት ካልተገኘ የዘምባባ ወይም ሌላ የአትክልት ዘይት መጠቀም።
   • አዲስ በማዘጋጀት በቀን ሦስት ጊዜ መጠቀም

  • ፓፓያ ፣ ዘይት እና ደን መሳይ የጭርት ቅጠል
      • አንድ እፍኝ ያህል አዲሱን ደን ቅጠል መሰል የጭርት ቅጠል መፍጨት።
   • የጥሬ ፓፓያ ፍሣሽ 10 ጠብታ ያህል እና አንድ የሾርባ ማንኪያ የጉሎ ወይም የዘምባባ ዘይት መጨመር።
   • ከዚያም ቀላቅሎ ቁስሉን በቀን 3 ጊዜ ማሸት።
   • ንፁህና አዲስ ዝግጅት በየጠዋቱ ማድረግ።

  ምንጭ     
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  እከክ የሚሳክኩ ጥቃቅን ሽፍታዎች በሰውነት ላይ እንዲወጣ ሲያደርግ፣ በእብጠቶችመካከል ጠቆር ያሉ የመርፌ ጫፍ የሚመስሉ ቅርፊቶችይታያሉ። እከክ በተለይ በልጆች ላይ የተለመደ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በጣትና በጣት መካከል፣ በእጅ አንጏ፣ በወገብና በአባላዘር ብልት አካባቢ ይታያል። መነሻው ጥቃቅን የሆኑ ነፍሳት ቆዳን በስተው ሲገቡ ነው። አንድ የቤተሰብ አባል ከተያዘ በጣም ተላላፊ በመሆኑ ሁሉም ቤተሰብ መታከም ይኖርበታል። ንጽህና በጣም አስፈላጊ ነው። መላ ሰውነትን ታጥቦ በቀን አንድ ጊዜ ልብስን መቀየር ተገቢ ነው። ልብሶች የአልጋ ልብስ ጭመር ታጥበው ፀሃይ ላይ መሰጣት ይኖርባቸዋል። የብረትም ይሁን የእንጨት አልጋዎች በነጭ ጋዝ ማጠብ ያስፈልጋል።

  መፍትሄዎች
  • ነጭ ጋዝ (ፓራፊንእና አትክልት ዘይት  1. አንድ ኩባያ ነጭ ጋዝ ከአንድ ኩባያ የአትክልት ዘይት ጋር በመደባለቅ ማዘጋጀት
  2. በቀን  2 ጊዜ ለ2 - 3 ቀናት ሰውነትን በሞላ ጥቦ እከኩ በሚታይበት አካባቢ መቀባት።
  3. ይህ ህክምና በማንኛውም ጥገኛ ትሎች ለሚመጣ የሚያሳክክ ነገር ጥሩ ሲሆን፣ ማሳከኩን አስታግሶ ትሎቹን (ወደ ሌላ የሰውነት አካል እንዳይዛመቱይከላከላል
  • ነጭ ሽንኩርት ዘይት   1. አንድ የሾርባ ማንኪያ በትንሹ የተከተፈ ሽንኩርት ማዘጋጀት።
   2. ነጭ ሽንኩርቱን ከ2 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት ዘይት ጋር በብርጭቆ ውስጥ መቀላቀል።
   3. በቀዝቃዛ ቦታ (2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጠን ባለበት ቦታ) ማስቀመጥ (ለሶስት ዎራት አስቀምጦ መጠቀም ይቻላላ)።
   4. የነጭ ሽንኩርቱን ዘይት በሽታው ባለበት ቦታ ላይ ማሸት።

  ምንጭ     
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  እባጭ ከቆዳ በታች የሚገኝ መግል ያዘለ መመረዝ ነው። ነጭ ሽንኩርት ወይንም ቀይ ሽንኩርት ጥሩ መፍትሄዎች ናቸው። ነጭ ሽንኩርት ሃይለኛና ከባድ ነው። የበሽተኛው ቆዳው ሊቃጠል ወይም ቀለሙ ሊለወጥ ይችላል  ሆኖም ግን ከቀይ ሽንኩርት የበለጠ መፍትሄ ነው። ቁስሉን በነጭ ሽንኩርት ዘይት መጀመሪያ ማጠብ የመድሃኒቱን ክብደትና ሃይለኛነቱን ይቀንሰዋል። በሁለቱም አንፃር የቀይ ሽንኩርት ቅባትን መጠቀም ቀላል ነው።

  • ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት ቆራርጦ ቁስሉ ላይ  በመጠቅለያ መጠቅለል (ለረጅም ቀናት ይህን መደጋገም)
  • በነጭ ሽንኩርት ዘይት ወይንም በቀይ ሽንኩርት ቅባት ማፅዳት (የነጭ ሽንኩርት ዘይት እና የቀይ ሽንኩርት ቅባት ለማዘጋጀት የሚከተለውን ይመልከቱ)  የነጭ ሽንኩርት ዘይት አዘገጃጃት
  • አንድ የሾርባ ማንኪያ በትንሹ የተከተፈ ሽንኩርት ማዘጋጀት።
  • ነጭ ሽንኩርቱን ከ2 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት ዘይት ጋር በብርጭቆ ውስጥ መቀላቀል።
  • በቀዝቃዛ ቦታ (2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጠን ባለበት ቦታ) ማስቀመጥ ( ለሶስት ዎራት አስቀምጦ መጠቀም ይቻላላ)።
  ከቀይ ሽንኩርት የተዘጋጀ ቅባት አዘገጃጀት
  • 30 ግራም ያክል ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ ይክተፉና ለአንድ ቀን በጥላ ስር ማድረቅ።
  • የተፈጨውን ቀይ ሽንኩርት ከትልቅ ቆርቆሮ ሙሉ (375 ግራም) የአትክልት ዘይት ጋር መደባለቅ።
  • በውሃ ማሞቂያ ሙቀቱ ከ100 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሳይበልጥ ማሞቅ።
  • 40 ግራም ሰም አቅልጦ (ወይም ሰም ከሌለ የሻማ ፍሣሽ) በዘይቱ ድብልቅ መጨመር።
  • በደንብ ካማሰሉ በሁዋላ በጥንሽ ዕቃቆች መገልበጥ እና በቀዝቃዛ ስፍራ ማስቀመጥ።

  ምንጭ    
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  የፓፓያ ወተት መሰል ፈሣሽ እና የበሰለ ፓፓያ

   

   • ያልበሰለውን ፓፓያ ፍሣሽ ለመውሰድ በመጀመሪያ ፓፓያውን በተፈላ ውሃ በደንብ ማጠብና መቁረጥ።
   • ከዚያም ነጩን ፈሣሽ በንፁህ ማንኪያ ወይም ስኒ ማጠራቀም።
   • አንድ ሊትር ተፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ላይ ከ3 - 5 ጠብታ የፓፓያ ፍሣሽ አድርጎ ማደባለቅ።
   • በተዘጋጀው የውሃና የፓፓያ ፍሣሽ ቅልቅል ቁስሉን ሦስት ጊዜ ማጠብ (ቁስሉን ለማጠብ እንደ አማራጭ የጨው እና ሙቅ ውሃ ቅልቅል መውሰድ ይቻላል)።
   • ከዚያ ሊበስል ያለውን ፓፓያ ፈጭተው በቁስሉ ላይ ማድረግ (ቁስሉ በጣም ያልመረቀዘ ከሆነ ፓፓያው ያልበሰለ መሆን ይገባዋል)።
   • ይህንንም ዘዴ ጥዋት፣ ከሰዓትና ምሽት ላይ መደጋገም።

  ምንጭ   
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )

 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  ፓፓያ (እንዳማራጭ የማርና የስኯር ድብልቅ መጠቀም ይቻላል)   • ተፈልቶ በቀዘቀዘ ውሃ ቁስሉን ወይም ቃጠሎውን ማፅዳት።
   • ጥሬ ፓፓያ በዛፉ ላይ እንዳለ በጨርቅና በፈላ ውሃ ማፅዳት።
   • ቢላውንም ካፀዳቹህ በሇላ የሞቀ ውሃ ውስጥ መክተት።
   • ውፍረቱ በህፃን ልጅ ትንሽ ጣት መጠን የሆነ ከፓፓያው መቁረጥ።
   • ከዚያም የተቆረጠውን በቁስሉ ላይ በማድረግ በፋሻ መጠቅለል።
   • ለሁለት ሰዓት ያክል እንደታሰረ ማቆየት። ህመሙ ግን ኃይለኛ ከሆነ ወዲያውኑ ያንሱት።
   • ይህን ህክምና በቀን አምስት ጊዜ ያድርጉ። መግሉ ጨርሶ እስኪጠፋ ድረስ ለብዙ ቀን ይፈፅሙት።
   • ዝንቦች እንዳያርፉበት መከላከል።
  ምንጭ   
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  በመጀመሪያ ቁስሉን በንጹህ ቀዝቃዛ ውሃ አብርዱት። ከታች የተዘረዘሩት መፍትሄዎች አላማ መመረዝን (Infection) ለመከላከል ነው።
  • ያልበሰለ ፓፓያ ወተት መሰል ፈሳሽ (ያልበሰለ ፓፓያ ከሊለ ግን በምትኩ ትንሽ ጨው የተፈላ ውሃ ውስጥ አሟሙቶ መጠቀም ይቻላል)   • ያልበሰለውን ፓፓያ ፍሣሽ ለመውሰድ በመጀመሪያ ፓፓያውን በተፈላ ውሃ በደንብ ማጠብና መቁረጥ
   • ከዚያም ነጩን ፈሣሽ በንፁህ ማንኪያ ወይም ስኒ ማጠራቀም
   • አንድ ሊትር ተፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ላይ ከ3 - 5 ጠብታ የፓፓያ ፍሣሽ አድርጎ ማደባለቅ
   • በተዘጋጀው የውሃና የፓፓያ ፍሣሽ ቅልቅል ቁስሉን ማጠብ 
  • የሬት ቅጠል   • እሬቱን በድንብ ማጠብ
   • ስለታማ ቢላዋ ማዘጋጀትና በተፈላ ውሃ ውሥጥ ማፅዳት
   • የቅተሉን ጫፍና ጎን ጎኑን በገሽለጥ
   • ከዚያም የቅጠሉን የውስጥ ክፍል ከላይኛው በማለያየት ቅጠሉን ማሃል ለማሃል መሰንጠቅ
   • ብዙ ፈሣሽ ያለውን የሬት ቅጠል በቃጠሎው ላይ ማሸት
   • በቀን አራት ጊዜ መደጋገም
  1. የገበታ ጨው (በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ጨው ከሌለ ሽንት ጨዋማ ስለሆነ የበሽተኛውን ሽንት ይጠቀሙ)
   • አንድ የሻይ ማንኪያ የገበታ ጨው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ ማሟሟት
   • ከዚያም ለ20 ደቂቃ ማፍላትና እንዲቀዘቅዝ ማድረግ
   • በቀን ሦስት ጊዜ ማጠብ

  ምንጭ  
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  የህክምናው ዋና አላማ ቁስሎች እንዳይመረዙ መከላከል ሲሆን፣ ይህም በሰውነት ውስጥ ያልውን ተፈጥሯዊ ፈውስ ሂደት እንዲሰራ ያደርጋል።
  1. የማር እና የስኯር ቅይጥ :- ስኩዋሩ ማሩ እንዳይፈስ ይረዳዋል። ማር ፀረ-ባክቴሪያ (ፀረ ተንቀሣቃሽ ነፍሳት) ነው። ስለሆነም ቁስሉን በንፅህና ይጠብቀዋል።
   • ማሩን በንፁህ የጥጥ ጨርቅ አስቀምጦ ጎድጉዋዳ ሳህን ላይ ማድረግ። ይህንንም ለአንድ ቀን ያህል በፀሃይ ምድጃ ላይ ማሩ እስኪንጠባጠብና ሰፈፉ እስኪወጣ ያድርጉ። ማሩ አሁን ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ ነው።
   • ቁስሉን መጀመሪያ ይጠቡ
   • ከዚያም ተመጣጣኝ ስኩዋርና ማሩን ደባልቀው ያድርጉበት
   • ቁስሉንም እንደገና ሳያጥቡት በቀን ውሥጥ በተደጋጋሚ በማርና በስኩዋር ድብልቅ ማከም ይገባል።
  2. ስኯር ብቻውን - ስኩዋር ስርገት (Osmosis) በተባለ ዘዴ ርጥበቱን ከጀርሞች ይመጠዋል፣ ከዚያም ጀርሞች ይሞታሉ
   • ቁስሉንም በቀን ሦስት ጊዜ ያክሙት።
  3. የበሰለ ፓፓያ
   • ለስላሳና የበሰለ የፓፓያ ቁራጭ በቁስሉ ላይ ያድርጉበት።
  ምንጭ 
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
 • @Kemal   2 years ago
  Sewasewer
  ምግባችን መድሃኒታችን መሆን አለበት! ትክክለኛ ምግብ ጥንካሬያችንንና የመከላከል አቅማችንን ይገነባል። ይህም በሽታን ለመዋጋትና ለመከላከል ያግዛል። ትክክለኛ ያልሆኑ ምግቦች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያመጣሉ፤ በማንኛውም በሽታና መመረዝ በቀላሉ እንድንጠቃ ያደርጋሉ።

  የሚከተሉት ምግቦች በቀላሉ የሚገኙና ጠቃሚ የምግብ አይነቶች ናቸው
  • ቀላል ኃይል ለማግኘት
   • ስታርች ምግብ :- ካሳቫ፣ ስኯር ድንች፣ ጎደሬ
   • ፍራፍሪዎች :- ሙዝ
  • ኃይል ሠጪና ፕሮቲን (ገንቢ ምግቦች)
   • ጥራጥሬና እህል :- ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ
   • ዳቦ:- ከነጭ ይልቅ ሳይፈተግ የሚዘጋጀው ይመረጣል
  • በፕሮቲን የበለፀጉ ገንቢ ምግቦች
   • የዘይት ዘሮች :- ዱባ፣ ሃባብ፣ ሱፍ፣ ሰሊጥ
   • ጥራጥሬ :- ባቄላ፣ አተር፣ ምስር፣ አኩሪ አተር
   • ስራስር :- ኦቾሎኒ፣ ለውዝ
   • የእንስሳት ተዋፅዖ :- ወተት፣ እንቁላል፣ አይብ፣ ዓሣ፣ ዶሮ፣ ማናቸውም ስጋ
  • ለቫይታሚንና ማእድኖች
   • ቅጠላ ቅጠል :- አረንጏዴ ቅጠል ያላቸው ተክሎች፣ ካሳቫ ቅጠል፣ ምጥጣሽና የምጥጣሽ ቅጠል፣ ቲማቲም፣ ካሮት፣ ዱባ፣ የሽፈረው ቅጠል እና ሌሎች
   • ፍራፍሬ :- ማንጎ፣ ብርቱካንና ሎሚ፣ ፓፓያ፣ ዘይቱን፣ ፓሽን ፍሩትና ሌሎች የፍራፍሬ ጭማቂዎች
  • ለጠንካራ የአካል መከላከል ብቃት - ጥሬ ነጭ ሽንኩርት መመገብ

  ምንጭ
  የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )
 • loader Loading content ...
  Load more...
loader Loading content ...

Comments (1)


loader Loading content ...